Telegram Group Search
#ነዳጅ

ከሰሞኑ በተለያዩ ከተሞች ረጃጅም የነዳጅ ሰልፍ በስፋት እየታየ ይገኛል። አሽከርካሪዎች ነዳጅ ለማግኘት ተሰልፈው እየዋሉ ፤ የስራ ጊዜያቸውም እየባከነ ፤ ስራዎችም እየተስተጓጎሉ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በሀዋሳ ከተማ ያለውን ሁኔታ ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

በሀዋሳ የነዳጅ ረጃጅም ሰልፍ በማደያዎች ለቀናት የቀጠለ ሲሆን ከወትሮዉ በተለየ መልኩ በሰልፉ ውስጥ የነበሩ የውጪ ሀገራት ተሽከርካሪዎችና የመድሐኒት ማመላለሻዎች እንዲሁም የእርሻ ትራክተር አሽከርካሪዎች አስተያየታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርተዋል።

አሽከርካሪዎቹ ምን አሉ ?

ሳራዋ ማቡዋ ከኬንያ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለመጫን ወደ ኢትዮጵያ የመጣ አሽከርካሪ ሲሆን በነዳጅ እጥረት ምክንያት ከዕቅዱ ዉጪ ለሶስት ቀናት በኢትዮጵያ ለመቆየት መገደዱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተነግሯል።

" ከሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለመጫን የመጣሁትን ምርት ከጫንኩ በኋላ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ነዳጅ ለመቅዳት ወደ ማደያ ብመጣም ረጅም ሰልፍ በመኖሩ እንድሰለፍ ተነግሮኝ ሰልፉ ሲቀል እመለሳለሁ ብዬ ወደ ማደሪያዬ በመሄድ በማግስቱ ስመለስ ሰልፉ ብሶበት ተሰልፌ ለማደር ተገድጃለሁ " ብሏል።

" ኢትዮጵያ ዉስጥ መቆየት ሰላም የሚሰጠኝ ቢሆንም በነዳጅ ምክንያት የዘገየኋት ሶስት ቀን በካምፓንያችን አሰራር መሰረት ለቅጣት ይዳርገኛል " ሲል ገልጿል።

ሮባ መሐመድ እና ሬድዋን ሀሰን የትራክተር ሹፌሮች ናቸው።

ድርጅታቸዉ በጌዴኦ ዞን ዲላ አከባቢ ካለዉ የእርሻ ኢንቨስትመንት ወደ አርሲ ዞን ወዳለዉ የእርሻ ቦታ እንዲሄዱ አዟቸው እየሄዱ ነዳጅ ስላለቀባቸዉ በሀዋሳ ሶስት ማደያዎች ተዟዝረዉ ቅድሚያ እንዲሰጣቸዉ ቢጠይቁም እንዳተፈቀደላቸዉና በዚህም ምክንያት ስራ እንደተስተጓጎለባቸዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

" በእርሻ ወቅት አንድና ሁለት ቀን ትልቅ ዋጋ አላቸዉ " ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ በነዳጅ ምክንያት ዘር ለመዝራት የተያዘዉ ቀጠሮ መስተጓጎሉን አስታዉቀዉ እንደሁኔታዉ ቅድሚያ ሊሰጣቸዉ የሚገቡ ተሽከርካሪዎችን በመለየት ቅድሚያ እንዲሰጣቸዉ ማድረግ ቢቻል መልካም ነዉ ብለዋል።

" ለልዩ አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ቅዲሚያ መስጠት አለበት " ያለን ስሙ እንዲገለፅ ያልፈለገ የመድኃኒት ማመላለሻ መኪና ሹፌር " ይህ ካልሆነ የነዳጅ ምርቶች እጥረት በሚኖርበት ወቅት ችግሩን ያባብሰዋል " ሲል ተናግሯል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ባሰባሰባቸውን መረጃዎች በየማደያው ከፍተኛ የነዳጅ ሰልፍ አለ።

አንዳንድ ማደያዎች ደግሞ " ነዳጅ የለም " የሚል መልዕክቶችን ለጥፈው እየተስተዋሉ ነው።

ከዚህ ቀደም በተሻለ ሁኔታ የሚገኘው ናፍጣ አሁን ላይ ማግኘት ከባድ ሆኗል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በነዳጅ ላይ የሚጨመር ዋጋ የለም " - ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ፤ ነዳጅ እያለ ዋጋ ይጨምራል በሚል እሳቤ ' የለም ' በሚሉ ማደያዎች ላይ  እርምጃ እንደሚወሰድ ገለጹ። " አንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ' ነዳጅ ይጨምራል ' በሚል አገልግሎት አቁመዋል። ነዳጅ ላይ የሚጨመር ዋጋ የለም " ሲሉ ለኤፍ ኤም ሲ ተናግረዋል። መንግስት ከግንቦት ወር ጀምሮ…
" የነዳጅ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል " - ሚኒስቴሩ

የሐምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ።

የሐምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከዛሬ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሰኔ ወር ሲሸጥ በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግሥት መወሰኑን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ የነዳጅ ማደያዎች እና ኩባንያዎች በነዳጅ ውጤቶች ግብይት አዋጁና በአሠራር መመሪያው መሠረት ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በእጀባ ተማሪዎችን የጫኑ 6 የሚጠጉ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች ደርሰው በሰላም ተመልሰዋል " - ሹፌሮች

ከሰኔ 16/2017 ዓ/ም በኃላ ተዘግቶ የሰነበተው የጎንደር መተማ መንገድ ዛሬ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች በመከላከያ ሰራዊት ፤ በከባድ ጥበቃ ታጅበው ደርሰው እንደተመለሱ ሹፌሮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለፁ።

ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት በቦታው የነበረው አሽከርካሪ ከጥቃቱ በኃላ መንገዱ ተዘግቶ የቆየ ቢሆንም ዛሬ ሰኔ 21/2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ከጎንደር መተማ ከመተማ ወደ ጎንደር ማመላለስ እንደቻሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ሌላው ለደህንነቱ በመስጋት ስሙን እንዳንጠቅስ የጠየቀን አሽከርካሪ " እጀባው የተካሄደው በሀገር መከላከያ ሰራዊት ሲሆን ብዛት ባላቸው እንደ ስናይፕርና መትረየስ የመሳሰሉ የቡድን መሳሪያዎችን በጫኑ ተሽከርካሪዎች ነው " ብለዋል።

ይህው አሽከርካሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገረው  " እኔን ጨምሮ ሌሎች ሹፌሮች በዚህ መስመር አንሄድም ብለን ብናምጽም የጎንደር ከተማ መናህሪያ  ስምሪት ክፍል በግዳጅ እንድንሄድ ስለታዘዝን ለመሄድ ተገደናል " ብሏል።

በእጀባ ተማሪዎችን የጫኑ 6 የሚጠጉ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች ደርሰው በሰላም መመለሳቸውን አሽከርካሪዎቹ አክለው ገልፀዋል።

በዚሁ መንገድ ሰኔ 16/2017 ዓ/ም እና 18 2017 ዓ/ም በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት 16 አሽከርካሪዎች ፣ የመንግስት የፀጥታ ሀይሎችና ንፁሃን መገደላቸውን የዞኑን አስተዳደርና የአይን እማኞችን ጠቅሰን መረጃ ማካፈላችን ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBahirdar

@tikvahethiopia
🕊#Peace

" ለችግሮቻችን መፍትሄ ከጠመንጃ ይልቅ የጠረጴዛ ውይይት እናስቀድም "  - የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር 

➡️ " በአሁኑ ሰዓት ትልቅ የህልውና አደጋ ለተጋረጠበት የትግራይ ህዝብ ስለ ዴሞክራሲና ልማት ማውራት ቅንጦት ነው " - የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር 


በአዲስ አበባ ከተማ " ሰላም ፣ ዲሞክራሲ እና ልማት በትግራይ እድሎችና ፈተናዎች " በሚል ርእስ የውይይት መድረክ ተካሂዶ ነበር።

የውይይት መድረኩ CENTRE FOR RESPONSIBLE AND PEACEFUL POLITICS (CRPP) የተባለ ተቋም ከአዲስ አበባ ዪኒሸርስቲ በመተባበር ነው ያዘጋጁት።

የውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የሰላም ሚንስቴር ሚንስትር አቶ መሐመድ እድሪስ " ከመነጋገር እናተርፋለን " ብለዋል።

" ሃሳብ ነው ሃገርን የሚገነባው ስለሆነም ለሃሳብ ክብርና ልዕልና እንስጥ ፤ ጠመንጃንና ጦርነትን እንጠየፍ የትግራይ የፓለቲካ ምህዳር ለወጣቶች እድልና ቅድሚያ ይስጥ " ሲሉ ተናግረዋል።

" ' አንዋጋም ይበቃል ' ማለት ታላቅ ድፍረት ይጠይቃል ከተቻለ ግን ውጤቱ እጅግ አመርቂና ፍሬውም ጣፋጭ ነው። ስለሆነም እርስ በርስ መዋጋት ይብቃ ፤ ሳንገዳደል አሸናፊ የምንሆንበት ሰላማዊ መንገድ እናስቀድም የመገዳደል የመተላለቅ ታሪክ ልንዘጋው ይገባል " ሲሉ ተደምጠዋል።

የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ፥ " የትግራይ ህዝብ አሁንም ከህልውና አደጋ አልወጣም " ብለዋል።

" ችግሮቻችን በውጭ ምክንያቶች እያሳሰበን ከመኖር ውስጣችን በደምብ በመፈተሽ የተወሳሰቡ ችግሮቻችን መፍታት እንችላለን " ሲሉ ገልጸዋል።

" ትግራይ ጥቂት አመራሮች ማረምና ማንሳት አቅተዋት በከባድ ፈተና ተዘፍቃ ትገኛለች ፤ ይህንን ከባድ ፈተና ለመወጣትና ለማለፍ ወጣቶችን ወደ መሪነት ማምጣት ይጠበቅበታል " ብለዋል።

" በአሁኑ ሰዓት ትልቅ የህልው አደጋ ለተጋረጠበት የትግራይ ህዝብ ስለ ዴሞክራሲና ልማት ማውራት ቅንጦት ነው " በማለት አክለዋል።

ለአንድ ቀን በተካሄደው የውይይት መድረክ " ሰላምና ደህንነት ፣ ዲሞክራሲ ግንባታ ፈተና እና እድል " የሚሉና ሌሎች የመወያያ ፅሁፎች ቀርበዋል።

በመድረኩ ከትግራይ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ፣ ስቪክ ማህበራት እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚኖሩ ታዋቂ ሙሁራንን ፓለቲከኞች ተገኝተው ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyMK

@tikvahethiopia            
#Medrek

አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ የመድረክ ሊቀመንበር ሆኑ።

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) " ታሪካዊ " ሲል የጠራውን ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዶ አዲስ አመራር መምረጡን ይፋ አደረገ።

" በሀገሪቱ ብቸኛው ቀዳሚ የብሔር ብሔረሰቦች የፖለቲካ ጥምረት " እንደሆነ የገለጸው መድረክ 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በተሳካ ሁኔታ በማካሄድ የውስጥ መነቃቃቱን የሚያበስር ወሳኝ እርምጃ እንደወሰደ ገልጿል።

በግንባሩ ጽ/ቤት የተካሄደው ጉባዔ፣ አዲስ አመራር በመምረጥና እውነተኛ ዴሞክራሲያዊትና ሰላማዊ #ኢትዮጵያን 🇪🇹 ለመገንባት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ በማስቀመጥ መጠናቀቁን አሳውቋል።

አዲስ የተመረጠው አመራር፣ ወጣት አመራሮችን ከተመክሮና ልምድ ካካበቱ አንጋፋ ፖለቲከኞች ጋር በስትራቴጂካዊ ቅንጅት ያካተተ እንደሆነና ይህም መድረክ የኢትዮጵያን ውስብስብ ፖለቲካዊ ተግዳሮቶች በብቃት እንዲወጣ እንደሚያስችለው አመልክቷል።

አዲሱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሆነው እነማን ተመረጡ ?

1. አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ ፦ የመድረክ ሊቀመንበር
2. አቶ ሱልጣን ቃሲም፦ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
3. ወ/ሮ መርየም ሓሰን ፦ ምክትል ሊቀመንበርና የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ
4. አቶ ሙላቱ ገመቹ፦ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ
5. ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ፦ ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ
6. አቶ ለገሰ ለንቃሞ፦ የመድረክ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
7. አቶ ደስታ ዲንቃ፦ የመድረክ ምክትል ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተመርጠዋል።

መድረክ ፦
- ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉዓላዊነት (ዓረና)፣
- የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣
- የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) እና የዓፋር ህዝብ ፍትህና ዲሞክራሲ ፓርቲን በአባልነት አቅፏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው የደረሰው ከመድረክ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።

(NB. ከላይ የተያያዘው የመድረክ መግለጫ ነው)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

ፎቶ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#EthiopianAirlines🇪🇹

" አውሮፕላኑ ያለምንም ችግር በሰላም አርፏል። ካረፈ በኋላ ስምንት ተጓዦች የህመም ስሜት ተሰምቷቸው ወዲያውኑ በህክምና ባለሙያዎች ክትትል ተደርጎላቸዋል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ አውሮፕላን ህንድ ውስጥ በድንገት ለማረፍ መገደዱና በተሳፋሪዎች ህመም ማጋጠሙን " ዘፋይናንሻል ኤክስፕረስ " የተሰኘው የውጪ ሚዲያ ዘግቧል።

ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኑ በሙምባይ ባጋጠመው ችግር " ሰባት ሰዎች መታመማቸው"ን የጠቀሰው ዘገባው፣ ከሰባቱ ሰዎች መካከል "አንዱ በጠና ታሞ ሆስፒታል ገብቷል" ብሏል።

የበረራ ቁጥር ET640 አውሮፕላኑ ክስተቱ ያጋጠመው 33 ሺህ ጫማ ብሎ መጓዝ እንደጀመረ መሆኑ ተመልክቷል። በዚህም " አውሮፕላኑ በድንገት ለማረፍ የተገደደው በአካባቢው በተከሰተው የአየር ፀባይ ነው " ተብሏል።  

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለጉዳዩ ማብራሪያ የጠየቀ ሲሆን፣ የአየር መንገድ የሕዝብ ግንኙነት ሐና አጥናፉ በሰጡን ቃል፣ " አውሮፕላኑ ወደ ሙምባይ እየበረረ በነበረበት ወቅት የበረራ አባላቱ በካቢን ውስጥ የነበረው ግፊት ቀንሶ አጎኝተውታል " ብለዋል።

" በበረራ ወቅት የበረራ አባላት ባረጋገጡት መረጃ መሰረት ፓይለቱ ደህንነቱ ወደ ተጠበቀ/ለፕሌኑ በሚመች (ከፍታ ቦታ ላይ) በመሄድ አርፏል " ያሉት ሐና፣ " የአደጋ ጊዜ የኦክስጅን ማስኮችን በአግባቡ ተጠቅሟል " ሲሉ ገልጸዋል።

" አውሮፕላኑ ያለምንም ችግር በሰላም አርፏል " በማለት ገልፀው፣ " ካረፈ በኋላ ስምንት ተጓዦች የህመም ስሜት ተሰምቷቸው ወዲያውኑ በህክምና ባለሙያዎች ክትትል ተደርጎላቸዋል" ሲሉም ሁነቱን አስረድተዋል።

" ሰባቱ በዚያው በአየር መንገዱ ህክምና አግኝተዋል። አንዱ ተጎጂ ለተጨማሪ ህክምና ወደ ሆስፒታል ተወስዷል። ነገር ግን ክትትል ከተደረገለት በኋላ ከሆስፒታል ወጥቷል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የአውፕላኑ አብራሪ ሁኔታው ሳይባባስ ፕሮፌሽናል በሆነ መንገድ መቆጣጠሩን ለመረዳት ተችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/06/29 00:58:39
Back to Top
HTML Embed Code: