group-telegram.com/enqopazion777/1149
Last Update:
✝ስቅለት✝
✍🏽ጌታ ሐሙስ ማታ በ፩ ሰዓት የሐዋርያትን እግር አጠበ በ፪ ሰዓት ራት
በሉ በ፫ ሰዓት ስለ መንፈስ ቅዱስ አስተማረ በ፬ ሰዓት ስለ ሐዋርያት
አስተማረ በ፭ ስለ እራሱ በጌቴሴማኒ ጸለየ ከእዚህ በኃላ በ፮ ሰዓት
በአይሁድ እጅ ተያዘ ልብሱን ገፈው የእንግርግሪት አስረው እያዳፉና
እየገፉ ወደ ሐና ወሰዱት ሊቀ ካህናቱ ሐና ምን እያልኽ ታስታምራለኽ
አለው በስውር የተናገርኩት የለም የሰሙትን ጠይቅ አለው አንዱ ጭፍራ "ከመዝኑ ትትዋሥኦ ለሊቀ ካህናት" ብሎ ፊቱን በጥፊ መታው ጌታም ክፉ ከተናገርኩ መስክርብኝ እንጅ እንዴት በዳኛ ፊት ትመታኛለኽ አለው ከዚያ
በኋላ ከሌሊቱ በ፫ ሰዓት ደግሞ ከሐና ወደ ቀያፋ ወሰዱት ጴጥሮስ ከሩቅ እየተከተለ ገብቶ እሳት ከሚሞቁት ጋራ ተቀምጦ ነበረ ደጃፍ ጠባቂዋ "በለሲዳ ኦ አረጋዊ ብእሲ እንተሁ እምገሊላ ብእሲ" አለችው ደንግጦ
አላውቀውም ኣለ ፪ኛ የማልኮስ ወንድም ኮልስብ ከእርሱ ጋራ አይቼኻለኹ እለው አላየኸኝም ብሎ ካደ አንዲት ሴት መጥታ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነኽ "ቃልከ የዐውቀከ" እንዲል ንግግርኽ ያስታውቅብኻል አለችው እሱም አላውቅም እያለ ይምል ይገዘት ጀመረ ወዲያው ደሮ ጮኸ ጌታ ሥልሰ ትክሕደኒ ብሎት ነበረና ዘወር ብሎ አየው ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሉ ኣሰቀሰ፡፡ ጌታም የሌሊት ድብደባው ሲጸናበት ተሰወራቸው የይሁዳ ዘመድ
የምትኾን አንዲት ሴት ልጇን ታቅፋ ኣገኛትና አትናገሪ አላት እሷ ግን
ወዲያው በእጇ ጠቁማ አመለከተቻቸው ጌታም ትቂት እስካርፍ መታገሥ አቃተሽ ብሎ እስከ ዕለተ ምጽአት ድንጋይ ኹኚ ከዚያ በኋላ አስነሥቼ እፈርድብሻላኹ አላት ወዲያው ድንጋይ ኾነች አይሁድም በጥዋት ወደ ጲላጦስ ወስደው ሊያሰቅሉት መከሩ "ወጸቢሖ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት" እንዲል ይሁዳም ሲወስዱት አይቶ ተጸጸተ እሱ በተአምራት ይድናል እኔ ብሬን ይዤ እቀራለኹ ብሎ ነበረ የማይለቁት ሲኾን ኺዶ እንኩ ገንዘባችኹን አላቸው የምንሻውን ሰጠኸናል የምትሻውን ወስደኻል ኣሉት ብሩን በቤተ መቅደስ በትኖ ሊታነቅ ኼደና ከዛፍ ተሰቀለ ዛፋም "ኦ ይሁዳ ነስሕ ከመ እኁከ ጴጥሮስ" ይላል እንደ ወንድምኽ ጴጥሮስ ንስሓ ግባ ብትለው ከሌላ ኺዶ ተሰቀለ ገመዱ ተበጥሶ በመውደቁ፡ ሰውነቱ ቆስሎ ከዛ ቀን በኋላ ሞተ፡ ጌታ ተይዞ ወደ ዐውደ ምኩናን ሲገባ ፮ ጦረኞች ከበር ቁመው ነበረ
ሲያያቸው ተደፍተው ሰገዱለት እነዚህ ከርእሱ ተመሳጥረው ነው በማለት በ፲ በ፲ ኀያላን አስያዟቸው አሸንፈው ሰገዱለት አኹንም በ፲፭ በ፲፭ ኀያላን እስያዟቸው መቆም አቅቷቸው ተኝተው ወድቀው ሰገዱለት ጲላጦስ ይህን አይቶ ፈራ እውን የአይሁድ ንጉሥ ነኽን አለው አንተ ትቤ አንተ አልኽ አለው አይሁድ ግን ሰንበትን የሻረ ኦሪትን ያቃለሰ ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ ያደረገ ለቄሳር ግብር የከለከለ ዐሳዊ ነው እንጅ ንጉሥ አይደለም ኣሉ ዝም አለ ይህን ያኽል ሲያሳጡኽ አትመልስም ልገድልኽም ላድንኽም
ሥልጣን አለኝ አለው "ወይቤሎ ኢኮንከ ብዉሐ ሊተ ወኢምንተኒ ሶበ
ኢተውህበ ለከ እምሰማይ" እን (ዮሐ፲፱፥፲፩) ይህን ተናግሮ ዝም አለ ይህን በተናገርንበት እስቲ ንገረኝ አለው መንግሥቴስ በዚህ ምድር ብትኾን ኑሮ ለአንተ ተላልፌ ባልተሰጠኹ ነበረ አዳምን ከልጅ ልጆቹ ጋራ ወደ ገነት ልመልሰው ከሰማይ ወርጄ ከድንግል ማርያም ተወልጄ በዚህ ምድር ወንጌልን እያስተማርኩ ሳለኹ አይሁድ ይዘው ለአንተ አቅርበውኛል እንጅ ብሎ ኹለን ነገረው ይህን ሰው በደል አላገኘኹበትም ብሎ ልልቀቀው አላቸው ከገሊላ ጀምሮ እስከዚህ ድረስ ሲያውክ የነበረ ነው አሉ ገሊላ ሲሉ ሰምቶ ወደ ገሊላው ገዥ ወደ ሄሮድስ ላከው ሄሮድስም ዝናውን እየሰማ ሊያየው ይወድ ነበረና ሲያየው ደስ አለው፡፡ ነገር ግን ቢጠይቀው የማይመልስለት ኾነ ይህስ ቢቻል ኹለት ሞት ይገባዋል ብሎ አክፋፍቶ አስገርፎ ቀይ ግምጃ አልብሶ ሰደደው ጲላጦስ ግን ብዙ እንዳስገረፈው ዐውቆ አዘነና ፫ ጊዜ አመጣችኹት በደሉ ምንድን ነው አላቸው ገርፌ ልልቀቀው በርባንን ልስቀለው አላቸው አይሁድ ግን ሕዝቡን አስተባብረው ስቀለው ስቀለው እያሉ ጮኹ ያን ጊዜ ከሚስቱ ከአብሮቅላ የማሰጠንቀቂያ ደብዳቤ ደረሰው ዲዳ የነበሩ ልጆቹ መካራና ደርታን አንደበታቸው ረቶ የኾነውን ነግረዋት ነበረና ይህን አይቶ ሊፈታው ፈለገ "እመ አሕየውኮ ለዝንቱ ኢኮንከ ዐርኮ ለቄሳር" እን (ዮሐ፤ሀና/፪) ይህን ብታድን የቄሳር ወዳጅ አይደለኽም አሉት ስለዚህ ውሃ አስመጥቶ "ንጹሕ አነ እምደመ ለዝ ብእሲ ጻድቅ" እን (ማቴ፳፯፥፳፬) እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ ብሎ እጁን ታጠበ እነሱ ግን ደሙ በእኛና በልጅ ልጆቻችን ይኹን ብለው ተቀብለው ፷፻፮፻፷፮ (6666) ጊዜ ገርፈውታል ዐጥንቱ እንደ በረዶ ነጭ ኾነ የሾኽ አክሊልጎ ንጉነው በራሰ ደፉበት ራሱንም በዘንግ ደበደቡት መስቀሉንም ከ፫ቱ ዕፀ አውልዕ ዕፀ ዘይት ዕፀ ወይን ከ፬ቱ ዕፀ በለስ ቁመቱ ፯ ክንድ ከስንዝር ወርዱ ፫ ክንድ ከስንገር አድርገው ሠሩ ከሊቶስጥራ አሸክመው ወደ ቀራንዮ ከወሰዱት በኋላ በ፮ ሰዓት ሰቀሉት በግራው ዳክርስን በቀኙ
ጥጦስን ዐብረው ሰቀሉ፡፡
በዚህ ጊዜ ፯ ተአምራት ተደርገዋል
~ፀሐይ ጨለመ
~ጨረቃ ደም ኾነ
~ከዋክብት ረገፉ
~መቃብራት ተከፈቱ
~ሙታን ተነሱ
~አእባን ተፈቱ
~መንጦላዕተ ቤተ መቅደስ ተተረተረ ✍🏽በዚህ ኹኔታ ስፍር ቍጥር የሌለውን መከራ ተቀበለ በጥቅሉ ፲፫ቱ ሕማማተ መስቀል ተብለው ይጠራሉ ፯ቱን አጽራሐ መስቀል ተናግሮ በ፱ ሰዓት ቅድስት
ነፍሱን ከሥጋው ለየ በሲኦል የነበሩ ነፍሳትን አውጥቶ ቀኝ እጁን የተወጋ ጎኑን አሳያቸው እንደ ጥምቀት ኹኗቸው ገነት አግብቷቸዋል ከዚህ በኋላ በ፲፩ ስዓት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከጲላጦስ አስፈቅደው ከመስቀል አውርደው በንጹሕ በፍታ ገንዘው ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር እያሉ ቀብረውታል፡:
✝.ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።✝
ምንጭ፦ባሕረ ሐሳብ እና የኢትዮጵያ ታሪክ👇👇👇
@Ethiopia7980
@Ethiopia7980
@Ethiopia7980
BY እንቆጳ ዝዮን
Warning: Undefined variable $i in /var/www/group-telegram/post.php on line 260
Share with your friend now:
group-telegram.com/enqopazion777/1149