. . . 'ጠናናነቱን' የሚያሳብቁ አይኖቹን እያየው
.....የኔ ፍቅር ታፈቅረኛለህ? እንዲያዘንብልኝ አንዴ የፀሐይዋን መጥለቅ ደግሞ ዘወር ብዬ ካፊያውን እየናፈቅኩ!
........እሱ ዝም... ጭጭ።
ቆይ!! ቃል ማውጣት ስራ ይሆናል? ለእሱማ ጥንብ የሆነበትን ሸክም የሚያራግፍበት ቀሊል የሚጠብቅ ነው የሚመስለው. ... በጣም ይከብደዋል።
....... እ? <የኔ ፍቅር ምን ያህል ታፈቅረኛለህ?> ለወጥ ሳደርግ ይመልስልኝ ይመስል...... የአጠያየቄ አይነት ሁልቆ መሳፍርት የለሁም። ...... ጥያቄ ጎጆዋን እንደቀለሰችብኝ መልስ ደሞ ደጅ ታስጠናኛለች።
.... ማሬ! እስኪ << አፈቅርሻለው >>በለኝ አልኩት እየተልመጠመጥኩ..... ምን አለ አፈንድቶት ቢገላግለኝ የጥያቄ መዝገበ ቃላቴ እኮ ታዘበኝ።
.....ለሽርደዳ ለሽርደዳማ ማንም አይችለውም። ..... ከንፋስ የፈጠነ፣ ከእስትንፋስ የቀረበ ነው። ............ 'በእግረ ደረቅነቴ' ላይ ሲያሽሞጥጥ የሚቀድመው የለም። ምን እሱ ብቻ መዘባበቻ ሲያደርገኝ የአለም ቃላት፣ ዓረፍተነገር፣ አንቀፅ ቀለበት ያሰሩለት ነው የሚመስሉት!!
... ''ለምን አይመልስልኝም?" ቃላት ማውጣት ይከብዳል? ያውም የሰለለ ድምፁን ከእሬት ስልቱ ጋር አዋህዶት ሊያቀርብልኝ
ግን! እኮ ያንን ቃል እወደዋለው እንደተፈታች እንቦሳ ያስፈነድቀኛል።
. . . ፈለግ የወረረውን ጣቱን ፈርሱ ላይ እያንሸራሸረ፣ አልፎ አልፎ እጆቹን ጉሹ በሸሸው አናቱ ላይ ችፍ ያለሁን ላቦቱን እየጠረገ፣ ልማደኛ ጥፍሩን ጭጉኝ በወረሰው ጢሙ ወጋ ወጋ እያደረገ፣ ....እንደ ማስቲካ አላምጦ ጣዕሙ ሲያልቅ ለሚተፋው ቃል ለምንስ እጨነቃለው?
. . . 'ስጋ' የሆነውን 'ቃል' እንኳን የገዛ ወገኖቹ አልተቀበሉትም። "ሰምና ወርቅ" ሲያወጡለት ስንክልክል ብለዋል። ...'የፍጥረትን ሩጫ' የሚያቃጥለው 'ዓረፍተ ነገር' በየጉራንጉሩ እንደ ጭቃ ይለጣጠፉበታል። <አንደበት ዓመፀኛ አለም ነው> ያሻው ፍቅርን ይገድልበታል። የገደለውን ይቀብርበታል። ታዲያ! ለዚ ቃል ነው ደጅ የሚያስጠናኝ? 'የህልም እንጀራ' አሳቅፎ የሚያንከራትተኝ!
.....'ያላበጀውን ፍቅር' በፊደሉ ቢራቀቅበት ምን አለ? ለእሱ ''ማርጃ'' ለእኔ ''የምስራች'' የሆነውን ቢነግረኝ ምን ቸግሮት?
.....<ሀሞቴ ፈሷል> ግን! የመጨረሻ ቃሌን አቀበልኩት
<<የእኔ ውድ በጣም አፈቅርሃለው!>> ጥያቄ አልነበረም። ምላሽም አይሻም!
. . . 'የበጨጨ' አልፎ አልፎ ጥጋ ጥጉን እንደ 'ዳመና' ጥቁር ያጠላበትን ጥርሱን ብልጭ አድርጎ እንደወትሮው በመሰሪ አይኖቹ 'ሴሰኛ' አስተያየቱን መርቆልኝ ..... የአምስት ወር ህፃን ይመስል እየዳኸ በሚንፏቀቁ ቃላቶች
<<አ..ላ...ፈ...ቅ...ርሽም>> አለኝ! ቦምቡን አፈነዳው። ስብርባሪው አልጎዳኝም። እንደሁም በተቃራኒው. . .
.... "ነፍሴ ሃሴት አደረገች". . . "ጮቤ ረገጥኩ". . . "ቦረቅኩ"!
<ውሃ እንደተጠማ ደርቆ መሰነጣጠቅ የጀመረው ተስፋዬ ረሰረሰልኝ> ... ቃሉ ለኔ ኃይል አለው። "ሳይፈቀሩ ማፍቀር ድሌ ነው"። "ምላሽ የሌለው መውደድ የሰባ ፍሪዳ ጮማዬ ነው" ።
✍ አርያም ተስፋዬ (2013)

ትልቅነቴን ያየሁበትን ቀን መቼም አልረሳውም።ከኋላ የሚከተለኝ ጥላ ከቁመቴ በላይ ግዙፍ ነው። በብርሃን ውስጥ ራሴን የፈለግኩበትን ዘመን ረገምኩት። ለካስ በባትሪ የሚፈለገው ነው ዕንቁ . . . የቀን የቀኑማ ተመሳስሎ የተሰደረ ብረት ብቻ!
'ፅልማሞት' እወዳለሁ። 'ፅልም ያኮስ' እቅፍ ውስጥ ድብቅ ስል ነገር አለሜን እረሳለው። ሊጠፋ ባቆበቆበው ብርሃን የጠቆረው ጥላዬ ከእኔነቴ ገዝፎ ሳየው አሸናፊነት ይሰማኛል።
''መማፀኛ ከተማዬ'' ነው። ነፍስ አጥፍቶ ከደም ተበቃይ የሚሸሽ ሰውን ይመስል ውሽቅ የምልበት 'ቤቴ' . . . በብርሃን ቢገለጥ የሚሰነፍጠውን ሕይወቴን ሸሽቼ የምሸሸግበት ከተማ. . . በድንግዝግዝ ስራመድ ሁሉም መንገድ መዳረሻ፣ ከገንቦ ጠብታ የማልቆጠረውን የኢያሪኮን ሞገስ የሚሰጥ፣ ኃጢአቴ ህያው የማይሆንበት ለኔ እንደ እናት ቤት የሚሞቅ ድሎቴ ነው።
አዎ! 'ጨለማ' እወዳለሁ! 'ሆድና ጀርባ' የሆነውን ማንነቴን ያስታርቅልኛል። 'እየተልመዘመዘ' የሚያስቸግረኝን እኔነቴን 'አደብ' ያስገዛልኛል።
'ፅልመትን' በመገኘቴ ስደምረው <ሽንተ መልካም> የሆንኩ ያህል እከበባለሁ። 'ቅርሽም' ያለው ነገዬ ይጠገናል። 'እየበተበተ' ያለቀው ትላንትናዬ ይፈካል።
'ከከቸችኩ' ሰንብቻለው! ድኩሙ ጉልበቴ ለእርምጃ አሻፈረኝ ብሎኛል። እንደ አረረ ወጥ 'የጎረናው' ስሜ ከሽታው በላይ ጣዕሙ መንችኮብኛል። እከሊት 'ደሰቃም' ናት የሚል ስያሜ ከተሰጠኝ ውሎ አድሯል። ይታወቀኛል። አውቀዋለሁ. . . የኔ ማንነት እሱ ነው <ሀገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው!>
ግን እኮ .... እኔ'ኮ <<ፅላቱ>> ነኝ ለ. . . 'ፅልመት'። ለጥልም ያ'ኮስ ጥሞናው፣ የብርሃንነቴ ፅህፈት ማንፀባረቂያው ነኝ። ጨለማ ውስጥ ለሚያየኝ ኔፍሊም!
ለዛ'ም ነው ጨለማን የምወደው. . . ድቅድቅ ውስጥ የምሸሸገው! . . . ቀን ያጨመተረውን፣ ጭምግግ፣ ጥፍግግ አድርጎ ያሰረውን እኔ'ነቴን የማታ ፅህፈት ስለሚያነፃኝ! ለዛ'ም ነው ጥልመት የምናፍቀው ለዚህም ነው በእሱ የምኖረው!
'አርነቴ' ነው! ያረጀ ያፈጀ ተረታ ተረቶችን የምረሳበት በውስጡ ራ'ሴን ሳየሁ ምሉዕነቴ የሚያሳብቅብኝ!

የራስ ጠጉሯ ከወደ ወገቧ ተዘናፍሏል...... የለበሰችው ነጭ የሀር ቀሚስ ያለማቋረጥ ከማሕፀኗ በሚወጣው ነስር ወደ ሀምራዊነት ተቀይሯል......በማልቀስ ብዛት የቀሉት አይኖቿ ውበታቸው አልደበዘዘም
.........እንባዎቿ መንታ መንታ እየወለዱ የተከፈለ ሮማን ከሚመስሉት ጉንጮቿ አልፈው ቀይ የሐር ፈትል የመሰለው ከናፍሮቿ ላይ ቤታቸውን ቀልሰዋል. .....ደጋግማ በእንባዎች የረጠበውን ከናፍሯን በምላሷ ልታብስ አፏን ስትከፍት ታጥበው እንደ ተሸለቱ ሁሉም መንታ እንደ ወለዱ መካን እንደሌለባቸው መንጎች የሆኑት ጥርሶቿ ብቅ ይላሉ!
ታላቅ ወንድሟና ሶስት ጓደኞቹ ከደፈሯት በኋላ ከራሷ ተቀያይማ ቀርታለች! ወንድሟ? አዎ! ወንድሟ ደፍሯታል!በራሷ ላይ ቂም አርግዛ የአዳም ዘር የወሲብ ጥማት ማርኪያ ከሆነች ሰንበትበት ብላል።
እሷ
ሴት - አዳሪ .......በመዳራቷ ገበታ ያልቀረበ...ከሴሰኝነቷ ሌማት ያልቆረሰ.....
ከአመንዝራነቷ መአድ ተቋድሶ. .....በዝሙቷ አገልግል ያልጠገበ .....በግልሙትናዋ ጽዋ ተጎንጭቶ ያልረካ የለም።
አሁን አሁን ከተገባት ውጪ የራሷን በመፈለጓ ለማይረባ አእምሮ ተሰጥታ ራሷን ራሷ ላይ መፈለግ ከጀመረች ውላ አድራለች..... ሴት-ለሴት አዳሪ!
ከደቂቃዎች በፊት:
ከሀኪሟ የተሰጣትን የህክምና ውጤት በተደጋጋሚ የሚፈሳት ደም መንስኤ የማሕፀን ካንሰር እንደሆነ አረጋግጦላታል። የመጨረሻ ደረጃ ላይ ስለደረሰች የሞቷን ቀን እንድትጠባበቅ በሀዘኔታ የነገራት የሀኪም ድምፀት በጆሮዎቿ ላይ በተደጋጋሚ ይሰማታል።
ይዛው የወጣችሁን የእጅ ቦርሳ እንኳን በቅጡ ሳታስቀምጥ መሬት ላይ ወርውራ ከቁም ሳጥኗ ውስጥ የምትወደውን የሀር የሌሊት ቀሚስ አውጥታ ለበሰች. .... የመርገም ጨርቋ ፅድቅ ይወልድላት ይመስል ከሰፊው መታጠቢያ ገንዳ ውስጥ ተሰየመች።
የመታጠቢያ ገንዳው ውሃ ቀይ ሆኗል ወሲብ ወሲብ የሚሸተው መዓዛዋ ደም ደም ይላል የወይን ዘለላ የሚመስሉት ጡቶቿ እንደ ዘብ ወታደር ቆመዋል የዝሆን ጥርስ የሚመስለው አንገቷ በከፊል ዘመም ብሏል ለደቂቃዎች እንደ ተከፈተ የቧንቧ ውሃ ይፈስ የነበረው እንባዋ ደርቋል...
በሰመመን የሚሰሟት ድምፆች አሉ። ለሷ ባዕድ አልነበሩም። ታውቃቸዋለች!...ያውቋታል! .....ይተዋወቃሉ!!
ሴሰኛ ነሽ! ሸርሙጣ! ስጋዋን ቸርችራ አጥንቷን የቆረጠመች! ጋለሞታነቷ የሸተተ ፣ ዝሙቷ የሚጣራ ፣ መዳራቷ የሚሰቀጥጥ ፣ አመንዝራ ....መውገሪያ ድንጋዮች! የሰመመኗ ድምፆች ነበሩ።
የመጨረሻዋ ድንጋይ:
...........የመጀመሪያውን ድንጋይ የእናቷ ልጅ ወረወረባት... ሰይጣናዊ ፍቅር ይዞት! ከሰባት ትውልድ የሚለውን የአምላክ ህግጋት ናቀ የማይገባሁን ተመኘ ከዘማዊነት መኝታ በራሱ ገላ እህቱን አርክሶ ፍቅሩ ጥላቻን ሲፈለፍልለት አውጥቶ ጣላት. ... ድንግልና የሚባለውን ሴትነቷን ነጥቋት ጋለሞታ የሚባል የፍርድ ፅሕፈት ወረወረባት።
አሁን:
የያዘችሁን የተሳለ ምላጭ በግራ እጇ ላይ አሳረፈች እንደ ውሃ ኩሬዎች የመሰሉት አይኗቿን ለመጨረሻ ጊዜ ከደነቻቸው! ... ጨፈነች! ጨከነች! በመጨረሻዋ ድንጋይ ራሷን ልትወግር ኃጥእ በኃጢአት ላይ ሊፈርድ....ራሷ ዳኛ ፣ራሷ ተከሳሽ. ..በያዘችው ምላጭ ደምስሮቿን ቆረጠች!
ሁሉም ነገር ፀጥ ረጭ አለ። በኃጢአት ድንጋይ ራሷን ወገረች! ኃጥእዋን በኃጢአት ገደለች!

ልጅነት አላውቅም። ልጅም ሆኜ አላውቅም። ልጅነት ግን ምንድን ነው? ልጅ መባል ልጅ መሆን ምንድን ነው?
ያኔ!.... ሲመሻሽ ፈራለሁ፣....ፀሀይ በጨረቃ ስትተካ እሳቀቃለው፣የማሳልፋቸውን ሌሊቶች በአይነ ህሊናዬ ስቃኝ ያንገፈግፈኛል፣ እጆቿን ይዥ በክንዶቼ ተጠምጥሜባት ትተሽኝ አትሂጂ ብላት ደስ ይለኛል። ግን አልችልም። እናቴ መሆኗን እፈራለው ውስጤ ያፍርባታል።
ለምን? እሷኮ እንደሌሎቹ እናት አልነበረችም። የሚያምር ፊት አልነበራትም፣ ምግብ አትሰራልኝም፣ ልጄ ብላኝ አታውቅም፣ አትወደኝም! ብትወደኝማ. . . ጥላኝ አትሄድም ነበር። አውቃለው! እሷ እናት መሆን አትችልም! እኔም ልጅ!
ግን እኮ ልጅ ነኝ. .. ያውም ከመኝታዬ ስነቃ የምንተራሰው ክንዶች የምፈልግ! የእናትነት ጠረን ማሽተት መማግ የምመኝ! ልጅ ነበርኩ! እጄን ይዛ የምትመራኝ እናት የምፈልግ.....
ከቤት ወጥታ እስክትመለስ ሰጋለሁ ካሁን አሁን ሞተች የሚሉኝ መስሎኝ አውጠነጥናለው። አንዳንዴማ ስጋቴ ልኩን አልፎ እታመማለው...ለምን ነው? እንደዛ የሚሰማኝ አልወዳትም እኮ ሰው ፊት በድፍረት እናቴ ናት ማለትን ከጎኗ እየሄድኩ ልጇ መባልን አልወደሁም እጠላዋለው. ...ልጅነትን እፈራለው ለዛች ሴት ልጅ መሆንን ባስ ሲል መባልን እፈራለው።
አንድ ቀን.......ተኛሁ.....ልጅ ሆንሁ። ልጅነትን ወደድኩት እጆቼን አንስቼ ዳሰስሁ...አጠገቤ ነበረች ነካዋት. ....ጠረኗ ይጣራል እናት እናት ትሸታለች። እናት እናት ትላለች። ከወደ አንገቷ ተወሽቄ ማግሁት! ደስ ይላል! ለዘላለም እዛ መኖሪያን ላሰናዳ ተመኘው።
የልቧ ትርታ ፍቅርን ፍቅርን ያወራል፣ ፍቅሯ ተጋባብኝ። .....ነጋ ከጎኗ በኩራት እየሄድኩ እቺ ናት የእኔ እናቴ አለሁ.......ወደድኳት፣ ከጎኔ ሆና ናፈቀችኝ፣ አላመንኩም! ዛሬ ጥላኝ አልሄደችም ፀሃይ በጨረቃ ተተክታ መልሳ በፀሀይ እስክትሰየም ከጎኔ ነበረች። ታቅፈኛለች፣ በእጆቿ ትዳብሰኛለች......አይኖቼን እያየች ልጄ ትለኛለች!
.... ፍቅር ናት ፍቅር ራሱ አካል ለብሶ እሷ ላይ አየሁት።ድንገት ግን ሁሉም ነገር ሩቅ እየሆነ ፣ መልኳ እየደበዘዘ ሄደ። ቀስ ቀስ እያለ ጠፋ። ...ነቃው ፈለግኳት ከጎኔ አገኛት ይመስል ግን የለችም! ህልሜ ነበረች! ህልሜን አየኋት። ህልሜን በህልሜ አየኋት! ልጅነቴን እናቴን አየኋት! ከህልሜ ፍቅር ያዘኝ ህልሜን አፈቀርኳት!

መንገድ ላይ ነን! እሱ ሊሸኘኝ እኔ ደግሞ ልሄድ....ብዙ ወራት ስጠብቀው ነበር። ከእሱ የምለይበትን ቀን!
ዝምታው ያስፈራል! የሆነ ፀጥ ረጭ ያለ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ድንገት የሚያስፈራ ግን ቀስ ያለ የሚሰቀጥጥ ድምጽ የምሰማ ያህል አስፈርቶኛል. ....
ምን እያሰበ ይሆን? ከእኔ መለየቱ ከብዶት ወይስ ካሁን አሁን ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው አውቶብስ ውስጥ ገብታ በተገላገልኳት እያለ?.....ምንም! ለዝምታው ፍቺ ላገኝለት አልቻልኩም
. .....እኔ ግን ያለ የሌለውን እየቀባጠርኩ ነው ለነገሩ መቀባጠሬ ለእሱ አዲስ አይደለም የእሱ ዝምታም ለእኔ አዲስ አይደለም። ግን ዝምታው ያስፈራል! አይኑን ላነበው ሞከርኩ ጥላቻ አልያም የመለየት ስቃይ? የቱ እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም። ውስጤ ያሰላስላል አፌ ግን ስራ አልፈታም አወራለው ለፈልፋለው እቀባጥራለው!!!
..እየሰማኝ አይመስለኝም. ...በወሬዬ መሃል እንደሰማኝ ለማረጋገጥ ለአፍታ ፀጥ ብዬ ምን ታስባለህ? እለዋለው እሱ ደግሞ ለሰከንድ የሚቆይ ፈገግታ ካሳየኝ በኃላ ፊቱን ቀጨም አድርጎ መልሶ ከሲዖል የሚያስፈራ ዝምታው ውስጥ ይገባል
.......የስልኬን ሰአት ደጋግሜ አያለው። ምነው! ቶሎ ተለይቼው በተገላገልኩ . ..... ከሰፈር ተነስተን ታክሲ ስንይዝ፣ ከታክሲ ወርደንም ባጃጅ ይዘር መናኸሪያ እስክንደርስ ቃል አላወጣም
...ወይኔ! ድምፁን ረሳሁት.....ምን አይነት ድምፅ ነበር ያለው? ወፍራም ወይስ ቀጭን? ...ቆይ ግን ድምፅ ይረሳል? ለዛውም አሁን ከጎኔ የሚሄድ ሰው ድምፅ!....
ሰአቱ፣ ደቂቃው፣ ሰከንዱ ደረሰ...ኡፈይ! ...እስከ ተሳፈርኩት መኪና ድረስ ሸኘኝ የያዘልኝን አነስ ያለች ሻንጣ እያቀበለኝ በቃ መልካም ጉዞ. ..ስትደርሺ ደውዪልኝ። ልክ ቃሉን ከአፉ ሲያወጣው የሆነ ነገር ከሰውነቴ ላይ የተወሰደ ያህል ቀለለኝ
...ኡፍ! ተገላገልኩት! ይሄን ያህል ሸክም ሆኖቦኝ ነበር እንዴ? መልሱ ምንም ይሁን ምን አሁን የሆነ ነገር ቀሎኛል ከዚህ በኃላ ወደ ዋላ የለም. .....ቻው ብዬው ወደ መኪናው ገባው
.....እሱ ግን ምን ተሰምቶት ይሆን? ዞር ብዬ ምን ያህል እንደምወደው እንድነግረው ፈልጎ ይሆን....ወይስ ከዋላው ሮጬ ተጠምጥሜበት ትቼህ አልሄድም እንድለው ጠብቋል? እኔጃ! እኔ ምን ቸገረኝ? አሁን ወደ ዋላ የለም አሁን ወደ ፊት ነው።
✍ ከአርያም ተስፋዬ (2012)

<ቅናተኛ> ነኝ! በተለይ በእሷማ ቀናለሁ!
የዕድሜ'ዬን ግማሽ የኖርኩት እሷን 'ልመስል' ስፅፍ ሳጠፋ ነው። ግን እሷን 'መሆን' አልቻልኩም።
የመሰልኩ በመሰለኝ ሰአትም ፊቱ ስቆም ከሙሉዕነቴ ይልቅ ባዶነቴ ያሳብቅብኛል።
ፈት ነኝ! አምስቴ አግብቼ ፈትቻለው። ያፈገገልኝ ሁሉ ጓዶሎዬን መሙያ እየመሰለኝ ከመኝታ ለመሰየም ቀናት አይፈጅብኝም።
. . .እሷን ግን መሆን አልቻልኩም።
ራሴው ለገፋውት አጨብጫቢ እሻለው፣ ያላከበርኩትን ክብር እንዲከብር ስንቴ ጠብቄሃለሁ ግን እንኳን መሆን መምሰል ራሱ አልቻልኩም።
መቼ'ለት ነው . . . ወግ ማዕረግ በደምግባት አገኝ ብዬ ከአንዱ ልባም ተጠጋው....ምን ዋጋ አለው? ፈጣሪን አለመፍራቴ አይሎብኝ "ውበት ሀሰት ነው" ብሎ ተረተብኝ።
ያቺ አጥንቴ የነቀዘላት ሴት ግን የከበረች፣ በጎዳና ከመታየት ይልቅ በጓዳዋ የተሸሸገች ናት።
. . .አንድ ባል ነው ያላት እንደ ንጉስ ያከበረችው ከመኳንንት ጋር ሲቀመጥ 'ፐ'! ሞገስስ በሱ ቀረ የሚባልላት!
ከመስታዎቴ ቆሜ ገፄ ላይ እሷን ስስል ውዬ አድራለው። የኀላ ኀላ አለመሆኔ ጎልቶ ከወደ ህሊናዬ ያንቧርቅብኛል።
'ራስን መሆን' የሚባል መድኃኒት አለ። በሌላ መስታዎት ራሴን ለማየት ስፍጨረጨር ለካስ የማላድን መድኃኒተኛ ኖሬያለሁ። ፍለጋዬን አስተካክያለው "በአንዱ ቀመር የሌላው ስሌት አይሰራም!"
አሁን የተስፋ ጭላንጭል አለኝ። እኔ ውስጥ እሷን ከመፈለግ የሚልቀው እኔነቴ ጥልቀት እኔን መፈለጉ ነው። ምን አልባት መሲሁ ይመጣ ይሆናል። ጉዴን ነግሮ በፃፈለኝ ማንነት ሌላውን እሆን ብዬ የሰረዝኩ የደለዝኩትን ሽሮ በራስን መሆን ባህር ዳግም ካጠመቀኝ... እጠብቃለው!
እስከዚያው ግን:
የማያቋርጥ ጠፈጠፍ፣ በዝናብ ጊዜ የሚያፈስ ቤት የሚመስለውን አመሌን ይዤ ወጣለው። 'አእምሮ የጎደለው' አገኝ ይሆን ብዬ... 'ከአላዋቂዎች' መካከል ልዝብ አንደበቴን ሰምቶ የሚሳብ ልቦናዬን በጌጤ የመዘነ አይጠፋምና።
✍አርያም ተስፋዬ(2013)

ርካሽ ነገር ይወዳል። ርካሽ ልብስ፣ርካሽ ጫማ፣ርካሽ ሽቶ፣ ርካሽ 'ሰው' ራሱ አይቀረኹም።ሆ ለካስ የሰው ርካሽ፤ ውድ የለም። ውድ'ም ርካሽ'ም የዋጋ ተመን ለወጣለት ነው። ወጣም ወረደም እሱ ረከስ ያለ ቦታ አይታጣም።
ደሃ ነው እያሉ ያሙታል።የነተበው አረንጓዴ ሸሚዙ፣ ከላዩ ወልቆ የማያውቀው ከጊዜ ብዛት ወደ ነጭነት የተለወጠው ሰማያዊ ሱሪውን ያዩ ቢሉ አይደንቅም። የሚጫማው ጫማ ምን አይነት እንደሆነ አይቼው አላውቅም። ግን ርካሽ መሆኑን መገመት አያቅተኝም።
አንድ ቀን
ሸፋፋ ነው! አለች ማን? የምርም ነገሩ አልገባኝም ነበር። አንቺ ደሞ ጫማው ነዋ! ብላ ወደ ጀመረችው ወሬ ተመለሰች።
ርቀቱ እኛ ካለንበት ሶስት እርምጃ ቢሆን ነው። ድምፅሽን ቀንሺ በሚል በጣቴ ምልክት ሰጠዋት። ያለችኝን ለማየት ራሱ ድፍረቱን አጣው።ከሀሳቤ ግን ሊወጣልኝ አልቻለም።
ጫማው በግራ ወይስ በቀኝ የተንሻፈፈው? ሁለቱም እግር ጫማ በአንድ ጊዜ ሊንሻፈፍ ይችላል? አይ! አንዱ ቢሆን ነው። እንጃ! አንዱ ይሆናላ? ጫማ ግን ምን ሲሆን ነው የሚንሻፈፈው? ጫማን የሚያንሻፍፈው የጫማው ጥራት ወይስ የሚያደርገው ሰው አረጋገጥ? የጥያቄ መአት በጭንቅላቴ ይመላለስ ጀመር። ጫማ ስንት ጊዜ ቢደረግ ነው የሚንሻፈፈው? ጫማቸው የተንሻፈፈ ሰዎች ምን ይሰማቸው ይሆን?
ቆይ! የተንሻፈፈ ጫማ ግን ምን ይመስላል? ከተሳፈርኩበት የሀሳብ መርከብ ተመለስኹ። በማያልቀው የሸፈፉ ጥያቄዎቼ አፈርኹ።ሌላ ነገር ለማውጠንጠን ሞከርኹ። አልቻልኩም።
'የተመኘ ካመነዘረ በምን ተለየ?' ሳላየው ይሄን ሁሉ ካሰብኹ ባየውማ ስንቱን አስብ ነበር። እንደሁም አይቼ ብገላገልስ? ላየው አይኔን ወደ እሱ ስወረውር ከጫማው መንሻፈፍ ይልቅ ጫማው ውስጥ ያለው እግሩ በለጠብኝ።ሸፋፋ ጫማ ለካስ ያምራል!
ሲያምር! ቃሉን ከአፌ ሳወጣው አልታወቀኝም ነበር። ማን? ጠየቀችን። ሸፋፋው ልጅ! ማነው ሸፋፋው ጫማ! ውይ አንቺ ደሞ ብላ የእርምጃ ፍጥነቷን ጨመረች።
✍️ አርያም ተስፋዬ(2015)

🛑 ፃማ 🛑
ክፍል ስድስት
ባሰበችው ቁጥርም ይሄ ንግግሩ ይገርማት ነበር። አሁን ግን ነገሮች እየተገለጡላት መጡ። "አፍቅሮኝ ነበር ማለት ነው" እራሷን ጠየቀች። ለዚህ ነው ወደ ንቅናቄው መግባቴን የተቃወመው? የመጨረሻውን ስብሰባ እንዳትካፈል ያላደረገው ጥረት እንዳልነበር ትዝ አላት። በተኩሱ መሀል መጥቶ ጎትቶ ሲወስዳት ዐይኑ ላይ ይነበብ የነበረው ፍቅር ከየት እንደመጣ በዛን ጊዜ ለማወቅ ተቸግራ ነበር። ግን ለምን አልነገረኝም? እኮ ለምን? ልቧ በሀዘን ደምቷል።
ታክሲው ካዛንቺስ ደርሶ ሲቆም ወረደች። የተባለው አድራሻ ጋ ለመድረስ ብዙ ሰአት አልወሰደባትም። አልአዛር ከተባለው ሰው የጥያቄዎቿን መልስ እንደምታገኝ ስለገመተች አድራሻው ላይ የሰፈረውን ቤት ለማግኘት ተቻኮለች። መለስተኛ ሆኖ የተደላደለ ኑሮ ሊኖርበት የሚችልበት ሰፊ ቤት አጠገብ ስትደርስ 'ይሄ መሆን አለበት' አለች በሆዷ። የበሩን መጥሪያ ተጫነችው። የሷን መምጣት በመጠባበቅ ላይ የነበሩ እስከሚመስላት ድረስ በሚያስደንቅ ፍጥነት የቤቱ በር ተከፈተ።
ከፊት ለፊቷ የቆመውን ሰው ስታይ ደነገጠች።ቁርጥ እዮብን። ልቧ በድንጋጤ ምቷን ጨመረች። እንድትገባ በሩን ወለል አድርጎ ከፈተላት። ምንም ሳታመነታ ወደ ውስጥ ዘለቀች። ጊዜ ሳይፈጅ 'አልአዛር' ብሎ እጁን ለትውውቅ ዘረጋ። 'ብሌን' አለች ነገር ግን ራሷን ማስተዋወቅ አስፈላጊ መስሎ አልታያትም። ወጣቱ ካወቃት የቆየ ይመስላልና።
አልአዛር ገና ብሌንን እንዳየ የወንድሙ እንደዛ በፍቅር መሰቃየት ተገለጠለት። ማንስ ቢሆን ከዚች ቆንጆ የፍቅር ወጥመድ ያመልጣል ሲል አሰበ። ሰውነቷ በድካምና በዱላ የተጎዳ ስለሚመስል ዛሬ ወንድሙ በአደራ ያስቀመጠውን ወረቀት ቢሰጣት ሊጎዳት ይችላል ብሎ ስለጠረጠረ ወረቀቱን ነገ ሊያሳያት ቀጠሮውን አራዘመ።
ቤቱ የአንድ ወንድ መኖሪያ ብቻ አይመስልም። በፅዳት ተስተካክላ የተዘጋጀችው ሳሎን የሴት እጅ የግድ ያረፈባት መሆኑን ገመተች። እንደገባች ከፊቷ የነበረው ሶፋ ላይ ተዘረረች። ድካሙና ረሀቡ ተደራርበው አቅም አሳጥተዋታል። የልቧ ሀዘን ደግሞ ይበልጥ ሰውነቷን ጎዳው። "ወንድሙ ነው?" እንዴት ወንድም እንዳለው ለማንም ሳይናገር ኖረ? ግራ ገብቷት ራሷን ጠየቀች።
አልአዛር ፈጠን ብሎ የሚበላ አቀረበላት። ምግቡን ከፊት ለፊቷ ቀርቦ ስታየው የረሀብ ስሜቷ ተቀሰቀሰ። በልታ እንደጨረሰች ወጣቱ በአበላል ሁኔታዋ መገረሙ አይቀርም ብላ አሰበች። እሱ ግን የተረዳት ይመስላል።
ራሷን በድንጋይ እንደተመታ ሰው ይፈልጣታል።መቋቋም እስኪያቅታት ድረስ ህመሙ እየጨመረ ሄደ። የራስ ምታት መድኃኒት ይኖርሃል? አለች ወጣቱን እያየች። ወደ መኝታ ክፍል ሄዶ ሁለት መድኃኒቶችን ይዞ መጣ። ይኸውና የራስ ምታት መድሀኒቱ ብሎ አንዱን ወደ እጇ አቀበላት። "ይሄ ደግሞ የእንቅልፍ ኪኒን ነው።" ብዙ እረፍት ያገኘሽ አትመስዪም አላት ፊቷን እያየ። ብሌን አላንገራገረችም ሁለቱንም መድኃኒቶች ዋጠቻቸው። የእንቅልፍ መድኃኒቱ ለመስራት ጊዜም አልወሰደበትም። ጭንቅላቷን ሶፋው ላይ አስደግፋ ለመተኛት ሞከረች። አልተመቻትም። ወጣቱ ሶፋው ላይ ሙሉ ለሙሉ ወጥታ እንድትተኛ ትራስና ወፍራም ጋቢ ከመኝታ ቤት አምጥቶ ሰጣት። መድኃኒቶቹን መኝታ ቤት አስቀምጦ እስከሚመለስ እንቅልፍ ወስዷታል።
ከሶፋው አጠገብ ቆሞ ሶፋው ላይ የተኛችሁን ብሌንን በአድናቆት ይመለከታታል። ሁለመናዋ ልብን ይማርካል። በብዙ ነገር ራሳቸውን አስጊጠው ከሚመለከታቸው ሴቶች ይልቅ በሷ ውስጥ ከጉስቁልናዋ በላይ ጎልቶ የሚታየው አፍዝዞታል። እጁን ዘርግቶ.......
✍️✍️✍️✍️ይቀጥላል...
@yabsiratesfaye ለወዳጅ ለዘመዶ ያጋሩ

ክፍል ሰባት
እጁን ዘርግቶ የተራቆተ እግሯን ሸፈነላት። ምን ነካኝ? አለ ራሱን ቆጣ ብሎ። የተገተረበትን ቦታ ለቆ ወደ መኝታ ቤቱ አመራና አልጋው ላይ ተወረወረ። ጎጃምን ለቆ ሲወጣ የሚያስታውሰው ነገር የለም። በዛን ጊዜ በጣም ልጅ ነበረ። ነገሮች ተረስተውታል። አንድ የማይረሳው ነገር ግን አለ። ታናሽ ወንድሙ እዮብ። በሁለት አመት ውስጥ አከታትላ የወለደቻቸው እናታቸው የ አራት ወንዶችና የሁለት ሴቶች ልጆች እናት ናት። የእድሜ ልዩነታቸው ብዙም ስላይደለ እዮብና አልአዛር መንታ ይመስላሉ።
አባታቸው በእናታቸው ላይ የሚያደርሰውን ግፍ ማየት የሚችልበት ጥንካሬ ስላጣ አንድ ቀን ወንድሙ እዮብን ብቻ ተሰናብቶ ጎጃምን ለቀቀ። ለቀቀ የሚለው ቃል አልአዛር እዚህ ቦታ ለመድረስ ያየው መከራና ጊዜ ባይገልፀውም እንዲሁ ለቀቀ ይባል። የወሰደበት ጊዜ ረጅም ነው ምን አልባትም የእድሜውን እኩሌታ ያህላል።
እዮብ ወደእዚህ አገር ሲመጣ አልአዛር ትንሽ ሱቅ ከፍቶ በመነገድ ላይ ነበር። የስጋ ነገር ሆነና እንደገና ለመገናኘት ዝምድናቸውንም ለማደስ ጊዜ አልፈጀባቸውም። እዮብ አዲስ አበባ ሲመጣ እናታቸው ሆነ አባታቸው ወንድም እህቶቻቸው በወረርሽኝ አልቀው ነበር። ብቻውን የቀረው አንድ እዮብም የተመደበበት ወደነበረው ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ በጎጃም የቀረው አንድም ቤተሰብ የለም። ሁሉም አልቀዋል። ለዚህም ተጠያቂው በምንቸገረኝነት ከዳር ሆኖ ሲመለከት የነበረው መንግስት ለመሆኑ ደምድሟል።
ልቡ በቀልን እንዳረገዘ ዩኒቨርስቲውን ተቀላቀለ። ከአንድ ወር በኃላም በልጅነቱ የተለየውን ወንድሙን አገኘና የብቸኝነቱን ስቃይ መቋቋም ቻለ። የእዮብና የአልአዛር ገበያ ግንኙነት በሚስጥር እንዲሆን ሀሳብ ያቀረበው እዮብ ነበር። አልአዛር ከአገሩ ከመውጣቱ በፊት የነበረውን ስም ሙሉ በሙሉ ቀይሮታል። "አንተነህ" ምን አይነት አስቀያሚ ስም ነው ሲል አሰበ። ገና አዲስ አበባ እንደገባ ወደ አልአዛር ቀየረ። ወንድማማቾቹ በእረፍት ቀናቸው በድብቅ ተገናኝተው ይወያያሉ። በመካከላቸው የነበረው ፍቅር ጠንካራ ነው። አልአዛር ወሩንና ቀኑን ባያስታውሰውም ብቻ የሆነ ቀን ወንድሙ እዮብ ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለ ወደ እሱ ሲሮጥ ተመለከተ። ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ ጓጉቶ ስለነበር የእዮብ ትንፋሽ መለስ እስኪል ራሱ አልጠበቀም። ምን እንደሆነ ለማወቅ በጥያቄ ያጣድፈው ጀመር።
ፍቅር ይዞኛል! አለው ከእሱ መፍትሔ ያገኝ ይመስል። ታዲያ ምን ችግር አለው? አለ አልአዛር በፍቅር መያዝ እንዲህ ወንድሙን ያስጨነቀበት ምክንያት አልገባሁም። ባክህ አድምጠኝ አለ እዮብ የወንድሙ ቸልታ ቅር አሰኝቶት። የተማሪዎች ህብረት አባል ነኝ። ልጅቷም እንዲሁ አለ እዮብ ከወንድሙ የደበቀውን ሚስጥር ማጋለጡ እያስፈራው።
አልአዛር ስጋቱ እውን ሆኖ ሲያየው የሚያደርገውን አሳጣው። ድሮውኑ የወንድሙን ቆራጥነት ያውቀዋል። የህብረቱ አባል መሆን ማለት ራስን በሸምቀቆ ወደተዘጋጀ ገመድ ማስገባት ማለት ነው። የእዮብን ግትር ውሳኔ ማስቀረት ፍፁም እንደማይቻለው ስለተገነዘበ በሀዘን አንገቱን አቀርቅሮ ዝምታን መረጠ።
አሊ አንድ ነገር በል እንጂ! አለ እዮብ የወንድሙን ዝምታ ጠልቶ። ምን ልበልህ? ራስህን ለሞት አሳልፈህ ስትሰጥ ዳር ሆኖ ከመመልከት ውጪ ምን አይነት ምርጫ አለኝ? አለ ተስፋ በቆረጠ ድምፅ። ከተል አድርጎም ነግረአታል? አለ አልአዛር ንግግሩ ህይወት አልባ ነበር። አልነገርኳትም ልነግራትም አልፈልግም። የህብረቱ አባል እንዳትሆን ያላዴግኩት ጥረት አልነበረም ሊሳካልኝ አልቻለም እንጂ።
ህብረታችን በቅርቡ በመንግስት ሀይል ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ዝግጅት አድርጓል። በዚህ ነገር ላይ እንዳትሳተፍ ብፈልግም ቁርጠኛ ሀሳቧን ማስቀየር የማይቻል ነገር ነው። ይህንን ለወንድሙ መንገሩ እፎይታን ሰጥቶታል። አልአዛር ግራ ተጋብቶ ወንድሙ ላይ አሁንም እንዳፈጠጠ ነው። እርዳታ ሲያሻት ወደ አንተ ትመጣለች። ለእኔ ስትል እንዳታሳፍራት። አለ ታላቅ ወንድሙን እያየ። ብሌንን አደራ መስጠቱ አርክቶታል። ፍቅሩ በአስተማማኝ እጆች ላይ ትሆናለች። ይህ ደግሞ ለእሱ ትልቅ ረፍት ነው። የልቡን አውጥቶ መንገር አለመፈለጉ የብሌንን እሺታን አልያም እምቢታን ማወቅ የለመፈለጉ ምክንያት ለአልአዛር አልተገለጠለትም።

ክፍል ስምንት
እዮብ የእሺታም ሆነ የእንቢታ መልሶቿ እንደሚጎዱት አስቧል። እንቢ ስትለው ልቡ በማይጠገን ሁኔታ ይሰበራል። ይህ ደግሞ ህብረቱ እሱን በጥብቅ በሚፈልግበት ሰአት የማይሆን ነገር ነው። እሺ ብትለው ደግሞ ፍቅሩን የሚያጣጥምበት ጊዜ የለሁም። በቅርቡ እንደሚሞት አውቋል። እሷም ብትሆን ከሞተ በኃላ በሀዘን እንድትሰቃይ አልፈለገም። እራሱን አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተተ የጥቃቱ ጊዜ ደረሰ። ያ ከሀዲ ዳዊት ባያጋልጣቸው ኖሮ ምናልባትም ዛሬ በህይወት ሊኖር ይችል ነበር። ሁሉም ነገር ግን በእዮብ ሞት መዝገቡን ዘጋ።
ብሌን ሌሊቱን ሙሉ በቅዥት ስትንፈራገጥ ነው ያደረችው። እዮብ ተመቶ ሲወድቅ ፣ ያ ከሀዲ ዳዊት እላይዋ ላይ ሲከመር እንዲሁም ሌሎች መጥፎ ነገሮች እንቅልፏን ሰላም አሳጡት። ከእንቅልፏ የኖረችው እንኳን "አይሆንም! ጫፌን እንዳትነካኝ! አንተ ከይሲ! ብላ አንቧርቃ ነው።
ስትነቃ ከሶፋው ትይዩ ባለው ጠረጴዛ ላይ የሻይ ስኒዎች ፔርሙዝና በትሪ የቀረቡትኔ ዳቦዎች ተመለከተች። አልአዛር ቀድሟት ተነስቷል ማለት ነው። ከዚህ በፊት ዶሮ ሳይጮኸ የምትነቃው ብሌን ዛሬ ስትነሳ ሰአቱ ወደ ሶስት ሰአት ተጠግቶ ነበር። የትላንቱ ድካሟ ትንሽ ጋብ ብሏል። አልአዛር ከጎኗ ባለው ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ እንድትበላ ጋበዛት። የሷ የምግብ ፍላጎት ግን ሞቶ ነበር። እጇን ታጠበችና እንደነገሩ ቀማመሰች። ትላንት በጭንቅላቷ ውስጥ ሲመላለሱ የነበሩትን ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ፊቷን ወደ አልአዛር አቅንታ " አንተ ለእዮብ ወንድሙ ነህ? ማለቴ መልካችሁ ይመሳሰላል" አለች። ግልፅ ለማድረግ አዎ! የአንድ እናት የአንድ አባት ልጆች ነን። አላት በአጭሩ። እሷ ግን ብዙ ነገሮችን ለመጠየቅ ብትፈልግም የትኛውን ማስቀደም እንዳለባት ጨነቃት። እዮብ ለምን ሊደብቃት ፈለገ? ለምን ማፍቀሩን አልነገራትም? ለምን እንደሚሞት እያወቀ ራሱን ለአደጋ አጋለጠ? ለምን? ለምን? ለምን? የሚሉ ጥያቄዎች በጭንቅላቷ ደውላቸውን ያሰማሉ።
ለጥያቄዎቿ መልስ ይሆንላት ይመስል በአልአዛር አይኖች ላይ አይኖቿን እንደተከለች ናት። አልአዛር ከኪሱ ውስጥ የሆነ ወረቀት አወጣ። ብሌን አልአዛር ወደ እሷ የዘረጋውን ወረቀት የያዘ እጅ እያየች እንደመቀበል ዝም አለችው። "እዮብ ላንቺ እንድሰጥ በአደራ ያስቀመጠው ወረቀት ነው!" ተቀበዪኝ! አለ እጁን ይበልጥ ወደ እሷ አሰጠግቶ። ቀስ ብላ ከእጁ ላይ ወረቀቱን ወሰደች። በእርጋታ ከፈተችው። በደንብ ዘርግታ ለማንበብ ተዘጋጀች።
በአሁኑ ሰአት ነገሮች ሊጨልሙብሽ ይችላል። ግን ተስፋ አትቁረጭ። አልአዛር ከጎንሽ አለ ምንም አይደርስብሽም። ፍቅሬም ሁሌም ይከተልሻል። ትላንትም ዛሬም እስክሞትም አፈቅርሻለሁ። በህብረቱ ውስጥ የማደርግብሽ ተፅዕኖ አሳዝኖሽ ከሆነ ይቅርታ እንደምታደርጊልኝ አምናለሁ። አንቺን ከአደጋ ለማውጣት ያደረግኩት ጥረት ነው ባይሳካልኝም። ቢሆንም ራስሽን ከአደጋ የምታወጪበትን መንገድ እንደማታጪ ፅኑ እምነት አለኝ። ራስሽን ብዙ በሀዘን አትጉጂ። የወደፊት ተስፋሽ ብሩህ ነውና። በፅናትና በጥንካሬ ችግሮችሽን እለፊያቸው። መልካምሽን ባይ ምኞቴ ነበረ። የሚሳካ አይመስለኝም እንጂ። ምናልባትም ይሄን ወረቀት ስታነቢ ሞቼ ይሆናል።
ብሌን እዚህ ጋር ስትደርስ ራሷን መቆጣጠር አቃታት። እንባዎቿ እንደጎርፍ እየወረዱ ወረቀቱን አራሱ። አይኗቿ በእምባ ስለተከለሉ ወረቀቱ ላይ የተፃፉትን ቃላት አገጣጥሞ ለማንበብ አቃታት። እንደምንም ብላ እንባዎቿን ለማስቆም ታገለችና ማንበቧን ቀጠለች። " ጠልተሽኝ ከሆነ አለመጠየቄ መልካም ነበር። ምን አልባት አንቺም እንደኔ ተመሳሳይ ስሜት ተሰምቶሽ ከሆነ ለምን ማፍቀሩን አልነገረኝም የሚል ጥያቄ ሊፈጥርብሽ ይችላል። እኔ መሞቴን ያወቅኩ ሰው ነኝ። የሌላ ሰውን ህይወት ከእኔ ጋር አብሮ እንዲጠፋ አልፈልግም። በተለይ ደሞ ያንቺ! ያለ ደስታ የሚኖር ሰው ከሙት እንደሚቆጠር መዘንጋት የለብሽም ስለዚህ ተደስቶ ለመኖር ሞክሪ። ፍቅሩን ያጣ ሰው ምን ያህል እንደሚሰበር ይገባኛል አንቺን ግን ለዚህ የሚያደርስ ፍቅር የያዘሽ አይመስለኝም። ያም ሆነ ይህ ማለት የፈለግኩት በማንኛውም መንገድ ራስሽን በሀዘን አትጉጂ። ማፍቀሬን ያልገለጥኩልሽ አንቺና ድርጅቱን ከአደጋ ለመጠበቅ ስል ነው። ባክሽ ላጠፋሁት ጥፋት ሁሉ ይቅር በዪኝ። ሁሌም አፈቅርሻለሁ! እዮብ።

ክፍል ዘጠኝ
ደብዳቤውን አንብባ እንደጨረሰች ራሷን ጉልበቶቿ መሀል ወሸቀቻቸው። ለምን ይሄን ሁሉ መስዋዕትነት? ለምን ይህን ያህል ለአንዲት ሴት ራስን አሳልፎ መስጠት? በምላሹ ታፍቅረው አታፍቅረው ሳያውቅ ለምን ራሱን ለእሷ ሰጠ? በህይወት ቢኖርና ይህንን ጥያቄዋን ቢመልስላት በወደደች ነበር ግን እዮብ አይመለስ አሸልቧል።
ተሳሳትክ እዮብ ብትነግረኝ ይሻል ነበር። ከጭንቅላቴ የማይሻር ጠባሳ ተውክብኝ! መቼም ከፊቴ የተዘረረውን ያንተን አካል መዘንጋት አልችልም ፣ከአእምሮዬ ሊጠፋ አይችልም። እዮብ ስህተት ሰርተኻል አዎ በጣም ተሳስተሃል! እጇ ላከ የነበረውን ወረቀት ጨመደደችው። ምን ልታስብ እንደሚገባት ማወቅ አልቻለችም። ብቻ ልትከፍለው የማትችለው የእዮብ ውለታ አለባት።
አፈቅረው ነበር? እራሷን ጠየቀች ልቧ የአዎንታም የአሉታም ምላሽ አልሰጣትም። ለረጅም ሰአት አነባች። አልአዛር ለማባበል አልሞከረም። ምክንያቱም የእሱም እምባ እየፈሰሰ ነበር። አንድ ብቸኛ ወንድሙን እንዳጣ ገብቶታል። በጀግንነት የሞተው የወንድሙ ወኔና ድፍረት ታወሰው። ለእዚች ከፊት ለፊቱ ለተቀመጠችው ሴት የነበረው የፍቅር ጥንካሬ የተለየ ነበር። ምን ያደርጋል? በህይወት ሳለ መፈቀሯን ሳታውቅ ከሞተ በኅላ ለፍቅሯ የከፈለውን መስዋዕትነት የተረዳችው ወጣት ላታገግም ቆስላለች። በምንም መንገድ ሊያፅናናት አይችልም።
ማን ያውቃል? ጊዜ የሚያመጣው አይታወቅም አለ ለራሱ እዮብን ልትዘነጋ የምትችልበት መንገድ ይኖራል። በተቻለው መጠን ሀዘኗን ልትረሳ የምትችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በሙሉ አቅሙ ቆርጧል። ከመንግስትም የደንነት አባላት ጋር በነበረው የጠበቀ ግንኙነት አንድ የውሸት መታወቂያ ሊያገኝላት ችሏል። የእሷን መምጣት ቀደም ብሎ እየጠበቀች ስለነበር ሁሉንም ነገር አስቀድሞ ዝግጁ አድርጓል።
መታወቂያውን ከኪሱ አውጥቶ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠው። 'መአዛ አሸናፊ' ይላል። ምንድን ነው በሚል ሁኔታ ተመለከተችው። አዲሱ ስምሽ ነው ትንሽ ራስሽን መቀየር ይኖርብሻል አለና ትርምስምሱ የወጣውን ረጅም ፀጉሯን አየ። መቆረጥ ሳይኖርበት አይቀርም። በተወሰነ መልኩ የፊትሽን ገፅታ ሊቀይረው ይችላል። ግን ይህን የመሰለ ፀጉር ተቆርጦ ሲወድግ ያሳዝናል ሲል አሰበ።
ብሌን አላመነታችም። በህይወት መኖር እስካለባት ድረስ ራሷን መለወጧ የግድ ነው። ሻወር መውሰድ ፈልጋለች። አልአዛር ጭንቅላቷን ያነበበ ይመስል መታጠብ ከፈለግሽ ሻወር ቤቱን ላሳይሽ እችላለሁ። ፀጉርሽን የምትቆርጪበት መቀስ በስተቀኝ ባለው ኮመዲኖ ላይ ይገኛል። አላት ጊዜ ሳታጠፋ ልብሷን አወላልቃ ውሀው ውስጥ ተነከረች። ውሀው እንደውጪው ቆሻሻዋ ልቧ ውስጥም ያለውን ሸክም መውሰድ ቢችል ምንኛ በተደሰተች ነበር። ዐይኗን ጨፍና ከላይ የሚወርደውን ውሀ ከጭንቅላቷ ጀምሮ ታች እስኪደርስ ድረስ ታዳምጠዋለች። ከውሀው አንድ መፍትሔ ታገኝ ይመስል አሁንም አሁንም ትነከራለች። ሰውነቷ ቢፀዳም መውጣቱን ጠላችው። በጣም ከምትወዳት ምስኪን እናቷ ጋር እንደማትገናኝ ተረድታለች። ይሄኔ እማዬ ሞቴን ሰምታ ሀዘን ተቀምጣ ይሆናል ስትል አሰበች። በራ ሄዳ አይዞሽ በህይወት አለውልሽ ልትላት ተመኘች።

ክፍል አስር
በግድ ከውሀው ወጣችና ወደ መስታወቱ አመራች። መስታወቱ ጎን ካለው ኮመዲኖ ላይ መቀሱ ተቀምጧል። አላመነታችም ብድግ አድርጋ ፀጉሯን ከጆሮዋ ትንሽ ዝቅ አድርጋ ቆረጠችው። ስትወጣ አልአዛር ተደነቀ። ከፊል እሷነቷ ፀጉሯ ሲቆረጥ ተቀይሯል። መአዛ አሸናፊ የሚለውን መታወቂያ ከጠረጴዛው ላይ አንስታ አየችው። ፎቶ የሚለጠፍበት ቦታ ባዶ ነው። ይሄ ማለት ደሞ ፎቶ መነሳት አለባት። አዲስ በገባችበት ኑሮ ውስጥ ያላት አስተዋጽኦ ምን እንደ ሆነ ተቀምጣ ማሰላሰል ጀመረች። ማንነቱን ከማታውቀው እንግዳ ሰው ጋር ተረጋግታ መቀመጧ ገርሟታል።
አልአዛር የተጠቀለለ ጋዜጣ ያለበትን ፌስታል ወደ ፊቷ ወረወረና ልብስሽን መቀየር አለብሽ። ከዛም ይዘሻቸው የመጣሻቸውን ልብሶች አቃጥያቸው አላት። ትህዛዙ አስደንግጧት ይሁን ገርሟት በማያስታውቅ ሁኔታ ዞራ ተመለከተችው። አልአዛር የአነጋገሩ አስደንጋጭነት የተረዳው ዘግይቶ ነበር። ማለቴ እራስሽን መለወጥ ካለብሽ ልብሶችሽንም እንዳይገኙ ማጥፋት ይገባሻል ብዬ አስቤ ነው አለ ይህንን ሲናገር አፉ ይንተባተብ ነበር።
ተመልሳ ወደ ሻወር ቤት ገባችና ልብሱን ቀይራ ተመለሰች። የሰጣትን ልብስ አልወደደችውም። የወንድን ትኩረት ለመሳብ የሚፈልጉ ሴቶች የሚለብሱት አለባበስ መስሎ ስለታያት ራሷን ከላይ እስከታች በጥላቻ ተመለከተች። አልአዛር የፊቷን ሁኔታ ሲመለከት በልብስ ምርጫው ተናደደ።
ምኑ የማልረባ ነኝ? ብሎ ራሱን ገሰፀ። የገዛው ልብስ ከወራት በፊት አብራው የነበረችውን የሴት ጓደኛውን ምርጫ ነበር። ምን ነካኝ? አለ በልቡ ትዝታና ብሌን ማለት ፍፁም የማይገናኙ የአንድ አለም ሁለት ገፅታዎች ናቸው። ብሌን አልአዛር የመንግስት ሰራቸኛ? ተማሪ? ነጋዴ? ይሁን የምታውቀው ነገር የለም። ይሄ ደግሞ አስጨንቋታል። ከጓኗ ያለውን ሰው ማንነት አለማወቋ የምርም ያሳስባል።
የት ነው የምትሰራው? ማለቴ ስራህ ምንድን ነው? አለችው ከጎኑ ቁጭ ብላ። 'ንግድ' አላት በአጭሩ። ከቤቱ አንድ መቶ ሜትር ርቀት ላይ የመኪና እቃዎች መሸጫ መደብር አለው። ከብዙ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ያገናኘው ይሄ ነው። ባገኘው ክፍተት ተጠቅሞ አንዳንድ መረጃዎች ለእዮብ ሲያቀብለው ነበር።
የዛሬን አያድርገውና አልአዛርና ትዝታ የተገናኙትና የተለያዩት በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው። ትዝታ አልአዛርን አሁን ድረስ ታፈቅረዋለች። የተቋረጠውን ግንኙነታቸውን እንዲቀጥል ያላደረገችው ጥረት አልነበረም። ቀድሞውኑም ቢሆን ግንኙነታቸው ሲጠነሰስ አልአዛር የችግር መርሻ አድርጎ ነው የወሰዳት እንጂ በልቡ ፍቅር የተባለ ለእሷ የለውም ነበር። ለትዝታ አልአዛርን ማጣት ማለት ሞት ነው። በየትኛውም መንገድ አልአዛርን መልሳ በእጇ ማስገባት አለባት ይህ ቁርጠኛ ውሳኔዋ ነው። አልአዛር ምን ሲያቀብጠው ከእሷ ጋር ግንኙነት እንደጀመረ አሰበ። ያገናኛቸውንም ሰውን ደጋግሞ ረግሞታል። ትዝታ የፍቅር ግንኙነታቸው ከቋመም ቢሰነባብትም ቤቱ መምጣት አላቆመችም። አበሳጭቶና አስቀይሞ ከራሱ ሊያርቃት ሞክሯል። እሷ ግን ሁሌም ተመልሳ ያው ነች።
አልአዛር ያሰጋው ነገር ትዝታ ብሌንን ከቤቱ ስታይ ምን ሊሰማት እንደሚችል ነው። የትዝታ ብሌንን ማየት ለእሱም ሆነ ለብሌን አደገኛ ነው። ብሌንን ገና ስታይ ለነገር ሽረባ የማይመለሰው ጭንቅላቷ ተንኮል እንደሚያስብ ያውቃል። ለእሱ ያላት ፍቅር የብሌንን ህይወት የሚቀጥፍ ነው።
የትዝታ አባት አንድ የታወቁ ነጋዴ ናቸው። በቅንጦት ያደገችው ትዝታ የፈለገችውንና የወደደችውን ለማግኘት ተቸግራ አታውቅም። ምርጫዋን ከምላሷ ቀድሞ ታገኘዋለች። አባቷ ብቸኛ ልጃቸውን የሚያስቀይም ነገር አይፈልጉም። አልአዛር ከሚባል ሰው ጋር ከተለያየች በኃላ ያመጣችው የፀባይ ለውጥ አሳስቧቸዋል። "ልጄን እንዲህ አስጨንቆማ በሰላም አይኖርም አሉ በንዴት መሬቱን በእርግጫ ብለው።

ያቀፍኩትን ጣዕረ ሞት ለመላቀቅ ሰከንዶች አልፈጀብኝም። ምንም የስንብት ቃል ሳላወጣ እየተጣደፍኩ ከፊት ለፊቴ ያገኘሁት ታክሲ ውስጥ ዘው አልኹ።
ታክሲው የት እንደሚሄድ የጠየኹት ከጋቢናው ቀጥሎ ካለው መቀመጫ ላይ ሶስተኛ ተደራቢ ሆኜ ከተቀመትኹ በኅላ ነው።
ከጎኔ የተቀመጠችሁን ሽቅርቅር ወጣት "ታክሲው የት ነው የሚሄደው?" አልኳት። ዝም! ምንም ሳትመልስልኝ ከፍ ዝቅ አርጋ አይታኝ በእጇ ወደያዘችው ተንቀሳቃሽ ስልክ አቀረቀረች።
ራሴን ተመለከትኹ... ምን አልባት ጣዕረሞት መስያት ይሆን? ቀፈፈኝ የሆነ የማይገባ ስሜት ተሰማኝ።
ረዳቱ ሂሳብ ሲሰበስብ የታክሲውን መዳረሻ አወቅኹት። ተመስገን! አልተሳሳትኹም።
ወዲያው ግን እነዛ ስሜቶች አካል ለብሰው አያቸው ጀመር። በጣም የምትበርድ ፀሐይ፣ እንደጭቃ የሚለጠፍ አዋራ፣ የሚሰነጥፍ ሽቶ፣ የቆንጆ ቀፋፊ መልኮች ይታዩኛል ይሰሙኛል።
ወይኔ! ደረቴ አካባቢ ስንጥቅ የሚያደርግ ውጋት ወጋኝ። አዞረኝ ፤ አቅለሸለሸኝ
በጠራራ ፀሐይ እት ት ት እያልኹ ስንቀጠቀጥ ላየኝ አጃኢብ ያስብላል የማያቸው ፊቶች ሁሉ የገጠጡ ጥርሶች፣ ደም የለበሱ ዐይኖች፣ የተጣመመ አፍንጫ..... ሰው አስጠላኝ ጣዕረሞት አንገሸገሸኝ!
የብዙ ፈገግታ ጓዳ ለቅሶ፣ ከብዙ ጠርጣራ ቆሌዎች ውስጥ የተሰበረ ዕምነት ፣ ጥቅመኝነት፣ አስመሳይነት ከተሸከምነው ስጋ በታች በቁም ያለ ሬሳ።
በስመ - አብ
በስመ - ወልድ
በስመ - መንፈስ ቅዱስ እንደምንም ኃይሌን አሰባስቤ ወራጅ አለ ቃሉ ከአፌ ሲወጣ የሆነ ነገር ቀለለኝ የቀን ቅዥት አይባል የያዝኩት የጨበጥኹት አለም ነው። የኔ ማነው የኛ አለም ክፋት ፣ ምቀኝነት፣ ጭካኔ ፣ ራስወዳድነት፣ ፍርሀት፣ ህመም፣ የልብ ስብራት፣ ክህደት፣ ሞት....
✍️ አርያም ተስፋዬ

ክፍል አስራ አንድ
በእሷ የመጣ ማንንም ቢሆን አይምሩም። ብቸኛ ልጃቸው ናትና። እንደ ዐይናቸው ብሌን ይሳሱላታል። ታዲያ በዚህ አይነት አስተዳደግ ያደገችው ትዝታ ፈልጋ ልታገኘው ያልቻለችው አንድ ነገር አልአዛርን ብቻ ቢሆን ምን ያስገርማል? ለእሷ የተመኘችሁን ማጣት ትልቅ ሽንፈት ነው። ሽንፈትን ደግሞ በፀጋ የሚቀበል ጭንቅላት የላትም። በፍፁም ላጣው አልችልም ብላ ለራሷ ደምድማለች።
በቅርቡ በመካከላቸው ግጭት ስለተፈጠረ ለጥቂት ቀናት ታግሳ ከእሱ ላለመገናኘት ወስናለችና ወደ ቤቱ ዝር አላለችም። ወደ ሱቁም ቢሆን አልሄደችም። ዐይኑን ካየች ሶስት ቀናት ቢያልፋትም ቢያንስ አንድ ሳምንት በትዕግስት ለማሳለፍ ራሷን አጠነከረች።
አልአዛር የትዝታ መጥፋት ቢያስገርመውም አጋጣሚው አስደስቶታል። እስከመጨረሻው ባያገኛት ምርጫው ነው። አልአዛር ትዝታን ከብሌን ጋር ሲያነፃፅር ልዩነታቸው የሰማይና የምድር ሆነበት። ብሌን ነገሮችን አጢና አውጥታና አውርዳ ነው የምታከናውናቸው። በዚህ በጭንቅ ጊዜ ላይ ሆና ራሱ ራሷን እንደጠበቀች ነው። ትዝታ ግን! አለ በሆዱ ትዝታ ግን ደገመው "ከራሷ ውጪ ለሌላው የማታስብ ስግብግብ ናት። ምቾቷ ይጠበቅ እንጂ ማንኛውም ሰው ለእሷ ፍላጎት ቢሰቃይ ግድም አይሰጣት። በአንድ ወቅት ከእንደዚች አይነት ሴት ጋር የፍቅርን ግንኙነት መመስረቱ አሁን ድረስ ያስገርመዋል።
በሀሳብ ብዙ እንደተጓዘ የውጪው በር ተንኳኳ። ብሌን የምትገባበት ጠፍቷት በፍርሀት ትንቀጠቀጥ ጀመር። አልአዛር ከትላንት በስቲያ ከሁለት ሳምንት በኃላ መጣለው ብሎት የሄደው ናትናኤል ዛሬ ሊመለስ እንደማይችል ያውቃል። ታዲያ ማን ሊሆን ይችላል? ራሱን በራሱ ጠየቀ። ድጋሜ በሩ ተንኳኳ። ትዝታ ብትሆንስ የሚለው ግምት ሲታሰበው ሊፈጠር የሚችለው ችግር ገና ካሁኑ ዘገነነው።
ፈራ ተባ እያለ ወደ በሩ አመራ። ለነገሩ በሩን ሲያንኳኳ የነበረው ሱቁ ውስጥ አብሮት የሚያሻሽጠው ታዳጊው አብይ ነበር። ያለቀ እቃ መግዣ ገንዘብ ሊወስድ ነበር አመጣጡ። የአልአዛር ልብ መለስ አለች። ገንዘቡን ከሰጠው በኃላ በሩን ጥርቅም አድርጎ ዘጋው። ቢሆንም ብሌንን ማነች ብሎ ለትዝታ እንደሚናገር ጨነቀው። በኃላ በኃላ አንድ ሀሳብ መጣለት። አብሮት የሚኖረው ናትናኤል!
ብሌን የናትናኤል እጮኛ ናት ብሎ ለትዝታ ሊዋሻት ይችላል። መቼስ ከናትናኤል ፀባይ አንፃር የማይታመን ነገር ነው። እንደምንም ብሎ ግን ማሳመን አያቅተውም። ዋናው ጭንቅ ግን ናትናኤል በሌለበት እሷ እዚህ ምን ትሰራለች የሚለው ጥያቄ ነው። ለዚህ የሚሆን ውሸት መፍጠር ከበደው። ሌላው የረሳው ጉዳይ ይሄንን ዘዴውን ለብሌንም ሆነ ለናትናኤል አልነገራቸውም። የልብ ጓደኛው ናትናኤል ትንሽ ባያንገራግርም እሺ እንደሚለው አይጠራጠርም። ግን ብሌንስ? ሌላ ጥያቄው ነበር። አሁኑኑ ሊነግራት ይገባል። ምን አልባት ትዝታ ዛሬ ልትመጣ ትችላለች።
በረንዳው ላይ ቆሞ ይሄንን ነገር ሲያውጠነጥን የብሌንን ከጀርባው መቆም አላስተዋለም። ማን ነበር? አለች ብሌን! ስጋቷ ከፋቷ ላይ ይነበባል። አይ የሚያስጨንቅ አይደለም። ሱቁ ውስጥ የሚሰራው ልጅ ነው። አለ ፈገግ እንደማለት ብሎ። እንዴት ብሎ እንደሚነግራት እያሰበ ነው። ኧ .... ብሌን ብሎ ጀመረ። ራስሽን ከአደጋ ለመጠበቅ ስትዪ አንድ ነገር ልታደርጊ ይገባል አለ ጨርሶ ለመናገር ድፍረት አጥቶ።
ምን? ምን ማድረግ ይገባኛል? አለችው ግራ በተጋባ ስሜት። አንድ አብሮኝ የሚኖር ጓደኛ አለኝ። ለታማኝነቱ ምንም ጥርጥር የለኝም። ለጊዜው አብሮኝ አይገኝም። ነገር ግን ከሁለት ሳምንት በኃላ ይመጣል። ወደ እዚህ ቤት ለሚመጣ ሰው ሁሉ የእሱ እጮኛ እንደሆንሽ እንድትናገሪ እፈልጋለው። አለ የልቡን ተንፍሶ። የእሷን ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ነው። የማታውቀው ሰው እጮኛ ነኝ ብሎ የመናገሩ ጥቅም ባይገባትም አንገቷን በእሺታ ነቀነቀች።
✍️✍️✍️✍️ ይቀጥላል

ክፍል አሰራ ሁለት
ስሙ ማን ይባላል? አለች። እጮኛዬ ነው ብላ የምትዋሸውን ሰው ስም እንኳን አለማወቋ እያስገረማት። ናትናኤል ይባላል። አለ አልአዛር ስሙን ስላልነገራት እያፈረ። ፈጠን ብሎ ከብፌው ላይ የተቀመጠውን የወጣት ፎቶ እያመለከተ ያ ነው አላት። ብሌን እጮኛዋ ነው የተባለው ሰው ፎቶ ላይ አፈጠጠች። ስንት አዲስ ነገሮችን በህይወቷ እንደምታይ አሰላሰለች። አዲስ ስም! አዲስ ኑሮ እንዲሁም እጮኛ ተፈጥሮላታል። ጊዜ የሚያመጣውን ከማየት ውጪ ሌላ አማራጭ ስለሌላት ሁሉንም በሽንፈት ተቀበለችው።
እዚህ ቤት ከመጣች ዛሬ አምስተኛ ቀኗ ነው። አልአዛር የሚወጣው ጠዋት የሚገባው ደግሞ ለአይን ያዝ ሲያደርግ ስለሆነ በዛ ቤት ውስጥ የወረራትን ብቸኝነት የሚጋራኝ ሰው ብላ ተመኘች። የሴት እንግዳ የለምና የወጥ ቤቱ አላፊ ከሆነች ሶስት ቀናት አስቆጥራለች። አልአዛር ሲመጣ ራት ከማቅረብ ውጪ በመሀላቸው የሚካሄደው የቃላት ልውውጥ በጣት የሚቆጠር ነው። በዛ በብቸኝነቷ መሀል ነው እንግዲህ በሩ የተንኳኳው። ለወትሮው አልአዛር በዚህ ሰአት አይመጣም። ናትናኤል ደግሞ ቢያንስ ግማሽ ሳምንት ይቀረዋል።
በሩን ስትከፍት ከፊት ለፊቷ የቆመችው ሴት ብሌንን ገረመመቻት። 'ማንን ፈለጉ?' አለች ብሌን በትህትና! ማንንስ ብፈልግ ምን አገባሽ? አንቺ ይልቅ ማነሽ? እኔን አባሮ አንቺን የመሰለችዋን አስቀያሚዋን አስገባ ደግሞ! ብሌንን ገፍተር አድርጋ ወደ ቤቱ አቀናች። ውስጥ ገብታ እስክትቀመጥ ድረስ ብሌን፤ ከኃላዋ ነበረች። ቆይ ግን አንቺ ማነሽ? አለች ብሌን በድፍረት። መጀመሪያ ያንቺን ማንነት ንገሪኝ አለች ትዝታ። ብሌን ጥያቄዋ በጥያቄ መመለሱ እሰጥ አገባ ውስጥ የሚከታቸው ስለመሰላት ቀልጠፍ ብላ ' መአዛ እባላለሁ የናቲ እጮኛ ነኝ አለች። የትዝታ ፊት በእፎይታ በራ ብሎ ዳግም ጠቆረ። ናትናኤል እጮኛ እንዳለው ሲናገር ሰምታ አታውቅም። ደግሞስ ናቲ ሴትን ከአንድ ቀን አዳር ውጪ መፈለግ የጀመረው መቼ ነው? ሊገለጥላት አልቻለም።
የናቲ እጮኛ አለቻት ፌዝ በተቀላቀለበት አንደበት። ይሄኔ አንዷን ወጣት አገባሻለው ብሎ ከእናቷ ጉያ አውጥቶ ጉድ ሰርቷት ይሆናል ብላ ወደ ብሌን ተመለከተች። ብሌንን ስታይ ግን በናቲ አይነት ወንድ የምትታለል አትመስልም። እውነትም ናቲ አብዷል ማለት ነው። አለች በልቧ! እኔ ደሞ ትዝታ እባላለሁ የአሊ እጮኛ ነኝ!አለች ትዝታ ነበርኩ ማለትን ትጠላለች።
ናቲ የት ነው? ስገባ አላየሁትም! ይሄን ስትናገር መጀመሪያ ወደነበረችበት የንቀት አነጋገር ተቀይራለች። ከቀናት በኃላ እመለሳለሁ ብሎ ከወጣ ሳምንት ሆነው። አለች ብሌን የሞት ሞቷን ውሸቷ እንዳይነቃባት ሰግታ። ታዲያ አንቺ እዚህ ምን ታደርጊያለሽ? ማለቴ ከሩቅ ነው የመጣሽው? በልቧ ግን ሞኚት እሱ ይሄኔ ከአንዷ ጋር እየቀበጠ ነው ስትል አሾፈች። አይ እዚሁ ነኝ ከቤተሰብ ተጋጭቼ መመለሱን ፈርቼ ነው!
ትዝታ ሁሌም ያሰበችው ነገር ልክ ሲሆን እንደምታደርገው አፏን በአንድ ጎን ከፈት አድርጋ የምፀት ሳቅ ሳቀችና እሺ እንግዲያውስ አሊ የት ነው? አለች። ብሌን ትዝታ የት ሊሆን እንደሚችል ታውቃለች ብላ በማሰብ ሱቅ ብሎ ነው የወጣው ምናልባት እዛ ይሆናል አለች! ትዝታ በሮብ ምድር አልአዛር ስራ መሄዱ ገረማት ምክንያቱም ካወቀችው ጊዜ አንስቶ ሮብ ለአላዛር የእረፍት ቀኑ ናት። አይ በቃ ነገ መጥቼ አየዋለው መጥታ ነበር ብለሽ ንገሪው ብላት ቆንጠር ቆንጠር እያለች ወጣች።
✍️✍️✍️✍️ይቀጥላል..

ክፍል አስራ ሶስት
ትዝታ ከቤት እንደወጣች ብሌን በእፎይታ ሶፋው ላይ ተወረወረች። እዮብ ቢሆን እንደዚች አይነቷን አይደለም ለጓደኝነት ለአይንም ቢሆን ይጠየፋት ነበር ስትል አሰበች። መልካቸው ብቻ ነው ለካ የሚመሳሰለው አለች በልቧ። ምንም ስለአልአዛር የግል ህይወት አያገባኝም! ግን ምን ሲሆን ከእንደዚች አይነቷ ጋር ሆነ? ብሌን ከቅሬታዋ በላይ የሚሰማት ብስጭት መንስኤውን አለማወቋ አሳሰባት። ምን አልባት አልአዛርን እንደ እዮብ ቆጥራው ይሆናል። ወይም የወንድሙ ውለታ ስለሱ እንድትጨነቅ አስገድዷትም ይሆናል። ብቻ ተበሳጭታለች። ማታ አልአዛር እስኪመጣ መታገስ አቃታት።
እንደምንም መሸና አልአዛር ቤት መጣ። እራት ካቀረበች በኃላ "ትዝታ የምትባል ሴት መጥታ ነበር።" እዚ ስታጣህ ሱቅ ይኖራል ብዬ ብነግራትም ነገ መጣለው ብላ ሄደች አለች በዝምታ የተዋጠውን ማዕድ በማደፍረስ። እና ምን አለችሽ? የሚያስቀይም ነገር ተናገረችሽ? ጥያቄውን አከታትሎ ጠየቃት። አይ ምንም አልተናገረችም የናትናኤል እጮኛ ነኝ ብዬ ስነግራት ያመነችኝ ትመስላለች ... ብሌን እናቷን ስትዋሻት ሁሌም ታውቅባት ነበር። ትዝታ ግን አለማወቋ አስደስቷታል።
አልአዛር የብሌን ትዝታን ማየት ረፍት ነሳው። የትዝታ መጥፎ ባህሪያቶች ብቻ ሳይሆን ብሌን ከነጭራሹ ከትዝታ ጋር የነበረውን ነገር ባታውቅበት ይመርጣል። ዛሬ ካለወትሮው ወደ ስራ ለምን እንደሄደ አሰበ "ሽሽት" አለ በሆዱ። እኮ ከምን? መልሶ ራሱን ጠየቀ። ከብሌን? እሱማ አይሆንም በሌላ ያሳበበው ስጋቱ እየተገለጠ ነው።
ጠዋት ይወጣል ማታ ይገባል። በሚገናኙበት ጊዜም ብዙም እንዲያወሩ አይፈልግም። የብሌን ትህትና መልክ አነጋገር ለወንዶች ቀዝቃዛ ወጥመድም ነው። በወጥመዱም ላለመያዝ ይሸሻል ግን ስሜቱ ባላወቀው መንገድ የተሸነፈ ይመስላል ወንድሙን እዮብን የከዳ ቃልኪዳኑን ያጠፈ ስሜት እስኪሰማው ያህል።
መሸሻ ፈለገ ከቤቱ የት ይሂድ? ብሌን ደግሞ እሷን ለአይኑ እንኳን የጠላት መስሏታል። ሊያናግራት አለመፈለጉ አይኖቹን ከእሷ ማሸሹ ለወንድሙ ሞት ተጠያቂ እሷ የሆነች አድርጎ ያሰበ መሰላት። ትክክል ነው ከኔ ውጪ ለእዮብ ሞት ተጠያቂ ማነው? እዮብን ስታስብ በፀፀት ልትሞት ትደርሳለች። ስለ እሱም ላለመስማት ላለማሰብ ጥረት አድርጋለች ግን ከጭንቅላቷ ሊወጣላት አልቻለም። ቀስ በቀስ ድባቴ ውስጥ መግባት ጀመረች። ቀን ላይ ስለነበራት ህይወት አሁን ስላለችበት ስለወደፊቷ በማሰብ ራሷን ታስጨንቃለች። መሽቶም አልአዛር ሲመጣ ከአንድ ሁለት ቃላት ውጪ ንግግር ስለማይኖራቸው የመሰልቸት የተጠያቂነት ስሜቷ አየለባት።

ይፈራል! ኸረ እንደሚስቴ አስቢና ባሰብሽበት ልዋል ይለኛል.... እንደ እናቱ እያሰብኩ ተቸግሮ እኮ ነው!
በልቶ ያልጠገበ፣ ተቀብቶ ያልወዛ ያህል ይሰማኛል። 'ትክ' ብዬ ሳየው የከሳ ይመስለኛል። ለነገሩ ዐይኔ ነው ያከሳው ዐይን ዐይኑን እያየሁት። የገረጣም የጠቆረም መልክ በአንድ ጊዜ ሰው እንዴት ያያል? እሱ ላይ ግን ይታየኛል።
እንስፍስፍ አንጀቴ ከአጋር ለወላጅ ይቀርባል። አድራጎቴ የእናት ነው። እንደሚስት እኮ ማሰብ እፈልጋለው። ግን እንዲህ አስብ እንዲህ በል አእምሮ አይባል።
... አለ አይደል ሲያመሽ ቀሙት፣ መቱት፣ ደበደቡት፣ ገደሉት ከሚል ጭንቀት ወጥቼ ያመሸው እያመነዘረ ነው ብል እኮ ደስ ይለኛል።
አዎ እሱም ብቻ ሳይሆን እኔም እፈራለሁ! ...በቃ ከስስቴ ቅናቴ አይሎ እንደ እኔ ሳይሆን ሁኚልኝ እንደሚለኝ ሚስቱ ቢያውለው እላለው።

ትላንትን መድገም እንዴት ያሰለቻል ነገን ደ'ሞ በተስፋ መኖር!
ኡፍፍፍፍ............
እሱ ምንሽ ነው? ብለው ቢጠይቁኝ መልሴ ሊሆን የሚችለው ዛሬ'ዬ የሚል ነው። አንተ እየኖርኩት ያለሁት ዛሬ ነህ። ትላንቴም ነገዬም እንድትሆን አልፈልግም።
ከትላንቴ ማህደር ሳገላብጥ የማገኘው ትዝታ ብቻ ነው። ያውም መጥፍ ትዝታ! ዘወር ብለው ቢያዩት የማይመለሱበት ትፋት! ታዲያ ምን ብዬ ነው ትላንቴ የማደርግህ?
በነገዬ አልተማመንም። ምን ይዞብኝ እንደሚመጣ አላውቅም። ምን አልባት ሊሰጠኝም ሊነሳኝም ይችላል ግን አላምነውም።
ስለዚህ አንተ ዛሬዬ ብቻ ሁንልኝ! ከእንቅልፌ ስነቃ እንደማያት ፀሐይ ፣ ሲመሽብኝ ደግሞ እንደምትተካው ጨረቃ አሁኔ ሁንልኝ እና ልኑርህ!

ሁሉም ሲያያት ለአልጋ የሚመኛት ሴት መሆን ስልችት ብሎኛል። ከስሜት ጡዘት በኃላ ጀርባ የሚሰጣት ሴት መሆኔ ደግሞ ስብርብር አድርጎኛል።
ደግሜ ደጋግሜ ራሴን ቀጥቼዋለው! ምርር ... ትክት ብሎኝ 'ሁለተኛ...' እርም ብዬ ምዬ ተገዝቼ ተመልሼበታለው፤ ተመላልሼበታለው!
ራሴን ታዝቤዋለው! ሰው እንዴት? ደግሞ ደጋግሞ ባቆሰለው ነገር ዳግም ለመቁሰል ይሄዳል?
የድሮዋ እኔን አጥቻታለው። ህሊናዬንም በመጠጥ ካላራስኩ የሚንቀሳቀስ ስጋ የለኝም። ለነገሩ የሚሰክር ነፍስ ሲኖረኝ አይደል!
መፈለግን እ'ኮ እፈልጋለሁ! መወደድን ከዛም ሲያልፍ መከበርን! አዝኜ ሳለቅስ የመጀመሪያዋን ማበሻ መሐረብ የሚሰጠኝን፣ የደስታዬ ልክ የለሽ ሳቅ የሚያስፈግገውን ፣ አቅም አጥቼ ስወድቅ ምርኩዝ የሚሆነኝን እናፍቃለው.... ግን ብዙ ርቀት ሳልሄድ ሽምቅቅ እልበታለሁ!
በፍቅር እቅፋት ፈውስ የሚሆነኝን ደረት ... ሀሴት ሲያስፈነድቀኝ ትኩስ ትንፋሼን ምጌው ከናፍሮቼን ከከናፍሮቹ የማገናኘውን እንጂ!
አሁንም .....
በቅንዝራም ዐይኖቹ አካላቴን የሚያራክሰውን ወንድ ነፍሴም ገላዬም ትፀየፋዋለች!
ቢሆንም..... ታጥቦ ጭቃ!