Telegram Group Search
🔈 #የጤናባለሙያዎችድምጽ

“ ማንም መልስ የሰጠን የለም። ችግሮቹም ከቀን ወደ ቀን እየተባበሱ ነው ” - የኢትዮጵያ ህክምና ማኀበር

የኢትዮጵያ ህክምና ማኀበር፣ “ በተለያዩ በሽታዎች ተይዘው ከፍተኛ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሀኪሞቻችን ተገቢውን ህክምና በፍጥነት ባለማግኘታቸው የህይወት ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ ” ሲል ወቅሷል።

ማኀበሩ ይህን ያለው፣ ከየካቲት 14 እስከ 15 ቀን 2017 ዓ/ም ስለሚያካሂደው 61ኛው ዓመታዊ የህክምና ጉባዔ በተመለከተ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው።

ጉባኤው፣ “ በኢትዮጵያ የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች ደህንነት አሁናዊ ሁኔታና አማራጭ መፍትሄዎች ” በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ አመልክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ስለሀኪሞች ህክምና የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ምን እንደሚመስል፣ ለኢትዮጵያ ሀኪሞች ምን መደረግ እንዳለበት ማኀበሩን ማብራሪያ ጠይቋል።

የማኀበሩ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ትዕግስት፣ በሰጡት ምላሽ “ በብዛት በኢንሹራስ ከቨር የሚደረግበት ሁኔታ አለ በጥናት የተደገፈ መረጃ ባይኖርም የሌሎች አገራትን ተሞክሮ በተመለከተ ” ብለዋል።

አክለው፣ “ የኛ አገርን በተመለከተ የኢንሹራንስ ከቨርም ስለማይደረግ ጤና ባለሙያዎች እንደማናቸውም ማኀበረሰብ በትንሽ በሀገር ታክመው የማይዳኑ በጣም የተወሳሰቡ ህመሞች ሲታመሙ እናያለን ” ነው ያሉት።

ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የማኀበሩ የቦርድ አባል ዶ/ር በሀሩ በዛብህ ፣ “ ችግሩ የቆዬ ነው። ማንም መልስ የሰጠን የለም። ችግሮቹም ከቀን ወደ ቀን እየተባበሱ ነው ” ሲሉ መልሰዋል።

ዶ/ር በሀሩ በዛብህ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል በዝርዝር ምን አሉ ?

“ ለሀኪሞች የኢንሹራንስ ከለላ መኖር አለበት። ራሳችን ያመጣነው በሽታ እንኳ ሳይሆን ስናክም ብዙ በሽታዎችን ነው የምናገኘው። ብዙ የጤና ባለሙያዎች በህክምና ሂደት ላይ ግራጁዋሊ በሚያገኙት በሽታ ሞተዋል።

ክብደት ያለውን ታካሚ እያነሳ የአካል ጉዳተኛ የሚሆንም አለ። ከተላላፊ በሽታዎች ጋር እንሰራለን። ስለዚህ ጤና ባለሙያዎች በእነዚህ በሽታዎች ይጎዳሉ።

ብዙዎች እንደዚህ አይነት ችግሮች መኖራቸውን ሲያውቁ ሙያቸውን ሁሉ የቀየሩ አሉ። ወጣቶች ትምርታቸውን አቋርጠው ወደ ሌላ ሙያ የሚሄዱበት ሁኔም አለ።

ለሀኪሞች ተላላፊ የሆነ በሽታ መከላከያ ሂደቶች የሉም። መካላከያ ኖሮም በሽታ የሚተላለፍበት ሁኔታ አለ። ግን ለማገገም የሚሰጥ ህክሞና የለም። 

አንዳንድ መከላከያዎች ውድ ናቸው። ያን ለማቅረብም የኢኮኖሚው ሁኔታ ያን ያክል አይፈቅድም”
ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ ሀኪሞች ብዙ ጭናዎችን ተቋቁመው እየሰሩ የሰሩትን የዲዩቲ ክፍያ እንዲፈጸምላቸው ሲጠይቁ ለእስር ሲዳረጉ መስተዋሉን የገለጸው ማኀበሩ፣ በጉባዔው ወቅት ውይይት እንደሚደረግበት ጠቁሟል።

(የማኀበሩ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ወቅታዊ የሀገሪቱ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ጠንካራ አመራር እና ውጤታማ የሰብአዊ መብቶች ሥራ የሚጠይቅ መሆኑን እያስታወስኩ መልካም የሥራ ዘመን እመኛለሁ " - ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ አቶ ብርሃኑ አዴሎን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር አድርጎ ሾሟል።

ኢሰመኮ ፥ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተሾሙት አቶ ብርሃኑ አዴሎ ከዚህ ቀደም በተለያዩ መንግሥታዊ ኃላፊነቶች ያገለገሉ ?መሆኑን ከእነዚህም መካከል ፦
- የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር፣
- የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትር
- የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እንደነበሩ አስታውሷል።

ተቋሙን በተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነርነት ሲመሩ የነበሩት ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ፥ ወቅታዊ የሀገሪቱ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ጠንካራ አመራር እና ውጤታማ የሰብአዊ መብቶች ሥራ የሚጠይቅ መሆኑን አስታውሳዋል።

የኢሰመኮን ኮሚሽነሮች እና ባልደረባዎች በመወከል ለዋና ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ አዴሎ ከወዲሁ “ መልካም የሥራ ዘመን እመኝላቸዋለሁ ” ብለዋል።

@tikvahethiopia
በግብይት ወቅት ገንዘብ በአግባቡ ወደ ቴሌብር አካውንትዎ መግባቱን ለማረጋገጥ ቀላል ዘዴ እናስተዋውቅዎ!

ቴሌብር ሱፐርአፕዎ ላይ ‘’መለያ’’ ወደሚለው አማራጭ ይግቡ፣ ‘’ክፍያ ያረጋግጡ’’ የሚለውን በመምረጥና የግብይት ኪው አር ኮድ ስካን በማድረግ ወይም የግብይት ቁጥሩን በማስገባት የክፍያውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

ቴሌብር ሱፐርአፕ ➡️ መለያ (Account) ➡️ ክፍያ ያረጋግጡ (Verify Payment) ➡️ የከፋዩን ኪው አር ኮድ ስካን ማድረግ ወይም የግብይት ቁጥሩን (Transaction Number) በማስገባት ማረጋገጥ

🔗 ቴሌብር ሱፐርአፕን https://onelink.to/uecbbr ይጫኑ!


ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
ሕብር ሙዳይ የቁጠባ ሒሳብ

ሙዳይ ተቀማጭ ሒሳብ በአነስተኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች የሚከፍቱት የቁጠባ ሒሳብ ሲሆን፤ አገልግሎቱ የቁጠባ ባህልን ለማዳበር አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቆጣቢዎችን ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ በመሆኑ ደንበኞችን ለማበረታታት በነፃ የገንዘብ ቁጠባ ሣጥኖች የሚሰጥበት የቁጠባ ሒሳብ ነው፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

📞 ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ https://www.group-telegram.com/HibretBanket
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡

#HibirMudai #savings #financialwellness
TIKVAH-ETHIOPIA
#FreeNaima " ገንዘቡን ካላገኘን በቀር እንዳንደውልላቸው አስጠንቅቀውናል። በጣም ተጨንቀናል " - ቤተሰብ በሊቢያ ታጣቂዎች በርካታ ስደተኞችን አግተው የማሰቃየት ድርጊት እየፈጸሙባቸው ይገኛል። ከእነዚህ ታጋቾች መካከል የሀገራችን ልጅ ነሒማ ጀማል አንዷ ናት። ነሒማ ከኦሮሚያ ክልል፤ ሻሸመኔ በመሰደድ ነው ወደ ሊቢያ ያቀናችው። ' ሬፊዩጂስ ኢን ሊቢያ ' የተሰኘው ተቋም በኤክስ ገፁ እንዳስታወቀው…
" ከዚህ በኋላ ምን እንደሚፈጠር አላውቅም፤ ስልክ መደወልም ሁሉም ነገር ያስፈራል " - ነሒማ ጀማል

ከጥቂት ሳምንታት በፊት በሊቢያ " ለባርነት ጨረታ ቀርባ " የነበረችው ኢትዮጵያዊቷ ነሒማ ጀማል ለአጋቾቿ 700 ሺህ ብር ተከፍሎ ነጻ መውጣቷን ተናግራለች።

በፎቶዎች እና በቪዲዮዎች ላይ አፏ በጨርቅ ተለጉሞ ስቃይ ሲደርስባት ትታይ የነበረችው ነሒማ በቤተሰቧ አማካይነት ገንዘብ ከኢትዮጵያ ተሰባስቦ ከተላከ በኋላ ከሁለት ቀናት በፊት አጋቾቿ ወደ ከተማ አምጥተው እንደለቀቋቸው ለቢቢሲ ተናግራለች።

ታግታ ከነበረችበት ስፍራ እሷን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ቢኖሩም የተለቀቁት ገንዘብ የተከፈለላቸው " ውስን ሰዎች ነበሩ " ብላለች።

ነሒማ በአሁኑ ወቅት በሊቢያ የምትገኝ ሲሆን " ድካም እና ህመም ላይ " እንደሆነች ገልጻለች።

" ከዚህ በኋላ ምን እንደሚፈጠር አላውቅም፤ ስልክ መደወልም ሁሉም ነገር ያስፈራል " ስትል ጭንቀት ላይ እንደሆነች እና ማውራት እንደሚከብዳት ተናግራለች።

መረጃው የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
#Dollar

💵 " ዶላርን በሌላ የመገበያያ ገንዘብ መተካት አይታሰብም፤ ይህን ባደረጉ አካላት ላይ 100% ታሪፍ እጥላለሁ '' -  ትራምፕ

➡️ "አሜሪካ ሌሎች ሀገራት ዶላርን ብቻ እንዲጠቀሙ ለማስገደድ መሞከሯ ያለፈበት እሳቤ ነው '' - ሩሲያ

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የBRICS+ አባል ሀገራት የአሜሪካን ዶላር ትተዉ በሌላ ገንዘብ ለመገበያየት ከወሰኑ ለአሜሪካ ገበያ በሚያቀርቡት ሸቀጦቻቸዉ ላይ የ100% የቀረጥ ጭማሪ እንደሚያደርጉ ዛቱ።

ትራምፕ ባሰራጩት ማስጠንቀቂያ የBRICS+ አባል ሐገራት ከዶላር ለማፈንገጥ ማሰባቸዉ " ማብቃት  አለበት " ብለዋል።

" ዶላርን በሌላ የመገበያያ ገንዘብ መተካት አይታሰብም " ሲሉ ገልጻዋል።

የBRICS+ አባል መንግሥታትን ለአሜሪካ " የጠላትነት አዝማሚያ " የሚታይባቸዉ በማለት ወርፈዋል።

ትራም እነዚህ ሀገራት " ግዙፍ " ያሉትን የአሜሪካን ዶላር ለመተካት አዲስ ገንዘብ ካሳተሙ ወይም በሌላ ገንዘብ ለመጠቀም ከወሰኑ ከአሜሪካ ገበያ መሰናበት አለባቸዉ ብለዋል።

ትራምፕ እንደሚሉት የBRICS+ ሀገራት አዲስ ዶላር ትተው በሌላ ገንዘብ ለመገበያየት ከወሰኑ አስተዳደራቸው ወደ አሜሪካ በሚገቡ የየሀገራቱ ሸቀጦች ላይ የ100% የቀረጥ ጭማሪ ያደርጋል።

ሩሲያ ለዚሁ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዛቻ ምላሽ ሰጥታለች።

" አሜሪካ ሌሎች ሀገራት ዶላርን ብቻ እንዲጠቀሙ ለማስገደድ መሞከሯ ያለፈበት እሳቤ ነው " ብላለች።

የBRICS+ ቡድን ባሁኑ ወቅት
#ኢትዮጵያን ጨምሮ 10 አባል መንግስታትን ያስተናብራል።

በኢንዲስትሪ የበለፀጉትን 6 ምዕራባዉያን ሀገራትና ጃፓንን የሚያስተናብረዉ ቡድን 7   የሚያደርሰዉን ተፅዕኖ ለመቋቋም ያለመ ነዉ።

ሩሲያና ቻይናን የመሳሰሉ የBRICS ጠንካራ አባላትና መሥራቾች የአሜሪካ ዶላር በዓለም ገበያ ላይ የሚያደርሰዉን ጫና አጥብቀዉ ይተቻሉ።

ማሕበራቸዉ አማራጭ መገበያያ እንደሚያስፈልገዉም ያሳስባሉ።

የአሜሪካዉ ፕሬዝደንት ግን ዶላርን መተካት " አስደናቂ " ከሚሉት ከአሜሪካ ምጣኔ ሐብት መሰናበት ነዉ።

መረጃው የዶቼቨለና ቴሌግራፍ ነው።

@tikvahethiopia
🔈#የአርሶአደሮችድምጽ

🔴 “ አምና 3,600 ብር ስንገዛው የነበረውን ማዳበሪያ ዘንድሮ በ8,400 ብር ለመዛት ተገደናል ” - አርሶ አደሮች

➡️ “ ከኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ የማዳበሪያ ዋጋ ጨምሯል ” - የሲዳማ ክልል ግብርና ቢሮ

የሲዳማ ክልል አርሶ አደሮች ማዳበሪያና ምርጥ ዘር በቆሎ የቀረበላቸው በውድ ዋጋ በመሆኑ ለመግዛት መቸገራቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ በዝርዝር ምን አሉ ?

“ አምና የአንድ ኩንታል ማዳበሪያ (ዳፕ) ዋጋ 3,600 ብር ነበር። ዘንድሮ ግን 8,400 ገብቷል። አምና 1,800 ብር የነበረው ምርጥ ዘር በቆሎ የአንድ ፕሎት ዋጋ ዘንድሮ 4,600 ብር ገብቷል። ይህ ለበቆሎ ብቻ የሚከፈል ነው።

በቆሎ ስንወስድ ለብልጽግና ቤት ግንባታ 1,500 ብር፣ ለማኀተም 1,000 ብር፣ ለግብር እስከ 3,000 ብር፣ ለብልጽግና ፓርቲ መዋጮ 300፣ ለቀይ መስቀል 200 ብር ወረዳው በግዴታ የሚያስከፍለን ወጪዎችም አሉ።

በአጠቃላይ ለአንድ ፕሎት ምርጥ ዘር በቆሎ አንድ አርሶ አደር ከ10,000 ሺሕ ብር በላይ እንዲያወጣ ተገዷል።

ስለዚህ የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ በተለይ በቆሎን በስፋት በማምረት የሚትታወቀው የሻመና አርሶ አደሮች ዘንድሮ በቆሎ ማምረት ይቸገራሉ"
ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ አርሶ አደሮች ላቀረቡት ቅሬታ ምላሽ እንዲድሰጥ የሲዳማ ክልል ግብርና ቢሮን ጠይቋል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ ምን መለሱ ?

“ ከኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ የማዳበሪያ ዋጋ ጨምሯል። እኛ የጨመርነው ነገር የለም የትራንስፓርት ብቻ ነው። ስለዚህ ያለ ዋጋ ነው፤ ያሳወቅነው ዋጋ።

ሌሎች ጋ አሁን ላይ ስርጭት ስላልጀመረ እንጅ ተመሳሳይ ነው። እነርሱ ቀድመው ስለሚገቡ በሚል እንጅ ፎርማሊ አሳውቀናል እኛ በደብዳቤ። አገራዊ ነው።

አምና ላይ ወደ 4,000 ገደማ ነበር። አሁን ላይ ከ7,500 - 8,000 ብር ይሄዳል እስከ ትራንስፓርት ታሳቢ ተድርጎ
ማለት ነው።

የበቆሎም አዎ በመሳሳይ ነው ይጨምራል። ፕሮዳክሽን ኮስት በየጊዜው ይጨምራል። ባለበት አይሆንም

ስለዚህ ለምሳሌ የአንድ ትራክተር ዋጋ፣ የነዳጅ ዋጋ ታሳቢ አድርጎ በየአመቱ ይጨምራል። መጨመር ያለ ነው። ከሌላ ጋ ካልሆነ በስተቀር ከኛ ጋ ኦፊሻሊ ታይቶ ዋጋ እንደ ሀገር ወጥቶለት በዚያ የምናቀርበው ስለሆነ ችግር ያለው አይደለም።

ለምሳሌ በትራክተር ለሚያርስ ነዳጅ፣ የጉልበት.. ካችአምናና አምና የነበረ ተመሳሳይ አይደለም። ያምና እና የዚህ ዓመት ተመሳሳይ አይሆንም። በዚያ ምክንያት የተወሰኑ መጨመሮች አሉ።

ማዳበሪያ ከአገር ውጪ የሚመጣ ስለሆነ እኛ መተመን አልችልም። መንግስት ሳብሲድ አድርጓል። እንደመንግስት እንዲያውም ከድጎማ በፊት 12 ሺህ ብር ነው የሚሆነው የአንድ ኩንታል ማዳበሪያ ዋጋ። 

በድጎማው ቀንሶ ነው ወደዛም የወረደው። 4,000 ከአንድ ኩንታል ድጎማ ነው ”
ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Afar

🚨“ የሟቾች ቁጥር 8 ነው። ቁስለኞች ከ10 በላይ ናቸው። ቁስለኞች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ” - ነዋሪዎች

➡️ “ ጥቃቱ የድሮን ጥቃት ነው፡፡ የሟቾች ”ቁጥር እስካሁን ባለኝ መረጃ  ስምንት ነው" - ኤሊዳዓር ወረዳ

በአፋር ክልል ኤሊዳዓር ወረዳ ሲያሩ ቀበሌ ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት በአርሶ አደሮች፣ ሴቶች፣ ህፃናት  ሞትና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎችና ወረዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ በሰጡን ቃል፣“ 8 ሰዎች ተገድለዋል። ከ10 በላይ ደግሞ ቆስለው ዱብቲ ሆስፒታል ገብተዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው ከወደ ጅቡቲ አቅጣጫ በመጣ ድሮን ነው ” ብለዋል።

መረጃ አቀባይ ነዋሪዎቹ በዝርዝር ምን አሉ ?

“ ትላንት ሌሊት አካባቢ መጀመሪያ ሦስት ሰዎች ተገደሉ። ሦስቱንም ዱሮን ነው ያጠቃቸው። ከዚያ ዛሬ ጠዋት ሟቾቹን ሊቀብሩ የነበሩ ሰዎችን ዱሮን እንደገና መጥቶ ነው ያጠቃቸው።

መጀመሪያ ሦስት ወንዶች የሞቱ ሲሆን፣ እንደገና መጥቶ ሦስት ጊዜ ነው ጥቃት የተፈጸመው። ሦስቱ ከተገደሉ በኋላ ድሮን መጥቶ ሴቶችና ህጻናትን አታክ ተደረጉ።

አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ስምንት ነው። ቁስለኞች ደግሞ ከ10 በላይ ናቸው። ቁስለኞች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ዱብቲ ሆስፒታል ገብተው ነው የሚገኙት።

ጥቃት የተፈጸመበት አካባቢ ድንበር ነው ለጅቡቲ። ድሮኑ በየት አቅጣጫ እንደሚመጣ ይታውቃል። ይታያል ማለት ነው ከጅቡቲ እንደመጣ ይታወቃል።

‘ ጅቡቲን የሚቃወሙ ታጣቂ ኃይሎች አሉ ’ ብለው ነው ጥቃቱን የሚፈጽሙት። ከቁስለኞቹ ውስጥ የአስር አመት ህጻናት አሉ። ሴቶች አሉ። ዱብቲ ሆስፒታል እግሯና እጇ የተቆረጠች ልጅ አለች ”
ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ “ የድሮን ጥቃት ደርሷል ” መባሉን እንዲያረጋግጡልን የጠየቃቸው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኤሊዳዓር ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን አካል፣ “ አዎ። ጥቃቱ የድሮን ጥቃት ነው፡፡ የሟቾች ቁጥር እስካሁን ባለኝ መረጃ ስምንት ነው ” ሲሉ ገልጸዋል።

“ ጥቃት የደረሰበት ሲያሩ ቀበሌ የጅቡቲ ድምበር ” መሆኑን ጠቅሰው ለተጨማሪ መረጃ በቦታው ያሉ የጸጥታ አካላት ምላሽ እየተጠበቀ መሆኑን አስረድተዋል።

“ በዚያኛው በኩል በስንት ኪሎ ሜትር እንደሆነ፣ በዚህኛው በኩል በስንት ኪሎ ሜትር እንደሆነ የጸጥታ አካላት ምላሽ እየተጠበቀ ነው ” ሲሉ ጠቁመዋል።

ከሟቾች በተጨማሪ በሴቶችና ሕጻናት ከባድ ጉዳት እንደደረሰ ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል ስለዚህስ ጉዳይ ምን ይላሉ ? ምን ያክል ሰዎች ናቸው የተጎዱት? ስንል ላቀረብነው ተጨማሪ ጥያቄም የወረዳው አካል ምላሽ ሰጥተዋል።

በምላሻቸውም፣ “ አዎ፡፡ እኛ በቦታው ስላልቆምን የጸጥታ አካላት ምን ያህል ሰው እንደተጎዳ፤ ቁስለኛው ፣ምን ያህል እንደሆነ አጣርተው እስከሚያመጡ እየተጠበቀ” ነው ብለዋል።

ተጨማሪ ማብራሪያ የጠየቃቸው አንድ የክልሉ ፓሊስ አባል፣ “ ከመረጃ ውጪ ነኝ ” ሲሉ የስልክ ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ኔትዎርክ የሌለበት ቦታ ነው ያለሁት። በእርግጥ መረጃ የለኝም። እያሉ ግን ሰምቻለሁ ” ከማለት ውጪ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

(በጉዳዩን ተጨማሪ መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል)

 #TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በመቐለ ከተማ በከንቲባ ስም ማንኛውም ተግባር እንዳይፈፅም አስጠነቀቁ።

አቶ ጌታቸው በእፅንኦት ያስጠነቀቋቸው ባለፈው ጥቅምት 2017 ዓ.ም በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ህወሓት እጩ አቅራቢነት ከንቲባ በመሆን የተሾሙትን ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) ነው።

ፕሬዜዳንቱ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ፅፈውት  ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች ይፋ በሆነው የማስጠንቀቅያ ደብዳቤ ፤ በከተማዋ የሚገኙ የመንግስት መዋቅሮች በጊዚያዊ አስተዳደሩ ቅቡልነት ባጡ ከንቲባ ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) በተፃፈ ደብዳቤ ማንኛውም ስራ መፈፀም የህግ ተጠያቂነት አንደሚያስከትልባቸው ያትታል።

ዶክተሩ ህገ-ወጥ ተግባራቸው እንዲያቆሙ የሚያሳስበው እና የሚያስጠነቅቀው ደብዳቤው ጊዚያዊ አስተዳደሩ የሚፃረር አቋም በመያዝ ከተማዋ መምራት አግባብነት የለውም ይላል። 

ስለሆነም በመቐለ ከተማ የሚገኙ የመንግስት መዋቅሮች በጊዚያዊ አስተዳደሩ ቅቡልነት በሌላቸው ከንቲባ የሚሰጣቸው ማንኛውም ዓይነት ትእዛዝ እንዳይቀበሉ የፕሬዜዳንቱ ደብዳቤ አስጠንቅቋል።

ህወሓት ለሁለት በመሰንጠቁ ምክንያት የመቐለ ከተማ ላለፉት 60 ቀናት ቢሮ ገብቶ የሚደራ ከንቲባ የላትም።

ህዳር 23/2017 ዓ.ም በጊዚያዊ አስተዳደሩ ደብዳቤ የተሾሙ ብርሃነ ገ/የሱስ አንድ ቀን ብቻ በአስተዳደሩ ግቢ ታይተው ለሁለተኛ ጊዙ አልተመለሱም።

በደብረፅዮኑ ህወሓት የተሾሙ ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) ከህዳር 23 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ቢሮ አልገቡም።

የመቐለ ከንቲባ ቢሮ አሁንም ታሽጎ በፓሊሶች ይጠበቃል፤ የከተማዋ ነዋሪ ደግሞ ከከንቲባ ማግኘት የሚገባውን አገልግሎት አጥቶ አቤቱታውን ለማን ማቅረብ እንዳለበት ግራ ገብቶት ይገኛል። 

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
2025/02/01 00:26:27

❌Photos not found?❌Click here to update cache.


Back to Top
HTML Embed Code: