የቅዱሳን አባቶች ተግሳጽ እና ምክር
ይህን መፅሐፍ ብላ
ሕዝ ፫፥፩
መግቢያ
በቤተክርስቲያን ገድለ ቅዱሳን የሚጠናበት መስክ ዜና አበው ወይም ትምህርት አበው ይባላል።
የአበው ታሪክ የአበው ትምህርት ማለት ነው።
ግሪካውያን "PATROLOGY" ይሉታል። ፓተር አባት፣ፓቲሮን አበው ማለት ሲሆን ፓትሮሎጂ ማለትም ነገረ አበው፣ዜና አበው ማለት ነው።
ቅድስት ቤተክርስቲያን ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አንስቶ አያሌ ቅዱሳንን አፍርታለች። ቅዱሳን ሁሉ አንድ ሲሆንም፣ በክብራቸው፣በግብራቸውና በተልእኳቸው በስምሪታቸው ይለያያሉ።
ከዚህ የተነሳ የቅዱሳንን ሕይወት ማንበብና ማወቅ የሚገባው፣ከዚህ ዓለም ሳሉና ከዚህ ዓለም ርቀው በገድልናትሩፋት ፈጣሪያቸውን አስደስተው ለታላቅ ክብርና ፀጋ የበቁ የቅዱሳንን ሕይወት መጻፍና ማንበብ በዓለም ለምንኖርና ደካሞች ለሆን ለእኛ፦
1.ህይወታቸው የነገረ መለኮታዊ አስተምህሮ መገለጫና መታወቂያ ፍሬ ስለሆነ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ መንገዱን ያሳየናል ይረዳናል። ምክንያቱም የቅዱሳን ሕይወት በክርስቶስ ባለው ህይወት ከስሙ ጀምሮ ክርስቶስን የተሸከሙ፣የክርስቶስ ማደሪያዎች ናቸውና።
2.ሕይወታቸው ለእኛ አብነታችን ምሣሌአችን ስለሆነ እንዴት ማደግና መምሰል እንደምንችል ለማወቅ ሕይወታቸው በተግባር የተፈተነ ስለሆነ እነሱን መመልከት ስለሚገባ።/ በመሳሰሉት
3.የቅዱሳንን ሕይወት ስናነብ ያሳዩንን ምሣሌ በጥልቀት ስንገነዘብ ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ ብርታትንና ጥቅምን እናገኛለን።
@ZenaAbewPATROLOGY

✥ ቅዱስ ባስልዩስ በትንዃ እስያ ውስጥ በምትገኘው የአገረ ቀጰዶቅያ ዋና ከተማ በሆነችው በቂሳሪያ በ329 ዓ.ም መገባደጃ ላይ ከአባቱ ከኤስድሮስ እና ከእናቱ ከኤማሊያ ተወለደ።ይህ ቤተሰብ በክርስትና ህይወት የታነጸ፣በአገሩ ህዝብ ዘንድ በስነ-ምግባሩ የተከበረ ሲሆን በዓለማዊ ሀብት ረገድም ባለፀጋ ነበር።ቤተሰቡ በአስር ልጆች በረከት የተጐበኘ ሲሆን አስቀድሞ በሞት ከተለየው ከአንዱ በስተቀር አምስቱ ሴቶችና አራቱ ወንዶች አድገው ለወግ ለማዕረግ በቅተዋል። የቤተሰቡ የበኩር ልጆች የሆነችው ማክሪና፣ባስልዮስ/የቂሳርያ ሊቀ-ጳጳስ/ጎርጎርዮስ /የኑሲስ ኤጲስ ቆጳስ/ እና ጴጥሮስ /የሰባቱ ኤጲስ ቆጶስ/ እንደ ወላጆቻቸውና ሴት አያታቸው ቅድስት ማክሪና ሁሉ ለቅድስናና ለክብር ሲበቁ ሌሎቹም ልጆች በተቀደሰ ክርስቲያናዊ ጋብቻ በህግ ህይወት ተወስነው እንደኖሩ ጎርጎርዩስ ከኑሲስ ወንድማቸው መስክሯል።
✥ ቅዱስ ባስልዩስ በ362 ዲቁና ከአውሳቤዩስ ሊቀ-ጳጳስ ደግሞ ቅድስናን ተቀበለ። ሰኔ 14 ቀን በ370 ዓ.ም በ41 ዓመቱ የቂሳርያ መንበር ሊቀ-ጳጳስ በመሆን ተሾመ። ቅዱስ ባስልዩስ በዘመኑ የተነሱትን መናፍቃን ለመመከት ብርቱ ትግል አድርጓል። በ379 ዓ.ም በሃምሳ አመቱ በስጋ አርፏል ይህ ቅዱስ ባስልዩስ ቤተክርስቲያን ከእግዚአብሔር የተሰጣት የቁስሏና የጉዳቷ ጠጋኝ ሐኪም ነበር።
በረከቱ ትድረሰን ፀሎቱ ትጠብቀን።

ባስልዩስ ዘቂሣርያ “ቤተ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር የተሰጣት
የጉዳቷ ጠጋኝ ሐኪም” በማለት የሚጠራው ሊቁ ቅዱስ
አትናቴዎስ የክርስትና እምነት በመላው ዓለም እንዲስፋፋና
ተጠብቆ እንዲቆይ ያደረገው ከትምህርቱና ከተጋድሎው
በተጨማሪ ክፉ ሰዎችና ለአገልግሎቱ እንቅፋት ለመሆን የተዘጋጁ ሰዎች ወደ አትናቴዎስ በቀረቡበት ሰዓት እንዲህ ይሉት ነበር
“አትናቴዎስ ሆይ ዓለም ሁሉ ጠላህ “ይሉት ነበር፡፡ሊቁ ቅዱስ
አትናቴዎስም“እኔም ዓለሙን አልወደውም ነገር ግን የሚጠሉኝን
ሰዎች ግን እወዳቸዋለሁ በማለት ሰይጣንንና ከፉ ተናጋሪዎችን
ያሳፍራቸው ነበር፡፡እስከ ሕይወቱ ፍጻሜም የሚጠሉትን በማፍቀር
ና በመጸለይ የእግዚአብሔርን ልጅነት እንዲያገኙ የሕግ ፍጻሜ
የሆነውን ፍቅርን ገንዘብ እንዲያደርጉ ያለመታከት ያገልግላቸው
ነበር፡፡( ስንክሳር ግንቦት 7) ይህንን ታሪክ በእውነት ተወዳጆች
ሆይ ሳነብ እጅግ ተገረምኩ ይህ ታላቅ አባት ምን ያህል
መምህሩን ጌታውን እንደመሰለ አስቡ እኛ ክርስቲያኖች ምንም
አይነት የቀና ሃይማኖት ቢኖረን በፍቅር ካልፈጸምነው ለጽድቅ
እንደማንበቃ መታወቅ አለበት፡፡ዛሬ የአዳም ልጆች ሁሉ
የተተበተቡባው የችግር መንገዶች ሁሉ በፍቅር በአንድ አሳብ
በመሆንእግዚአብሔርን ቢጠይቁት መልስ ያገኛሉ፡፡ የእውቀት
ባለቤት የጥበብ መገኛ
ሕያው እግዚአሔር በፍቅር እንድናገለግል ያስፈልጋል፡፡የቂመኛ
፤የበቀለኛ ጸሎቱ ከእሾህ መሃል እንደወደቀ ዘር ነው፡፡እኛም
በራሳችን የሃይማኖት ቁር ደፍተን ወገብ ልቡናችንን በንጽሕና ዝናር
ታጥቀን ኃይለ መንፈስ ቅዱስን እንደ ሰይፍ መዘን የሕግ ሁሉ
ፍጻሜ የሆነውን ፍቅርን እንደ ጽሩር ለብስን መንግሥቱን
እንድንወርስ አምላካችን ይርዳን፡አሜን.
ዲ/ን ጌታመሳይ
ኃይለሚካኤል ነሐሴ 25/2010

ባልና ሚስት በሚኖሩበት አንድ ቤት ውስጥ ከመሸ በራቸው
ይንኳኳል ሚስት ልመክፈት ትሄዳለች ክፕዛም ባየችው ነገር
በጣም ተገረማለች .3ነጫጭ ሽበት ያለባቸው የሚያማምሩ
ባለግርማ ሞገስ ሽማግሌዎች ነበሩ ።አቤት ግቡ ምን ፈልጋቹ
ነው አለቻቸው 3ታችንም አንገባም አንዳችን ነን የምንገባው
እራሳችን እናስተዋውቅሽ አሉና ራሳቸውን ማስተዋወቅ ጀመሩ
1 ፦ 1ኛው ስኬት እባላለው እኔ ቤትሽ ከገባው አሳብሽ ሁሉ
ይሳካል አላት
2ተኛ ገንዘብ እባላለው እኔ ቤትሽ ክገባው ችግር የሚባል
አይኖርም አላት
3ተኛው ፍቅር እባላለው ፍቅር ማብራሪያ የለውም አላት ከዛ
ሚስት ባለቤቷን ላማክር ብላ ወድ ውስጥ ገባችና ልፕባለቤቷ
ስትነግረው በነገሩ ተደንቆ እንዲህ አለ በእውነቱ ይሄ እድል
ሊያመልጠን አይገባም ገንዘብን የሚያክል ነገር ደጅ ቆሞ
መወያየት ግፍ ነው .ሰርቼ ከሰው በታች የሆንኩት ገንዘብ
ሰለሌለኝ ነው እና ፈጠን በይ ገንዘብን ወደቤታችን እንዲገባ
..ንገሪው አላት ሚስትየውም በሀሳቡ ተስማምታ ገንዘብን
ልትጠራው ስትል ልጇ እንዲ አላት እማዬ ገንዘብ ገብቶ ...አባዬ
እንደለመደው ማታ ማታ ከሚደበድብሽ ፍቅር ገብቶ ሰላምሽን
ብታገኚ አይሻልም ?አላት እሷም በልጇ ሀሳብ ተደስታ ባልየውን
ፍቅር ካልገባ ብላ ሞገተቹ በመጨረሻም ፍቅር እንዲገባ
ወስነው ወደ ሽማግሌዎች ሄዱና ፍቅር የተባልከው ሰው
ወደቤታችን ግባ ይሉታል።እሱም ተከትሏቸው ይገባል ባልና
ሚስቱም።ዞር ብለው ሲያዩ 3ቱም።ሰዎች ቤት ገብተው ቆመዋል
ባልየው ደንግጦ እኛ በቤታችን እንዲገባ ያልነው ፍቅርን እኮ
ነው አለ ...ከሽማግሌዎቹም .አንዱ ዞር አለና ልክ ብለሀል ነገር
ግን ፍቅር ካለ ስኬት አለ ፍቅር ካለ።ገንዘብ አለ። በማለት
3ቱም።ወደቤታቸው ገቡ ፍቅር የሆነው ክርስቶስ ወደቤታችን
ሲገባ መልካም የሆኑ በሙሉ አብረው ይገባሉ
አሜን ጌታ ሆይ ወደቤቴ ግባ ...
#Share ማድረግ አትርሱ።
JOIN 👇👇👇👇

ብሒለ አበው!
1 ‹ራስህን በሐሰት አትውቀስ ራስን መክሰስ ትህትና አይደለም ታላቁ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ
መታገስ ነው።›› /ቅዱስ ስራፕዮን/
2 ‹‹የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትስራው ከሰራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ።›› /መጽሐፈ ምክር/
3 ‹‹አንደበቱን ከቧልት ከሐሜት ያየውንም ሚስጥር
ከመናገር የሚከለከል ሰው ልቦናውን ከኀልዮ ኃጥያት
ያርቀዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/
4 ‹‹ ጸጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እንዳታጣ።›› /ማር ይስሐቅ/
5 ‹‹ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ‹ጥበብ ይለየዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/
6 ‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ።›› /አባ
እንጦንስ/
7 ‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን
ይቻልናል።›› /ቅዱስ አትናቴዎስ/
8 ‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል።›› /ቅዱስ ሚናስ/
9 ‹‹በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና።›› /ታላቁ አባ መቃርስ/
10 ‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ
በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም።›› /ቅዱስ አርሳንዮስ/
11 ‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል።›› /ቅዱስ
እንድርያስ/
12 ‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው
ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ
መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን።›› /አባ አብርሃም
መፍቀሬ ነዳያን/
13 ‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው።›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/
14 ‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ።›› /ብፁዕ አቡነ
ጎርጎርዮስ ካልዕ/
15 ‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ
እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር።›› /ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ/
16 ‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል።›› /ቅዱስ እንጦስ/
በረከተ ቅዱሳን አበው አይለየን።
አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

ምክረ አበው
“እምነት አለኝ” ብሎ ምግባር የሌለው ሰውና፥ “ምግባር አለኝ” ብሎ እምነት የሌለው ሰው እኩል ናቸው፤ ኹለቱም መንግሥተ ሰማያት አይገቡም፡፡
ስለዚህ “እምነት አለን” ብለን ልል ዘሊላን አንኹን ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላልና፡- “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም” (ማቴ.7፡21)፡፡
ስለዚህ እምነት እንደሌላቸው ሰዎች ከመንግሥተ ሰማያት ውፁአን እንዳንኾን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ነቅተን እንሥራ፡፡ ምግባር ትሩፋትን ተግተን እንሥራ፡፡ አምነን ልጅነትን ከተቀበልን በኋላ ልጅነታችንን አጽንተን የምንጠብቀው፣ ርስቱንና መንግሥቱንም የምንወርሰው ይህን ያደረግን እንደ ኾነ ነውና ነቅተን እንሥራ፡፡
እኛ ሥራ ሠርተን አንበቃምና ጽዋ ተርታችን ዕድል ፈንታችን ይህ ይኾን ዘንድ ከባሕርይ አባ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነቱ፣ ኃይሉና ክብሩ አንድ የሚኾን ጌታችንና መድኃኒታችን በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ ይርዳን፤ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን!!!
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ብሒለ አበው †††
• “ቂመኛ ሰው ሥጋ የለበሰ ሰይጣን ነው፡፡” /አረጋዊ መንፈሳዊ/
• ስትሰጥ፡- “በዝናብ ያበቀለው በፀሐይ ያበሰለው
የእግዚአብሔር ገንዘብ ነው” ብለኽ በትሕትና መጽውት፡፡ /ማር
ይስሐቅ/
• አንድ ወንድም አባ ሲዞስን፡- “አባ! ወድቂያለኹና ምን ላድርግ?”
ብሎ ጠየቃቸው፡፡ ርሳቸውም “እንደገና ተነሥ” ሲሉ መለሱለት፡፡
ያም ወንድም “መልሼ ብነሣም እንደገና ወድቅኁ” አላቸው፡፡
“እንደገና ተነሣ” ብለው ነገሩት፡፡ “ለምን ያኽል ጊዜ?” ሲል
ጠየቃቸው፡፡ “ወይ በጽድቅ አሊያም በኀጢአት እስክትሸነፍ ድረስ፡፡
ማንም ሰው የሚፈረድበት በመጨረሻ በተገኘበት ኹኔታ ላይ
ነውና፡፡”
• አንድ ወጣኒ (ዠማሪ) አባ ሲዞስን “አባ! በቀድሞ ዘመን ሰይጣን
አኹን እኛን በሚፈትንበት ኹኔታ ሰዎችን ይፈትን ነበርን” ሲል
ጠየቃቸው፡፡ ርሳቸውም “ዛሬ ብሶበታል፤ ምክንያቱም ዘመኑ
እያለቀ በመኾኑ በጣም ተበሳጭቷልና” አሉት፡፡
• “እናት ልጇን ዳዴ ስታስለምደው አስቀድማ እጁን ትይዘዋለች፡፡
እንዲሔድም ታደፋፍረዋለች፡፡ ትንሽ መሔድ ሲዠምር
ትለቀዋለች፡፡ ትልቀቀው እንጂ ልቧ ሐሳቧ ኹሉ ግን ከልጇ ጋር
ነው፡፡ ሊወድቅ ሲል ፈጠን ብላ ትደግፏለች፡፡ እግዚአብሔርም
ለእኛ ለልጆቹ እንደዚኽ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በእኛ እይታ ክፉ
በሚመስሉ ኹኔታዎች እንድናልፍ ይፈቅዳል፤ ወርቅ ወርቅነቱ
ይታወቅ ዘንድ በእሳት እንዲያልፍ፡፡ ነገር ግን ልክ እንደዚያች
እናት በቅርብ ርቀት ኾኖ ይከታተለናል፡፡ ሐሳቡ ልቡ ኹሉ ከእኛ
አይለይም፡፡ አንዳንድ ጊዜም ልንወድቅ እንችላለን፡፡ ነገር ግን
መልሶ ያነሣናል፡፡ እዚኽ ጋር መጠንቀቅ ያለብን ቢኖር በዚኹ
የልምምድ ጊዜ ሰይጣን ያንን ኹናቴ ተጠቅሞ በክፉ ዐይን
እንድናየው እንዳያስደርገን ብቻ ነው፡፡” ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
• ከዕለታት በአንዲቱ ቀን አባ ጴሜን ስለ ዮሐንስ ሐፂር ሲናገር
እንዲኽ አለ፡- ዮሐንስ ሐፂር ፆርን ኹሉ ከርሱ እንዲያርቅለትና
በሕይወቱ ምንም የሚያስቸግረው ነገር እንዳይኖር ወደ
እግዚአብሔር አጥብቆ ጸለየ፡፡ እግዚአብሔርም የልቡን
ፈጸመለት፡፡ ይኽንንም ለአንድ ሽማግሌ እንዲኽ ሲል
አጫወታቸው፡- “አኹን ጠላት ስለሌለኝ ሰላምን አግኝቻለኁ፡፡”
ሽማግሌው ግን አዘኑና፥ መልሰው እንዲኽ አሉት፡- “ልጄ! አኹንኑ
እግዚአብሔር ፈተና ያመጣብኅ ዘንድ ጸልይ፡፡ ትሕትናን ገንዘብ
የምታደርገው ፈተና ሲገጥምኅ ነው፡፡ በመንፈስ እየጐለመስክ
የምትሔደው ፈተና የገጠመኅ እንደኾነ ነው፡፡” ከዚኽ በኋላ
ዮሐንስ ሐፂር እግዚአብሔርን ማለደው፤ እግዚአብሔርም ሰማውና
ፈተናውን ዳግም አመጣለት፡፡ ነገር ግን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ
ፈተናው ይርቅለት ዘንድ ጸልዮ አያውቅም፤ “አቤቱ በተጋድሎዬ
እበረታ ዘንድ ጽናትን ስጠኝ” ይላል እንጂ፡፡
ሼር ማድረግ አትርሱ።