Telegram Group Search
🚨 የጥበቃ ጊዜው አብቅቷል — Big 5 Construct Ethiopia እና የEast Africa Infrastructure and Water Expo የንግድ ትርዒት ነገ ይከፈታል!

በኢትዮጵያ ትልቁ በሆነውና ከሰኔ 19–21፣ 2017 ዓ.ም ድረስ በሚሊኒየም አዳራሽ፣ አዲስ አበባ በሚከናወነው የኮንስትራክሽን እና የመሠረተ ልማት የንግድ ትርዒት ላይ ተሳታፊ ይሁኑ።

ከ10,000+ ባለሙያዎች እና ልምድ ያላቸው ተቋማት
ከ20 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ከ180+ ተሳታፊ ኩባንያዎች
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዕይታ የሚቀርቡ አዳዲስ ምርቶች
20+ የCPD ማረጋገጫ ያላቸው ትምህርታዊ ቆይታዎች በኮንስትራክሽን፣ መሠረተ ልማት እና ውኃ ጉዳዮች ላይ
አስደሳች እና አሳታፊ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች

ያስታውሱ! ይህ ዓውደ ርዕይ፣ ለኮንስትራክሽን እና ለመሠረተ ልማት ባለሙያዎች የቀረበ ልዩ ዕድል ነው!

አሁኑኑ #በነፃ ይመዝገቡ፦
👉 https://www.big5constructethiopia.com/Tikvah_Ethiopia
📅 ሰኔ 19–21፣ 2017 ዓ.ም
📍 ሚሊኒየም አዳራሽ፣ አዲስ አበባ
ዋሪት ፈርኒቸር !

ክቡራን ደንበኞቻችን ምቾታቸውን እና ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶቻችንን እንደሁልጊዜው እርሶን ይጠብቃሉ ይምጡና ይሸምቱ!

ለእያንዳንዱ የሕይወት ምዕራፍ ምቾት የሚሰጡ
🚼የሕፃናት ትራሶች
🤰🏽የእርግዝና ትራስ
ቢን ባግ
🌊የውሃ ማጣሪያዎች

ወደ ማሳያ ክፍሎቻችንን በመምጣት ይጎብኙን !
* 22 - ዋሪት ህንፃ
* ጉርድ ሾላ - ሴንቸሪ ሞል
* ለቡ - ቫርኔሮ ፊት ለፊት
* አዳማ - ሶረቲ ሞል * ቡልቡላ- ልዑል ህንፃ ፊት ለፊት * ፒያሳ- ፍርዱ ኮሜርሻል
*ወሎ ሰፈር- Ethiolife life real estate
ዋሪት ፈርኒቸር
ትክክለኛ ምርጫ!
ለተጨማሪ መረጃ: ☎️ 0911210706 / 07
#ኢትዮጵያ🇪🇹

ኢትዮጵያ የአለማቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ቁልፍ የህዝብ መረጃ ልውውጥ ስርዓት የአባልነት ማረጋገጫ ተቀበለች።

ኢትዮጵያ 105 አገራትን ባቀፈው የአለማቀፉ አቪዬሽን ድርጅት ቁልፍ የህዝብ መረጃ ልውውጥ ስርዓት (PKD) አባል መሆኗን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ከተቋሙ ዋና መቀመጫ ከሆነችው ካናዳ ሞንትሪያል ከሚገኘዉ አለም አቀፉ የሲቪል አቬሽን ተቋም ተቀብላለች።

ኢትዮጵያ የዚህ ማዕቀፍ አባል መሆኗ የኢትዮጵያን ፓስፖርት የያዙ ዜጎች በአባል አገራቱ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ያለምንም እንግልት እንዲጓጓዙ የሚያስችል ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ በየብስም ሆነ በአየር በተጭበረበረ የጉዞ ሰነድ ለመምጣት የሚሞክሩ አካላትን በቀላሉ ለመለየት የሚረዳና በአገር ላይ ሊቃጣ የሚችል የደህንነት ስጋትን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያግዝ ነው።

ኢትዮጵያ ወደዚህ ማዕቀፍ በይፋ መቀላቀሏን ተከትሎ የአለማቀፉ አቪዬሽን ድርጅት አባል አገራት ተወካዮችና የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች አካላት በተገኙበት አገሪቱ ያላትን ሁለንተናዊ አቅም የሚያስተዋውቅ መድረክ ተዘጋጅቷል።

በዚህ ወቅትም የኢትዮጵያን የአቪዬሽን ገፅታ፣ የኢሚግሬሽን ስርዓትና አሁናዊ ሁኔታ እንዲሁም የኢትዮጵያን የቱሪዝምና የቢዝነስ አቅሞች የሚያስተዋውቁ ገለፃዎች ተደርገዋል።

በስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት " ኢትዮጵያ የዚህ ማዕቀፍ (PKD) አባል መሆኗ ዜጎች በሚሄዱበት አገር ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ከማድረጉ ባሻገር የአገርን ደህንነት በመጠበቅ ረገድ አይነተኛ ሚና የሚጫወት ይጫወታል " ብለዋል።

" ኢትዮጵያ ጠንካራ በሆነው የአለም አቀፍ አቪዬሽን ትብብር ስርዓት ውስጥ የላቀ ቴክኖሎጂን መጠቀሟ ድንበሯን ከመጠበቅ ባለፈ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ የጋራ ደኅንነት መጠበቅ ያላትን ቁርጠኝነትም የሚያሳይ ውሳኔ ነው " ሱሉ ጠቁመዋል።

የካናዳ ትራንስፖርት ሚኒስትር ምክትል ሚኒስትር ኒኮላስ ሮብሰን " ኢትዮጵያ ወደዚህ ስርዓት በይፋ መቀላቀሏ በአቪዬሽን መስክ የምትሰራውን ስራ በዓለም የታመነ እንዲሆን ያደርጋል " ብለዋል።

" በተለይም በርካታ ዜጎችን ወደ ተለያዩ ክፍለ-ዓለማት የሚያጓጉዝ የግዙፍ አየር መንገድ ባለቤት በመሆኗ ይህን ማዕቀፍ መቀላቀሏ የሚደነቅ ውሳኔ ነው " ሲሉ ጠቁመዋል።

የአለማቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ፕሬዝዳንት ሳልቫቶሬ ሻኪታኖ ኢትዮጵያ ወደ ማዕቀፉ በመግባት የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ ተቋማቸው የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

መረጃው የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
" የአስራ ሁለት አመት ልጄን ነው በወባ በሽታ ያጣሁት " - አቶ ኦስማ አባመረሀባ በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ቆንዳላ ወረዳ ውስጥ ሁለት ህፃናትና አንድ አዋቂ በቱዋምቢ፣ ዲቾ እና ሹራ የተባሉ የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ በወባ በሽታ ህይወታቸው ማለፉን ነዋሪዎች እና የቤተሰብ አባላት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል። የቱዋምቢ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት አቶ ኦስማን አባመረሀባ የ12 ዓመት ልጃቸውን በወባ በሽታ…
" ሶስቱ ልጆቼ በወባ በሽታ ተይዘው በመንግስት የህክምና ተቋም መድሃኒት ማግኘት አልቻሉም " - አንድ የአካባቢው ነዋሪዎች

" መንግስት በነፃ መድሃኒቶችን  አቅርቧል  ህብረተሰቡ እጥረት አለ ካለ መጠቆም ይችላል " የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ

በኦሮሚያ ክልል በሶስት ዞኖች የወባ በሽታ ስርጭት መጨመሩን የኦሮምያ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ተስፋዬ ከበበው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ዶክተር ተስፋዬ ከበበው ምን አሉ ?

የክረምቱን መግባት ተከትሎ በጅማ፣ ምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች ስርጭቱ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል።

ሥርጭቱ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር  ሲነፃፀር በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል የሞት ቁጥር ግን ቀንሷል።

በአሁን ወቅት በሳምንት ውስጥ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1000 እስከ 2000 ሲሆን የሞት ቁጥር ደግሞ 1 ወይም ሁለት ነው። ይህ ቁጥር በክልል ደረጃ የተመዘገበ ነው።

የወባ በሽታ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያቀረቡት ቅሬታ ፦

" በቂ የመድሃኒት አቅርቦት በመንግስት የጤና ተቋም የለም " ሲሉ ነዋሪዎቹ ቅሬታ ያነሳሉ።

በምዕራብ ወለጋ ዞን የቆንዳላ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘሮ ጎልጃ ገርባ ሦስቱ ልጆቻቸው በወባ በሽታ ተይዘው በአካባቢው ባለው የመንግስት የህክምና ተቋም ቢሄዱም መድኃኃኒት እንዳላገኙ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ የቄለም ወለጋ ዞን ዳሌ ዋበራ ወረዳ ነዋሪ አቶ ተወከል ከማል በወረዳው ገጠራማ ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖሩ በርካታ ነዋሪዎች ለወባ በሽታ ተጋልጠዋል፤ ቀድሞ በመንግስት ተቋማት በነፃ ይሰጥ የነበረው የወባ መድሃኒት ከግል ተቋም በውድ ዋጋ  ለመግዛት መገደዳቸውን ገልፀዋል።

ወደ ሌላ ቦታ ሂዶ ለመታከምም በአካባቢው ባለው ግጭት ምክንያት መንቀሳቀስ አለመቻሉን አክለዋል።

ነዋሪዎች ባቀረቡት ቅሬታ ዙሪያ የምክትል ቢሮ ኃላፊው ምን ምላሽ ሰጡ ?

በቂ የመድሃኒት አቅርቦት ለሁሉም ወረዳዎች ቀድመን ልከናል እስካሁን የመድሃኒት እጥረት መከሰቱን ሪፖርት ያደረገ ዞንም ወረዳም የለም።

የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች በየ ቀበሌው ካሉ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጋር እንዲሰሩ ሶስት ሶስት የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ሰልጥነው አገልግሎት እየሰጡ ነው።

ህብረተሰቡ መንግስት በነፃ ያቀረበውን  መድሃኒት ማግኘት ካልቻለ ለቢሮው ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ምክትል ጤና ቢሮ ኃላፊው ዶ/ር ተስፋዬ ክበበው ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

በሽታው እንዳይባባስ ቢሮው ምን እየሰራ ነው ?

የበሽታው ስርጭት ጎልቶ በታየባቸው አካባቢዎች 600 ሺህ የአልጋ አጎበር የተሰራጨ ሲሆን በተለይ በምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች 12 ወረዳዎች እና በኢሉ አባቦር 3 ወረዳዎች ውስጥ ለ400 ሽህ ቤቶች የኬሚካል ርጭት ስራዎች በቅርቡ  እንደሚጀምር ጠቁመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነቀምቴ
#TikvahEthiopiaFamliyNekemte

@tikvahethiopia
#ኦዲት

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለቋሚ የሥራ ቅጥር መደቦች የቀን ሠራተኞችን በመቅጠር ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ መፈጸማቸው ተገለጸ፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የመንግሥት ተቋማት የ2016 በጀት ዓመት የበጀት ኦዲት አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርብ ነው የተገለጸው፡፡

ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በሪፖርቱ እንደጠቀሰው 12 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሳይፈቀድላቸው ለቋሚ የሥራ መደቦች ላይ የቀን ሠራተኞችን ቀጥረው ተገኝተዋል ብሏል።

ተቋማቱ በጠቅላላው 61,882,081 ብር ለቀን ሠራተኞች ክፍያ እንደፈጸሙ የገለጸው የፌዴራል ዋና ኦዲተር ፦
➡️ ጅማ ዩኒቨርሲቲ 25,310,211 ብር፣
➡️ አምቦ ዩኒቨርሲቲ 10,938,834 ብር፣
➡️ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ 7,888,374 ብር፣
➡️ ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ 5,170,600 ብርና ዲላ ዩኒቨርሲቲ 4,414,974 ብር በመክፈል ዋነኞቹ እንደሆኑ በሪፖርቱ ተጠቅሰዋል፡፡

እንዲሁም 17 የመንግሥት ተቋማት በጡረታ፣ በሞትና በሌሎች ምክንያት ከሥራ ለለቀቁ ሠራተኞች 408,462 ብር ያላግባብ ደመወዝ መክፈለቸው በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ካልተፈቀደ በስተቀር የሠራተኞች ቅጥር፣ የደረጃ ዕድገትና ዝውውር እንዳይፈጸም ቢከለክልም በስምንት መሥሪያ ቤቶችና በአንድ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በጠቅላላው 24,073,003 ብር የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንን ሳያስፈቅዱ ለቋሚ የሥራ መደቦች ሠራተኞችን በኮንትራት በመቅጠር ክፍያ ፈጽመዋል ተብሏል፡፡

ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንን ሳያስፈቅዱ የኮንትራት ቅጥር ከፈጸሙት ተቋማት መካከል ፦
- የቅደስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ፣
- ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ፣
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የአለርት ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋነኞቹ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ በ2015 በጀት ዓመትና ከዚያ በፊት በተከናወኑ የኦዲት ሪፖርቶች መሠረት ዕርምጃ የተወሰደ መሆኑን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ በአጠቃላይ እንዲመለስ አስተያየት ከተሰጠበት 20.5 ቢሊዮን ብርና 23,230 ዶላር ውስጥ፣ የተመለሰው ሦስት ቢሊዮን ብርገደማ ብቻ መሆኑን የፌዴራል ዋና ኦዲተር አስታውቋል።

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች አገልግሎትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በአጠቃላይ 37,304,100 ብር የአገልግሎት ገቢ ተመናቸውና በሚመለከተው አካል ሳያፀድቁ ገቢ መሰብሰባቸውም ተገልጿል፡፡

እንዲሁም 28 የፌዴራል መሥሪያ ቤቶችና ሰባት ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የፈጸሙት 348 ሚሊዮን ብር ክፍያ የተሟላ የወጪ ማስረጃ አልቀረበበትም ተብሏል።

የተሟላ የወጪ ማስረጃ ሳይቀርብ በወጪ ከተመዘገቡት መሥሪያ ቤቶች መካከል የጤና ሚኒስቴር፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና የቤተ መንግሥት አስተዳደር ዋነኞቹ ናቸው።

በ70 የፌዴራል መሥሪያ ቤቶችና በሰባት ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ከ404 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግሥትን የግዥ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ ያልተከተለ ግዥ ተፈጽሞ መገኘቱን ዋና ኦዲተር ገልጿል።
- ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣
- የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣
- የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽንና አርሲ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ከሕግ ውጪ ግዥ ከፈጸሙ ተቋማት መካከል ዋነኞቹ ናቸው።

ስምንት ተቋማት ደግሞ በጠቅላላው ከ6.5 ሚሊዮን በላይ ብር ዋጋ ያላቸውና ተገዝተዋል የተባሉ ንብረቶች እስካሁን ገቢ እንዳላደረጉ ሲገለጽ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ የቤተ መንግሥት አስተዳደርና የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ግዥውን ፈጽመው ዕቃዎቹን ገቢ ያላደረጉ

እንዲሁም በ2016 በጀት ዓመት 20 የፌዴራል መሥሪያ ቤቶች ከተመደበላቸው ዓመታዊ በጀት ውስጥ ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ ሳይጠቀሙበት ወደ መንግሥት ካዝና ተመላሽ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የዚህ መረጃ ባለቤት ሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

⚡️ በዕለታዊ የዳታ ጥቅሎች ከፈተና መልስ ዘና ፈታ እንበል! 🥳

በልዩ ልዩ አማራጮች የቀረበልንን የሳፋሪኮም የኢንተርኔት ጥቅል የM-PESA Appን በመጠቀም አሁኑኑ እንግዛ! በፈጣን ዳታ እንንበሽበሽ!

#1wedefit
#Furtheraheadtogethe
TIKVAH-ETHIOPIA
" የጉዞ ታሪክ በሌላቸው ሁለት ታዳጊዎች ላይ የMpox ምልክት መታየቱ ስጋት ፈጥሮብናል " - የሰገን ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዎች ➡️ " በኮንሶ ዞን የኤም ፖክስ(Mpox) በሽታ ምልክት በሁለት ሰዎች ላይ ታይቶ ናሙና ተወስዶባቸው ዉጤት እየተጠባበቅን ነዉ " - የዞኑ ጤና መምሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ የሰገን ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዎች ስለዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) በሽታ ምልክቶች በተለያዩ አጋጣሚዎች…
#Update

" በሰገን ዙሪያ ወረዳ በሁለት ሰዎች ላይ የታየዉ ምልክት የMpox በሽታ ስላልሆነ ሕብረተሰቡ ከስጋት ነፃ ሆኖ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት " - የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ


ከሰሞኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ አማራይታ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ በሁለት እህታማምች ላይ የታየዉን የሰዉነት ላይ ምልክትን ተከትሎ ሕብረተሰቡ " የኤም ፖክስ በሽታ ሊሆን ይችላል " በሚል ስጋት ዉስጥ መግባቱንና የዞኑ ጤና መምሪያ በበኩሉ ከተጠረጠሩት ሁለት የአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ ናሙና ወስዶ ለምርመራ መላኩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳቆ ነበር።

የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ግርማ በሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ከሁሉቱ እህታማሞች የተወሰደዉ ናሙና ዉጤት ከአዲስ አበባ መምጣቱንና በዉጤቱ መሰረት ምልክቱ MPox (የዝንጀሮ ፈንጣጣ) አለመሆኑ ተረጋግጧል ብለዋል።

አቶ ግርማ ሕብረተሰቡ በሽታዉን መጠንቀቁ አግባብ ቢሆንም ልጆቹንና ቤተሰቦቻቸውን ያገለለበት መንገድ ተገቢ አለመሆኑን ገልፀዋል።

ዉጤቱን ተከትሎም ስለ በሽታው የግንዛቤ ማስፋትና የጥንቃቄ ስራዎች እየተሰሩ ያለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ልጆቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ መደረጉንም አስታውቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
🔈#የአሽከርካሪዎችድምጽ

" ወደ 21 የሚሆኑ ሹፈሮች በታጣቂዎች ተገድለዋል " - የአሽከርካሪዎችን ጉዳይ የሚከታተል አካል

➡️ " የተገደሉ ሹፌሮች እንዳሉ ሰምቻለሁ፤ በጣም ከፍተኛ ችግር ነው ያጋጠመን በአጠቃላይ በጎንደር መስመር " - የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር

አማራ ክልል ከጎንደር መተማ በሚገኘው  መንገድ ሹፌሮች በታጣቂዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበርና የአሽከርካሪዎችን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተል አንድ አካል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የአሽከርካሪዎችን ጉዳይ የሚከታተለው አካል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ ከጎንደር መተማ ባለው መንገድ ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ/ም " ወደ 21 ሹፌሮች በታጣቂዎች ተገድለዋል " ብሏል።

የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊያሻቅብ እንደሚችል፣ ለጊዜው የደረሰው መረጃ ይህ እንደሆነ፣ የተገደሉት ከጂቡቲ ማዳበሪያ ጭነው የመጡ እና ሌሎች አሽከርካሪዎች መሆናቸውን፣ ጉዳዩን በተጨማሪ አጣርቶ እንደሚገልጽ ጠቁሟል።

ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ/ም አሁን ግድያ ተፈጸመ በተባለበት ቦታ አንድ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በታጣቂዎች መቃጠሉንም ገልጿል።

" ይህን ያህል ሰው እየተገደለ ጉዳዩ ትኩረት የማይሰጠው ለምንድን ነው? እኛ ዜጋ አይደለንም ወይ? ከ1500 ኪሎ ሜትር በላይ ማዳበሪያ ጭኖ የመጣን ሹፌር እልል ብሎ ይቀበሉታል እንጁ እንዴት ይገደላል ? " ሲል ይኸው የአሽከርካሪዎችን ጉዳይ የሚከታተለው አካል በሀዘን ጠይቋል።

ደረሰ የተባለውን ጥቃት በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያ የጠየቅነው የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር በበኩሉ፣ ከጎንደር መተማ ባለው መንገድ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ አሽከርካሪዎች መገደላቸውን መስማቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ማኀበሩ በሰጠን ቃል፣ " የተገደሉ ሹፌሮች እንዳሉ ሰምቻለሁ። ሁኔታው በጣም አስቸግሮናል፤ ፈተታኝም ሆኖብናል፤ ምን እንደምናደርግ ግራ ገብቶናል፤ በጣም ከፍተኛ ችግር ነው ያጋጠመን በደቡብ ጎንደር፤ በአጠቃላይ በጎንደር መስመር " ሲል ገልጿል።

" በጎጃም መስመር በኩል ያለው እንቅሴቃሴ ከሌሎቹ አንጻር የተሻለ ነው " ሲል የገለጸው ማኀበሩ፣ " የሚከፈል ገንዘብ ካለ እንጂ ግድያ የለም "ብሎ፣ " የሁለቱም ደቡብ ጎንደር፣ ከወሎ ከተወጣ በኋላ ከጋይንት እስከ ሰሜን ጎንደር ድረስ ጫካማ ቦታ ነው፤ ታጣቂዎች ሁለት፣ ሦስት ሆነው ጥቃት ያደርሳሉ " ሲል አስረድቷል።

በተያያዘ ዜና በድሬዳዋ መስመር " ቦርደዴ " ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ሰኔ 17 ቀን 2017 ዓ/ም ምሽቱን አንድ አሽከርካሪ በታጣቂዎች ታግቶ እንደተወሰደ፣ ያለበትም እንዳልታወቀ ማኀበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

በተለይም የጸጥታ፣ የኬላ፣ የመንገድ ችግሮች ዘርፉን በእጅጉ እንደፈተኑት፣ ለመንግስት አካላትም እንዳሳወቀ የገለጸው ማኀበሩ፣ " ለምሳሌ ኬላ ላይ የሚጠየቅ ክፍያን በተመለከተ የትራንስፓርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር አካላት የሚታገትበት ቦታ እየሄዱ በቪዲዮ ቀርጸው በፓርቲ ደረጃ ነው ያቀረቡት። ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ም ባለሃብቶችን ባወያዩበት ወቅት ‘ፍተሻውን እያካሄድን ክፍያው እንዲቀር አብን እንሰራለን’ ብለዋል፤ እንግዲህ ጉዳዩን እዛ ድረስ አድርሰናል " ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🚨#Alert

በትግራይ ክልል ላጋጠመ የደን ቃጠሎ የፌደራል መንግስት እገዛ ተጠየቀ። በሄሊኮፕተር የተደገፈ የውሃ ርጭት እገዛ እንዲደረግ ነው የተጠየቀው።

የትግራይ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ዛሬ ሰኔ 18/2017 ዓ.ም ለፌደራል የአደጋ ስጋትና አመራር ኮሚሽን በደብዳቤ እንዳስታወቀው ፤ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አፅቢ ወረዳ ቃልአሚን ቀበሌ  ሓይለ-ቡሐለ ልዩ ቦታ በሚገኘው የዱስኣ ጥብቅ ደን የእሳት ቃጠሎ አጋጥሟል።

" በዓፋር ክልል ልዩ ቦታ ገረብ ዋሕለ የጀመረው ቃጠሎ በሃይለኛ ንፋስ እየተስፋፋ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል " ብሏል።

" የአከባቢው ማህበረሰብ ቃጠሎው በባህላዊ መንገድ ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል " ያለው ኮሚሽኑ " ባለው ደረቅ የአየር ሁኔታና ሃይለኛ ንፋስ እየተባባሰ የከፋ ጉዳት በማድረስ ላይ ነው " ሲል ገልጿል።

የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ ከአከባቢው ማህበረሰብ አቅም በላይ በመሆኑ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደርና የፌደራል መንግስት እገዛ ተጠይቋል።

የእሳት ቃጠሎው በቁጥጥር ስር ለማዋል የፌደራል መንግስት በሄሊኮፕተር የተደገፈ የውሃ ርጭት እገዛ በአስቸኳይ እንዲያደርግ ኮሚሽኑ ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
2025/06/26 13:46:26
Back to Top
HTML Embed Code: