Telegram Group Search
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Eliyah Mahmoud
Video
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ከሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል የቀረበ የትምህርት እድል

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በተለያዩ አካባቢዎች ከሚሰጣቸው የንጽጽራዊ ሀይማኖት ስልጠናዎች በተጨማሪ፣ በአዲስ አበባ እና በሸገር ሲቲ የሚገኙ የተለያዩ መርከዞችና ኢስላማዊ የትምህርት ተቋማትን አወዳድሮ ከፊል የትምህርት እድል ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል።

የንጽጽር ትምህርት ስልጠናው ከትምህርታቸው ጎን ለጎን ለአንድ አመት ጊዜ የሚሰጥ ሲሆን ማዕከሉ ባዘጋጀው ስርአተ ትምህርት/Curriculum/ መሠረት በዘርፉ ልምድ ባላቸው ኡስታዞች አማካኝነት ይሰጣል።

በዚህ የትምህርት እድል ለመስጠት የታቀደው የመርከዞችና የትምህርት ተቋማት ብዛት 6 ሲሆን በዚህ ዘርፍ ተማሪዎቻቸውን ማብቃት ለሚፈልጉ ተቋማት ባስቀመጥነው መስፈርት መሠረት አወዳድረን እድሉን እንሰጣለን።

በዚህም መሠረት በተቋማችሁ ውስጥ የኃላፊነት ወይንም የውሳኔ ሰጭነት ሚና ያላችሁ ወንድምና እህቶች ብቻ ከዚህ በታች የተቀመጠውን ፎርም በመሙላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፦

https://bit.ly/4dvInRv

© ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል
ጸጋችን ብዙ ነበር ግን…
……
እጅዎ የጋገረችልዎ የዳጉሳ እንጎቻ ሌሎች ከሚጋግሩልዎ የማር እንጀራ በባህር አሸዋ ቁጥር ልክ ይበልጣል፡፡ ምንም ትቆምጥጥ የእጅዎ ትሩፋት የኾነችው ኩርማን እንጎቻ ከደጋ ማር በላይ ጣፋጭ ናት፡፡

ኑሮዎን በራሶ ልክ ሰፍተው ለራሶዎ እንዲሰፋዎ ማድረግ ይቻላል፡፡ ብዙዎች ኑሮአቸው የጠበባቸው በራሳቸው ልክ መስፋት ስላልቻሉና ሌሎችን አስገብተው በሌሎች ቁመትና ወርድ ልክ ስለሰፉት ነው፡፡

ወዳጄ አኹንም ልብ ይበሉ! እግር ምንም ያህል ቀጭን ይኹን ጨቀጨቁን ማሻገር ከቻለ፣ ሰዎች ዘንድ ካለ ጢያራ በላይ ነው፡፡ አንገትም ምንም ያሕል ይቅጠን ራስን መሸከም ከቻለ ስለምን እንደነ እንቶኔ አንገተ -ደንዳና አልኾንኩም ማለት ጸጋን ማማረር ነው፡፡

ሰው ጤነኛ ኾኖ ሳይጨነቅ ውሎ እያደረ፣ቀናቸው ሌታቸውም ጭንቀትና ስጋት በኾኑ “ባለጸጎች” መቅናቱ አላህ ለርሱ የዋለለትን ዓለማወቁን ወይም እጅግ ዝንጉ መኾኑን ያሳያል፡፡

ቃሩን በጌጥ ተሸልሞ ከሕዝቦች ፊት ሲታይ “ምን አለ እንደ ቃሩን ለኛም በኾነልን” ብለው የተመኙ ቃሩን ከነንብረቱ ምድር ስትውጠው ምኞታቸው ከንቱ እንደነበር ሳይረዱ አይቀርም፡፡

ወዳጄ ሐብት ማለት መብቃቃት ብቻ ነው፡፡ የራስ ዳሽን ያህል ቁልል ወርቅ ካላብቃቃ ከድሃ ሆድ አድራ የምታሞቀው ጭብጥ ቆሎ ብትሻል እንጂ አታንስም፡፡ ስንቶች የቆለሉት ወርቅ ተንዶ መጨረሻቸው ከፍቷል!? ስንቶችስ ምንም ሳይኖራቸው ረዥም ዘመን በጤንነትና በሐሴት ተመላልሰዋል!?

ባለበርካታ ሕንጻ ባለቤቶች ብዙ ክፍል ባለው ሕንጻቸው ውስጥ በርካታ ክፍሎቻቸውን ዘግተው እነርሱ ግን በአንዲት ነጠላ ክፍል ተከርችመው ያድራሉ፡፡ ያ ኹሉ ማንም ላይኖርበት የተገነባ ሕንጻ የስንቱን ምስኪን በር በዘጋ ነበር?! ስንትስ መስጂድ በየገጠሩ ማስገንባት በቻለ ነበር?

ይህ ዓይኑ ቀድሞ መጥገብ እንዳለበት የሚያምንና በአንድ ገበታ አስር ሳሕን በየዓይነቱ ካልቀረበ ያልበላ የሚመስለው መብላትን ስራ አድርጎ የተያያዘ ሕዝብ ካለው ላይ መስጠትን ደም ከመለገስ በላይ አግዝፎ እያየ በርካታ መሄጃ ያጡ ሙስሊም ወጣቶች ከነዲግሪያቸው በየ ጫቱ ቤቱ ቢውሉ ምን ይገርማል?

ትንሽ አለኝ ያለውም፣ በአካፋ እያዛቀ ያለውም፣ ለመዛቅ እየተንደረደረ ያለወም ኹሉም በምልዓት መዳረሻውን ዱንያና ፌሽታ ብቻ አድርጎ እያለ ኡማው ድልና የበላይትን ያገኛል ብሎ ማሰብ፣ ክው ካላ ጓል አፈር ላይ ጤፍ ማጨድን ከመመኘት ይከብዳል!!

ጥቂቶች ብቻ የሰበሰቡት ብዙኋኑ ግን ተኮርምቶ የሚያድርበት ተጨባጭ ላይ ኹነን እጅግ ቅንጡና መትረፍረፍ የበዛበት ኅይወት “አርኣያ” ከሚባሉና መድረኮች ያለነሱ የእህል አውድማ ናቸው የሚባልላቸው ሰዎች ዘንድ ስታይ በዚህ ልክ በዱንያ ባለመፈተንህ አላህን ካላመሰገንኽ ኢማንኽን ተጠራጠር፡፡

“ተዝኪየቱ አኑፉስ” እያሉ የሚሰብኩን አንደበቶች የዱንያ እሽቅድቅድም ውስጥ ገብተው ትላንት ውኃን እንደ ምግብ በሚበሉበት ወቅት (ድሃ በነበሩበት ወቅት) የነበሯቸውን የልብ ወዳጆች ኹሉ አዘቅዝቀው ሲመለከቱ ስታይ አኹንም በዚህ ልክ ባለመፈተንኽ ጌታኽን ካላመሰገንኽን ኢማንኽን ተጠራጠረው፡፡

ወዳጄ አላውቅ አልንና ነው እንጂ እኛ ዘንድ ያለው ጸጋ ኹሉ ከሌላው እጅጉን ይገዝፋል!!!
وإن تعدوا تعمة الله لا تحصوها
https://www.group-telegram.com/boost/E_M_ahmoud.com
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በሀድያ ዞን ሆሳዕናን ጨምሮ በርካታ የሚሽነሪ ት/ቤቶች አሉ። በዞኑ ያለው የሙስሊም ት/ቤት ግን አንድ ብቻ ነው። እሱም በሻሸጎ ወረዳ ቦኖሻ ከተማ የሚገኘው ኑር ት/ቤት ነው። በዚህ ት/ቤት በሚሽነሪ ት/ቤቶች ሊማሩ የነበሩ በርካታ ሙስሊም ልጆች ይማሩበታል።

ይህ ት/ቤት ግን በርካታ ወጭዎች ገጥመውት እየተንገዳገደ ይገኛል። ሁሉኑም ወጭዎች መሸፈን እንኳን ቢከብድ አሁን ላይ አንገብጋቢ ማነቆ የሆነባቸውን የመምህራን ደሞዝ ተባብረን እንድንሸፍንላቸው ለመማጸን ወደ እናንተ መጣሁ። የአንድ አመት የመምህራን ደሞዝ 600ሺ ብር ነው። ይህ በእርግጥ በአንድ ሰው ሊሸፈን ይገባው የነበረ ቢሆንም በአቅማችን ልክ ሁላችንም አኽለል ኸይር በመሆን እንድንሸፍነው እጠይቃችኃለው።

ከዚህ በታች የተቋሙን አካውንት አስቀምጣለሁ፣ ከ100 ብር ጀምሮ የአቅማችሁን በመነያት የኸይር ስራው ተጋሪ ይሁኑ፣ ከቻሉ ያስገቡበትን ደረሰኝ ኮሜንት ላይ በማስቀመጥ ለሌላውም መነሳሳት ይፍጠሩ፦

1000432023037
Bonosha Noor school
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/11/18 10:34:00
Back to Top
HTML Embed Code: