Telegram Group Search
🚨#Alert

በትግራይ ክልል ላጋጠመ የደን ቃጠሎ የፌደራል መንግስት እገዛ ተጠየቀ። በሄሊኮፕተር የተደገፈ የውሃ ርጭት እገዛ እንዲደረግ ነው የተጠየቀው።

የትግራይ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ዛሬ ሰኔ 18/2017 ዓ.ም ለፌደራል የአደጋ ስጋትና አመራር ኮሚሽን በደብዳቤ እንዳስታወቀው ፤ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አፅቢ ወረዳ ቃልአሚን ቀበሌ  ሓይለ-ቡሐለ ልዩ ቦታ በሚገኘው የዱስኣ ጥብቅ ደን የእሳት ቃጠሎ አጋጥሟል።

" በዓፋር ክልል ልዩ ቦታ ገረብ ዋሕለ የጀመረው ቃጠሎ በሃይለኛ ንፋስ እየተስፋፋ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል " ብሏል።

" የአከባቢው ማህበረሰብ ቃጠሎው በባህላዊ መንገድ ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል " ያለው ኮሚሽኑ " ባለው ደረቅ የአየር ሁኔታና ሃይለኛ ንፋስ እየተባባሰ የከፋ ጉዳት በማድረስ ላይ ነው " ሲል ገልጿል።

የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ ከአከባቢው ማህበረሰብ አቅም በላይ በመሆኑ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደርና የፌደራል መንግስት እገዛ ተጠይቋል።

የእሳት ቃጠሎው በቁጥጥር ስር ለማዋል የፌደራል መንግስት በሄሊኮፕተር የተደገፈ የውሃ ርጭት እገዛ በአስቸኳይ እንዲያደርግ ኮሚሽኑ ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
#ሴጅ_ማሰልጠኛ

የሁለት ወር የልጆች የክረምት ስልጠና (25% ቅናሽ እስከ ቅዳሜ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም)
👉ስልጠናው ዕድሜያቸው ከ 5-18  ዓመት ላሉ ልጆች የሚሰጥ ነው።
👉 ልጆች ፕሮጀክቶች እየሰሩ የሚሰለጥኑበት
👉ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
የስልጠናዎቹ ዓይነት፦
👉 Computer Programming and Website Development
👉 AI and Robotics
👉 Graphic Design, Video Editing and Animation
👉 Art (Film Acting, Writing and Modeling)
👉 Painting, Drawing and Sculpture
👉 Language and Basic Computer

0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram
Tiktok
Linkedin
" የጓደኞቼ ፉገራ ለተሻለ ስራ አነሳስቶኛል፤ አሁን ላይ በአንድ ማስታወቂያ በሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ይከፈለኛል " - ወጣት ዳግማዊ

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሀዋሳ ከተማ በብስክሌት በላይ የሚደረግ ማስታወቂዎችን ማየት የተለመደ ሆኗል።

ወጣት ዳግም ታምራት ከአምስት ወራት በፊት ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ይጠቀምባት በነበረው አንዲት ብስክሌት ላይ የተወሰኑ የፈጠራ ስራዎችን ጨምሮ የተንቀሳቃሽ የማስታወቂያ ስራ የጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በቋሚነትና በጊዜያዊነት ለ7 ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር ችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወጣት ዳግም ታምራትን በስራዉ ዙሪያ አነጋግሮታል።

" ስራዉን የጀመርኩት ለራሴ መንቀሳቀሻ እጠቀምበት በነበረዉ ብስክሌት ላይ ተቀጣይ ባለ ሁለት ጎማ ላሜራ በመስራት የራሴን ማስታወቂያ ሰዎች እንዲያነቡት በማድረግ ነበር ፤ ቀስ በቀስም የሰዎችን ትኩረት ማግኘት ሲጀምር ሌሎች ድርጅቶችንና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማስታወቂያ ለማሰራት ጥሪ ማቅረብ ጀመሩ " ሲል ገልጿል።

" በአሁኑ ወቅት የብስክሌቶችን ቁጥር ከፍ በማድረግ ለ3 ቋሚና 4 ተጠባባቂ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጥሪያሁ " ያለን ወጣት ዳግም " በቀጣይም በዘርፉ የተለያዩ የማስታወቂያ ስራዎች ላይ ለመሰማራትና በLED ላይት የታገዘ ተንቀሳቃሽ የማስታወቂያ ስራ ለመጀመር ዕቅድ እንዳለዉ " ተናግሯል።

" በሞተር ሳይክል የሚንቀሳቀሱ ጓደኝቼ ' አንተ ምን አለብህ የነዳጅ ወጪ ሰልፍና ዋጋ አያስጨንቅህ፤ ለነገሩ ለጤናህም ስፖርት ነዉ ' እያሉ የሚቀልዱብኝ ቀልድና ፉገራ እንደዉም ለምን ይህን ብስክለት የገቢ ማመንጫ አላደርገዉም የሚል ቁጭት አሳድሮብኝ ብስክሌቴን ወደ ተሻለ ስራ አስገብቻለሁ አሁን ላይ በአንድ ማስታወቂያ በሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ይከፈለኛል " ሲል ተናግሯል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
" የውጭ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች ማመልከቻቸውን ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ ይችላሉ " - ብሔራዊ ባንክ

ኢትዮጵያ የባንክ ዘርፉን ለውጪ ባንኮች ክፍት ማድረጓን በይፋ አስታወቀች።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፉን ለውጭ ባንኮች ለመክፈት የሚያስችለውን መመሪያ አጽድቋል።

ባንኩ፥ መመሪያ ቁጥር SBB/94/2025 ወይም "የባንክ ሥራ ፈቃድ፤ የእድሳት መስፈርቶች እና የውክልና ቢሮ መመሪያ " መጽደቁን ነው ያስታወቀው።

በዚህ መመሪያ መሰረትም ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ባንኮችን ጨምሮ ሌሎች ስትራቴጂክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የባንክ ሥርዓት ውስጥ እንዲሳተፉ ይፈቅዳል።

ብሔራዊ ባንክ ትላንት ባወጣው መግለጫ ፥ " የኢትዮጵያ የባንክ መስክ ለውጭ ኢንቨስተሮች ተከፍቷል፤ የውጭ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች ማመልከቻቸውን ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ ይችላሉ " ሲል አስታውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Big 5 Construct Ethiopia እና የEast Africa Infrastructure & Water Expo

🔥 የመጀመርያው ቀን እጅግ የተለየ ነበር —  2ተኛው ቀን በፍጹም እንዳያመልጥዎ!

የBig 5 Construct Ethiopia እና የEast Africa Infrastructure & Water Expo አጀማመሩ እጅግ ደማቅ ሆኗል!  በከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ሹማምንት ተመርቆ የተከፈተው ደማቅ የንግድ አውደ ርዕይ፣ ለንግድ፣ ለፈጠራ እና ለዓለም አቀፋዊ ትሥሥሮች ሁነኛ መድረክ መሆኑን አስመስክሯል።

በመጀመሪያው ቀን ካልተገኙ:
  ከ20+ ሀገራት የተውጣጡ 180+ የምርት መለያዎችና አገልግሎቶች
የምርት ሙከራዎች፣ አዳዲስ ምርቶች እና በሲፒዲ የተረጋጠላቸው ትምህርታዊ ውይይቶች አምልጠዎታል!

ነገር ግን አልረፈደም! አውደ ርዕዩ በነገው ዕለትም ይቀጥላል!

📍 በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ
🕙 ከጠዋቱ አራት ሰዓት ጀምሮ!
🎟 አሁኑኑ በነጻ ይመዝገቡ: [https://www.big5constructethiopia.com/Tikvah_Ethiopia]
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DStvEthiopia

📣 ከእሁድ እስከ እሁድ አለንላችሁ!

❗️❗️ለአጭር ጊዜ የሚቆይ! ደንበኝነትዎን ከሰኔ 8 ጀምሮ ሲያራዝሙ ከፍ ወዳለው ፓኬጅ ከተጨማሪ ቻናሎች ጋር በስጦታ ያገኛሉ!!

አዲሱን እና የተሻሻለውን MyDStv መተግበሪያ ያውርዱ።
⬇️ https://mydstv.onelink.me/vGln/xepsjmo7

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው!

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
#EthPL🇪🇹

ክለቦች በየግል ሜዳቸው መጫወት ካቆሙ አመታት ያለፉት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2017 ዓ.ም ውድድር ተጠናቀቀ።

ኢትዮጵያ መድን በታሪኩ የመጀመሪያ ዋንጫውን አንስቷል።

በሱፐር ስፖርት ያለፉትን አመታት በአዲስ ቅርፅ የቀጥታ ሽፋን ያገኘው ሊጉ የአምስት አመት የቀጥታ ስርጭት ውል በይፋ ተጠናቋል።

ሱፐር ስፖርት ባለፉት አመታት 802 ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ለተመልካቾቹ አድርሷል።

በቀጣይ አመት ሊጉ በአዲስ ቅርፅ ሊደርግ እንደሚችል የአክስዮን ማህበሩ ዋና ስራ አስኪጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ ፍንጭ ሰጥተዋል።

" አሁን እየተጫወትን ከምንገኝባቸው ሜዳዎች የሜዳ መጫወቻ ' Home ' አድርገው የፈለጉትን ከተማ እንዲመርጡ አስበናል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ውድድሩን አርብ ፣ ቅዳሜ እና እሁድ በየሳምንቱ ለማድረግ አስበናል " ሲሉ ገልጸዋል።

ካለፉት ዓመታት ወዲህ ውድድሩ በተመረጡ ከተሞች ባሉ ስታዲየሞች ሲደረግ የቆየ ሲሆን ክለቦች መላ የቡድን አባላቶቻቸው ይዘው አንድ ከተማ ላይ ለሳምንታት በመቆየት ነው ውድድሩን የሚያደርጉት።

የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ እነማን ናቸው ?

➡️ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች :- ሀይደር ሸረፋ ( ኢትዮጵያ መድን )

➡️ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ :- ገብረመድህን ኃይሌ ( ኢትዮጵያ መድን )

➡️ የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ :- አቡበከር ኑራ ( ኢትዮጵያ መድን )

➡️ ወጣት ተጫዋች :- ይታገሱ ታሪኩ ( ኢትዮጵያ ቡና )

የአመቱ ምስጉን ዋና ዳኛ :- ማኑኤ ወልደፃዲቅ

➡️ የአመቱ ምስጉን ረዳት ዳኛ :- ሙስጠፋ መኪ  በመሆን ተመርጠዋል።

Via @tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ታጣቂዎቹ በየመኪናው የነበሩ ሹፌሮችንና ተሳፋሪዎችን ሳይቀር ነው እየዞሩ የገደሉት " - የአይን እማኝ

ከጎንደር ወደ መተማ በእጀባ ሲሄዱ በነበሩ አሽከርካሪዎች ላይ ከጫካ የወጡ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ከ20 በላይ አሽከርካሪዎች እና ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።

ከትላንትና በስቲያ ሰኞ ሰኔ 16/2017ዓ.ም ከጎንደር ተነስቶ በእጀባ ወደ መተማ ሲጏዙ በነበሩ ብዛት ባላቸው መኪኖች ላይ " መቃ" ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ ከጫካ የወጡ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት ከ20 በላይ አሽከርካሪዎችና ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸ የአይን እማኞች ገልፀዋል።

ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀን በቦታው የነበረ አንድ በተለምዶ " አባዱላ " ተብሎ የሚጠራው መኪና አሽከርካሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፦

" ከጎንደር ወደ መተማ ለመሄድ አጃቢ ስጠብቅ ቆየሁ ከ9:00 በኃላ አንድ አራት ከሚሆኑ ሹፌር ጏደኞቼ ጋር ተነጋግረን እንሄድ በቃ ቀረጥ ከፍለን ብናልፍ ይሻላል ተባብለን ጉዞ ጀመርን።

ከዛ ' መቃ ' የሚባለው ቦታ ላይ ቆመን ለታጣቂዎቹ ቀረጥ ለመክፈል ተራ እየጠበቅን እያለ ከኃላ ሌሎች መኪኖችን ያጀበ አንድ ፓትሮል ሙሉ አድማ ብተና ፖሊስ መጣ ከዛም ታጣቂዎቹ ' መኪኖቹን አስቁሟቸው ቀረጥ ከፍለው ነው የሚያልፉ ' ሲሉ ነገሯቸው ፖሊሶቹም ወርደው ወደ ታጣቂዎቹ ' የታጀበ ተሽከርካሪማ አይከፍልም ' በማለት መልስ ሰጡ። ታጣቂዎቹ መልሰው ' እና ጫካ ያለው ታጣቂ ምን ሊበላልህ ነው ? ' ብለው መለሱ። በዚህ ጭቅጭቅ ተነሳ። በጭቅጭቁ መሀል አንድ ታጣቂ ይመታል ወዲያውኑ ሁኔታው ተቀያየረ።

ከጫቃ በርካታ ቁጥር ያላቸው ታጣቂዎች እየተኮሱ ወጡ ፖሊሶችና ታጣቂዎች ሲጨቃጨቁ ከመኪናቸው ወርደው ጭቅጭቁን ከበው ሲሰሙ የነበሩ አሽከርካሪዎች በሙሉ ተገድለዋል።

በኃላም ታጣቂዎቹ በየመኪናው የነበሩ ሹፌሮችንና ተሳፋሪዎችን ሳይቀር ነው እየዞሩ የገደሉት በአጠቃላይ ከ20 በላይ ሹፌሮችና ንፁሃን ተገድለዋል።

አስከሬናቸውም ትላንት ነው የተነሳው የጎንደር መተማ መንገድ ከትላንት በስቲያ ጀምሮ ተዘግቷል እኔም ትላንት በአብድራፊ ዞሬ ነው ወደ ጎንደር የገባሁት " ብሏል

ጭኑ ላይ በሁለት ጥይት ተመትቶ በመተማ ሆስፒታል እየታከመ ያለ አንድ የአይሱዚ ረዳት መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የተናገረው የአይን እማኝ ደግሞ፦

" ወደ መተማ በእጀባ እየተጏዝን እያለን ነበር ተኩሱ የተጀመረው።

እኔና ሹፌሩ መኪና ውስጥ ተቀምጠን እያለ አንድ ታጣቂ መጥቶ ሹፌሩን ገደለና እኔን ሁለት ግዜ ጭኔ ላይ ተኩሶ አቆሰለኝ።

ይህ የሆነው ከ10:30 እስከ 11:00 ሰዓት ነው ታጣቂዎቹ የሚፈልጉትን ከገደሉ በኃላ ሄዱ ብዙ ቆይቶ መከላከያ መጣ የመጣውም ከምሽቱ 2:30 አካባቢ ነበር እኔንም አንስተው ወደ ሆስፒታል የላኩኝ በዚህ ሰዓት ነው።

ከ10:30 እስከ ምሽቱ 2:30 ድረስ ከጏደኛየ አስከሬን ጋር መኪና ውስጥ ነበር የነበርኩት።

ትላንት 18 አስከሬን ተነስቶ ወደ መተማ መጥቷል ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ የማውቃቸው ሹፌሮች ናቸው " ብሏል።

ሌላው በአንድ ሚኒ ባስ ውስጥ ተሳፍሮ ሲጏዝ የነበረ እና አሁን ቆስሎ መተማ ሆስፒታል የሚገኝ ተሳፋሪ ደግሞ ፦

" ተኩሱ ሲበዛ ወርደን በአንድ የጭነት መኪና ጉማው ስር ተኛን እንደገና ተነስተን እየሮጥን እያለን እግሬ ላይ በጥይት ተመትቼ ወደኩ " ብሏል።

በመተማ ሆስፒታል የሚሰራ አንድ ስሙን መግለፅ ያልፈለገ የህክምና ባለሙያ ትላንት የ3 ሹፌር አስከሬን በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ መመልከቱንና ቆስለው የመጡ ሰዎች በሆስፒታሉ ማከሙን ነግሮናል።

ይህው የህክምና ባለሙያ ቆስለው የገቡ ሰዎች ነግረውኛል ያለውን መረጃ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲገልፅ " እርስ በራሳቸው ሲለሚተዋውቁ ሲነጋገሩና ሲደዋወሉ ነበር ከዚህ ተነስተው 21 ሹፌሮች ብቻ ሙተዋል ብለው ነግረውኛል " ብሏል።

የአብዛኛዎቹ ሟቶች አስከሬን ወደ ሆስፒታል አልመጣም ሲልም አክሏል።

ሌላው ተኩስ ከመጀመሩ በፊት በ3 ኬላዎች ላይ 6 ሺ ብር ቀረጥ ከፍሎ ያለፈው ሌላው አሽከርካሪ ሲናገር ምንም እንኳን መንገዱ አለም አቀፍ ቢሆንም ትኩረት ያልተሰጠው ሽፍታ እንደልቡ የሚፈነጭበት መንገድ ነው ይላል።

" በዚህ መስመር በሆና ፣ ግንትና መቃ በሚባሉ ቦታዎች ላይ 3 ኬላዎች አሉ እንደ ህጋዊ ተቆጥረው ነው ገንዘብ የሚሰበስቡት ሁለት አመትም እየተጠጋቸው ነው " ብሏል።

" ' መቃ ' ላይ ታጣቂዎች ምንም ነገር የሚፈሩ አይደሉም እንዴት የመንግሥት ፀጥታ ኃይል አጅቦ የሚያልፍን ተሽከርካሪ ቀረጥ ክፈል ይላሉ ከዛም አልፈው ይከራከራሉ ፤ ፀጥታ ኃይል ላይም ይተኩሳሉ ? ሽፍታ ይሄን ያህል ድፍረት ከየት አመጣ ከጀርባቸውስ እነማን ቢኖሩ ነው ? " ሲል ጠይቋል።

በጥቃቱ ዙሪያ እስካሁን ከመንግስትም ሆነ ከሌላ ሶስተኛ ወገን የተባለ ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባህር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBD

@tikvahethiopia
በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የሚፈጠሩ የእርቃን ምስሎች ስጋትነታቸው ጨምሯል !

➡️ " አንዳንዶች እነዚህን ምስሎች የቀድሞ የፍቅር አጋራቸውን ለመበቀል ይፈጥራሉ " - ተመራማሪዎች


ዓለማችን በተለያየ ጊዜ በርከት ያሉ የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎችን እያስተናገደች ነው የመጣችው። ከቴክኖሎጂዎቹ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ስጋቶችንም በዛው ልክ አስተናግዳለች።

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የወቅቱ አነጋጋሪው ቴክኖሎጂ ሲሆን ጥቅሙም ስጋቱም በዛው ልክ እየጨመረ መጥቷል።

በዓለም ላይ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በመታገዝ የሚፈጠሩ የእርቃን ምስሎች ስጋትነታቸው ከቴክኖሎጂው መዘመን ጋር እየጨመረ መጥቷል።

የአሜሪካ 38 ግዛቶች በዲፕፌክ የሚሰሩ የህፃናት የእርቃን ምስሎች ላይ እገዳ ቢጥሉም የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዌብሳይቶች የእርቃን ምስሎችን ለመስራት በመቅለላቸው ስጋታቸው አይሏል።

በእነዚህ ዌብሳይቶች ሰዎች የሚያውቋቸውን ሰዎች ምስል በማስገባት ወደ እርቃን ምስልነት እንደሚቀይሩ ተገልጿል። ምስሎቹ ለእውነትነት የቀረቡ በመሆናቸው ሰዎች ለመለየት እንደሚቸገሩ ባለሙያዎች አስረድተዌ።

የኮምፒውተር ሳይንስ ባለሙያው ማይክል ዚመር ፤ ምስሎቹ ፍፁም እውነተኛ እንደሚመስሉና በርከት ያሉ የመተግበሪያ ድርጅቶች እንደዚህ አይነት ምስል የሚሰሩ መተግበሪያዎችን ማስወገዳቸውን ገልጿል።

ይህንን የሚሰሩ ድህረገጾች ግን አሁንም መኖራቸውን ባለሙያው ተናግሯል።

ዚመር " የፎቶ ኤዲቲንግ ቴክኖሎጂው በጣም ዘምኗል " ያለ ሲሆን " አሁን ላይ እነዚህን የእርቃን ምስሎች ለመፍጠር አንድ ክሊክ ብቻ በቂ ነው " ሲል አብራርቷል።

ኤሊስተን ቤሪ የተባለች የ14 አመት ልጅ በእንደዚህ አይነት መንገድ የእርቃን ምስል እንደተሰራባት ትናገራለች።

ይህንን ምስሏንም ከ2400 የሚበልጡ የትምህርት ቤቷ ተማሪዎች እንደተመለከቱት ገልጻለች።

' ቶርን ' የተሰኘ ድርጅት ዕድሜያቸው ከ13-20 በሚሆኑ 1200 ልጆች ላይ ጥናት ማድረጉን ገልፆ በጥናቱ ከስምንቱ ልጆች አንዱ በዲፕፌክ በተሰራ የእርቃን ምስል የተጠቃ ሰው እንደሚያውቅ እንደዚሁም ደግሞ ከ17 ሰዎች አንዱ እራሱ የዚህ ድርጊት ሰለባ አንደሆነ መታወቁን ይፋ አድርጓል።

ተመራማሪዎች አንዳንድ ህፃናት እነዚህን ምስሎች ማወቅ ስለሚፈልጉ ብቻ ይፈጥራሉ ያሉ ሲሆን አንዳንዶች የቀድሞ የፍቅር አጋራቸውን ለመበቀል ይፈጥራሉ ብለዋል።

በአሜሪካ በርካታ ግዛቶች ያለ ግለሰቡ ፈቃድ የእርቃን ምስል መፍጠርና ማጋራት ወንጀል ቢሆንም አሁንም ጉዳዩ አስጊነቱ በመጨመሩ ጥንቃቄ ያሻል ተብሏል።

በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በመታገዝ የሚፈጠሩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ውስብስብ እየሆኑ የመጡ ሲሆን እውነተኛ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ስለሚከብድ ነገሩን በጥንቃቄ ማየት ይገባል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከፎክስ 6 ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
2025/06/27 02:56:03
Back to Top
HTML Embed Code: