Telegram Group & Telegram Channel
5⃣ መኽረጃቸዉ ስንት ነዉ ?

↔️መኽረጅ ማለት በቋንቋ መዉጫ ቦታ ማለት ሲሆን በተጅዊድ ምሁራን ገለፃ ፊደሎች የሚወጡበት ግልፅ የሚሆኑበት & ከሌላዉ ፊደል የሚለዩበት ማለት ነዉ።
↔️የፊደላት መዉጫ ቦታዎች ስንት ናቸው? በሚለዉ በተጅዊድ ምሁራኖች ዘንድ የተለያየ አቋም ቢኖርም በትክክለኛዉ አተያየት  አስራ ሰባት (17)  ናቸዉ ።
↔️ይህም አቋም የኢማም ሙሀመድ ኢብኑል ጀዘሪ ረሂመሁላህ ነዉ።
➡️እነዚህን 17 መዉጫዎች በ5  ዋና ዋና ጠቅላላ መዉጫ ተካተዉ እናገኛቸዋለን ። 
5ቶቹ ጠቅላላ መዉጫዎች (መኻሪጁል አማህ) የሚባሉት:-
1⃣አል-ጀዉፍ   الجوف  
2⃣አል-ሐልቅ  الحلق
3⃣አል-ሊሳን اللسان
4⃣አሽ-ሸፈታን الشفتان
5⃣አል-ኸይሹም  الخيشوم
     
        1⃣አልጀዉፍ   الجوف
➡️ጀዉፍ ማለት በቋንቋ ባዶ ቦታ ማለት ሲሆን በተጅዊድ ሙሁራን ገለፃ  የአፍና የጉሮሮ ባዶ(ክፍት)  ቦታ ነዉ ።
   1⃣ከዚህ ቦታ ሶስት ፊደሎች ይወጣሉ።
1,አሊፍ (ا)  ስኩን ሆና ከፊቷ ፈትሀ ከመጣ
2,ዋዉ (و) ሱኩን  ሆና ከፊቷ ደማ ከመጣ
3,ያ  (ي) ሱኩን   ሆና ከፊቷ ከስራ ከመጣ
    እነዚህ 3ቶቹ የመድ ፊደሎች ሁሩፉል
ጀዉፊያ  በመባል ይታወቃሉ ።

          2⃣አል ሐልቅ  الحلق
➡️አል-ሐልቅ ጉሮሮ ማለት ሲሆን በዚህ ክፍል 3 መዉጫ ቦታ ሲኖረዉ ስድስት (6)  ፊደሎች ይወጣሉ።
   2⃣1.አቅሰል ሐልቅ / ከጉሮሮ ስር ወይም ሩቁ  የጉሮሮ  ክፍል ء እና ه ይወጣሉ።
   3⃣2 ወሰጠል ሐልቅ /ከጉሮሮ መካከል ع እና            ح ይወጣሉ።
   4⃣3 አድነል ሐልቅ /ከጉሮሮ ጫፍ  ወይም በአፍ በኩል ያለዉ ቅርብ የጉሮሮ ክፍል   غ እና  خ  ይወጣሉ።
 እነዚህ 6 ፊደሎች ሁሩፉል ሐልቂየህ ( የጉሮሮ ፊደሎች ) በመባል ይታወቃሉ።

         3⃣አል ሊሳን اللسان
 ➡️ሊሳን /ምላስ/ ማለት ሲሆን አራት ክፍሎች አሉት። በእነዚህ አራት ክፍሎች አስር(10) መዉጫዎች ይገኛሉ። በአስሩ መዉጫዎች አስራ ስምንት (18) ፊደሎች ይወጣሉ።
    1, አቅሰ-ሊሳን :- ከጉሮሮ ከፍ ብሎ ለአፍ ርቆ የሚገኝ የምላስ ክፍል ሲሆን ሁለት መዉጫዎች አሉት ።
5⃣1.የ ق  እና
6⃣የ  ك    መዉጫ  
2.ወሰጠ ሊሳን :- መካከለኛዉ የምላስ ክፍል ሲሆን  ይህ ክፍል አንድ መዉጫ ቦታ ብቻ ሲኖረዉ (3) ፊደሎች ይወጣሉ።
7⃣-የ  ج ፣ የ ش እና  የመድ ፊደል ያልሆነችዉ  የ ي  
 ↔️ 3ቱ ፊደሎች ሁሩፉል ሸጀሪያህ በመባል ይታወቃሉ።
8⃣3.ሓፈተይል ሊሳን :-የምላስ ጎኖች ማለት ሲሆን ሁለት መውጫዎቻ አሉት።
  የ  ض እና
  የ   ل 
9⃣4.ጠረፈ ሊሳን :- የምላስ ጫፍ ማለት ሲሆን  በጠረፈ ሊሳን አምስት (5) መዉጫዎች  ያሉት ሲሆን  አስራ አንድ (11) ፊደሎች  ይወጡበታል ።
  1⃣0⃣1- የ  ن መዉጫ 
  1⃣1⃣2- የ  ر መዉጫ
  1⃣2⃣3- የ ط د ت   መዉጫ
  1⃣3⃣4- የ ص س ز  መዉጫ 
  1⃣4⃣5- የ ظ ذ ث   መዉጫ

          4⃣አሽ-ሸፈታን الشفتان:-
ሸፈታን ማለት ሁለት ከንፈሮች ማለት ሲሆን   ይህ መኽረጅ ሁለት መዉጫዎች ሲኖሩት አራት(4) ፊደሎች ይወጡበታል።
1⃣5⃣1, በጥኑ ሸፋ (የከንፈር ሆድ) - የ ف መዉጫ
1⃣6⃣2, ሸፈታን (ሁለቱ ከንፈሮች )  የ م ب و    መዉጫ

        5⃣አል-ኸይሹም  الخيشوم
  አል ኸይሹም ማለት ኮሾኮሾ ( ሰርን ) ማለት ሲሆን የአፍንጫ ሩቅ ክፍል ወይም የዉስጠኛዉ የአፍ ክፍል ጋ የሚያገናኘዉ የአፍንጫ ቀዳዳዉ ክፍል ነዉ። 
1⃣7⃣ይህም አንድ መዉጫ ያለዉ ሲሆን በዚህ ቦታ *#ጉና* ዜማ ይወጣል።
  ➡️5 ቶቹ ዋና ዋና ጠቅላላ መዉጫዎች እና በስሮቻቸዉ ያሉ  17  መዉጫዎች ይሄን ይመስላሉ።የበለጠ አንድ በአንድ ኢንሻአላህ ወደፊት የምናያቸዉ ይሆናል።

  6⃣ሁሌም የሚወፍሩ ፊደሎች እነማን ናቸዉ?
    ሁሌም የሚወፍሩ የአረብኛ ፊደሎች  የእስቲእላእ ባህሪ ያላቸዉ ፊደሎች ናቸዉ።
  ሁሩፉል ሙፈኸማ ወይም ሁሩፉል ኢስቲእላእ በመባል ይታወቃሉ ።
     ↗️እነሱም ሰባት ናቸዉ ።
خ ص ض غ ط ق ظ  
  በግጥም
  خُصَّ ضَغْطٍ قِظْ   ከሚለዉ ስንኝ ይካተታሉ ።
  ↔️እነዚህ 7ፊደሎች በማንኛዉም ሁኔታ አወፍረን ነዉ የምናነባቸዉ  ማለትም በፈትሀም፣በከስሯም፣በደማም እና በሱኩንም ጊዜ የዉፍረት ደረጃቸዉ ቢለያይም ምንጊዜም ይወፍራሉ።  
  ↔️ከነዚህ ከ7ቱ አራቱ(4) የኢጥባቅ ባህሪ ያላቸዉ በጣም ይወፍራሉ ።
ط ض ص ظ  
ከዛም
ق غ خ

እንደ አጠቃላይ የሚወፍሩ ፊደሎች በደረጃ ሲቀመጡ
  ⓵ط⓶ ض⓷ ص⓸ ظ
ق⁵ غ ⁶ خ⁷
ሁሉም ዉፍረታቸዉ ደረጃ ያለዉ ሲሆን  በ7ትም በ5ትም ይከፍሉታል  ። ለጀማሪዎች ቀለል እንዲል 5ቱን እንይ:- ኢብኑል ጀዘሪ ረህመቱላሂ አለይህ "አት-ተምሂድ ፊዒልሚ ተጅዊድ" በተሰኘዉ ኪታባቸዉ ያስቀመጡት 5 የዉፍረት ደረጃዎች አሉ።
*⃣ከ7ቱ የሚወፍሩ ፊደሎች አንዱ ፊደል*⃣
   1⃣ ፈትሀ ሆኖ  ከሱ ቀጥሎ አሊፍ ሱኩን ከመጣ :-قال
ከق  ቀጥሎ አሊፍ ሱኩን ا  መጥቷል  
   2⃣ ፈትሀ ብቻ ሲሆን  ማለት አሊፍ ሱኩን ከሱ በኋላ ካልመጣ:-  وَقَبَ 
  እዚህ ላይ ق ፈትሀ ነዉ ቀጥሎት አሊፍ ሱኩን የለም ።
  3⃣ ደማ ሲሆን:-    صُرِفَتْ 
     ከ ص ላይ ደማ አለ።

   4⃣ ሱኩን ሲሆን :-   يَطْبَعُ 
      ከ(ጧ) ط ላይ ሱኩን አለ

   5⃣ከስሯ ሲሆን:-   قِيلَ  
       ከ ق ላይ ከስራ አለ
   ↔️የ7ቱም ሁሩፉል ሙፈኸማ የዉፍረት  ደረጃቸዉ ከ1⃣ _5⃣  ይህን ይመስላል። ስንቀራ  ሁሉንም ከላይ ባየነዉ ቅደም ተከተል ልክ ነዉ የምናወፍራቸዉ ።

   7⃣ አንዳንዴ የሚወፍሩ አንዳንዴ የሚቀጥኑ ፊደሎች እነማን ናቸዉ?
   ➡️የመቅጠን እና የመወፈር ባህሪ ያላቸዉ ፊደሎች ከሁሩፉል እስቲፋል ናቸዉ  ግን በተለያየ ምክንያት አንዳንዴ ሊወፍሩ ይችላሉ። እነሱም 3 ናቸዉ :- ا  ل  ر 
↗️  ➊ አሊፍ  (ا)
     አሊፍ ሱኩን  ፈትሀን የያዘ ፊደል ተከትላ የምትመጣ ስትሆን ከሚቀጥኑ ፊደሎች በኋላ ከመጣች ትቀጥናለች። ከሚወፋሩ ፊደሎች በኋላ ከመጣች ትወፍራለች ። 
 ↪️በሚቀጥንበት ጊዜ  ለምሳሌ:- ሱረቱል መሠድ አያ 3 መጨረሻ ላይ  كَانَ تَوَّابًا  ከ ك ቀጥሎ አሊፍ (ا)  መጥቷል ك  ከሚቀጥኑ ፊደሎች ስለሆነ አሊፍን   ا እናቀጥናታለን ማለት ነዉ።ከ و ቀጥሎ አሊፍ (ا) መጥቷል ዋዉ ከሚቀጥኑ ፊደሎች ስለሆነ  አሊፍን  እናቀጥናታለን ።
 ↪️በምወፍርበት ምሳሌ:- ሱረቱል ቃሪአህ አያ አንድ ٱلْقَارِعَةُ   ስንል ከ ق ቀጥላ የመጣችዉ አሊፍ( ا) ق ከሚወፍሩ ፊደሎች ስለሆነ  ትወፍራለች::  
        ↗️➋ላም (ل)
 ላም ምንጊዜም ቀጥነዉ ከሚነበቡ ፊደሎች ዉስጥ አንዷ ብትሆንም  አላህ (الله )& اللهم አላሁመ)  ከሚለዉ ቃል ላይ ብቻ ስመጣ ወፍራና ቀጥና ትነበባለች። 
   ↪️ላም (ل) የሚወፍርበት ሁኔታ
1⃣,  አላህ (الله ) ከሚለዉ ቃል ቀድሞት የመጣዉ ፊደል  ፈትሀ እና ደማ ከሆነ ላሟ(ل)  ተወፍራ ትነበባለች። 
ምሳሌ :- በፈትሀ  ሱረቱል ኢኽላስ ላይ قُلْ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ   ስንል الله  ከሚለው በፊት ያለችው ፊደል ዋው (و) ስለሆነች ላሟ (ل) ተወፍሮ ይነበባል::

©©©©

group-telegram.com/quranlife01/226
Create:
Last Update:

BY Quran Life

Warning: Undefined variable $i in /var/www/group-telegram/post.php on line 260

Share with your friend now:
group-telegram.com/quranlife01/226

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

The company maintains that it cannot act against individual or group chats, which are “private amongst their participants,” but it will respond to requests in relation to sticker sets, channels and bots which are publicly available. During the invasion of Ukraine, Pavel Durov has wrestled with this issue a lot more prominently than he has before. Channels like Donbass Insider and Bellum Acta, as reported by Foreign Policy, started pumping out pro-Russian propaganda as the invasion began. So much so that the Ukrainian National Security and Defense Council issued a statement labeling which accounts are Russian-backed. Ukrainian officials, in potential violation of the Geneva Convention, have shared imagery of dead and captured Russian soldiers on the platform. In December 2021, Sebi officials had conducted a search and seizure operation at the premises of certain persons carrying out similar manipulative activities through Telegram channels. Stocks closed in the red Friday as investors weighed upbeat remarks from Russian President Vladimir Putin about diplomatic discussions with Ukraine against a weaker-than-expected print on U.S. consumer sentiment. WhatsApp, a rival messaging platform, introduced some measures to counter disinformation when Covid-19 was first sweeping the world. After fleeing Russia, the brothers founded Telegram as a way to communicate outside the Kremlin's orbit. They now run it from Dubai, and Pavel Durov says it has more than 500 million monthly active users.
from us

Telegram Quran Life
FROM American