group-telegram.com/yabsiratesfaye/116
Last Update:
ልጅነት አላውቅም። ልጅም ሆኜ አላውቅም። ልጅነት ግን ምንድን ነው? ልጅ መባል ልጅ መሆን ምንድን ነው?
ያኔ!.... ሲመሻሽ ፈራለሁ፣....ፀሀይ በጨረቃ ስትተካ እሳቀቃለው፣የማሳልፋቸውን ሌሊቶች በአይነ ህሊናዬ ስቃኝ ያንገፈግፈኛል፣ እጆቿን ይዥ በክንዶቼ ተጠምጥሜባት ትተሽኝ አትሂጂ ብላት ደስ ይለኛል። ግን አልችልም። እናቴ መሆኗን እፈራለው ውስጤ ያፍርባታል።
ለምን? እሷኮ እንደሌሎቹ እናት አልነበረችም። የሚያምር ፊት አልነበራትም፣ ምግብ አትሰራልኝም፣ ልጄ ብላኝ አታውቅም፣ አትወደኝም! ብትወደኝማ. . . ጥላኝ አትሄድም ነበር። አውቃለው! እሷ እናት መሆን አትችልም! እኔም ልጅ!
ግን እኮ ልጅ ነኝ. .. ያውም ከመኝታዬ ስነቃ የምንተራሰው ክንዶች የምፈልግ! የእናትነት ጠረን ማሽተት መማግ የምመኝ! ልጅ ነበርኩ! እጄን ይዛ የምትመራኝ እናት የምፈልግ.....
ከቤት ወጥታ እስክትመለስ ሰጋለሁ ካሁን አሁን ሞተች የሚሉኝ መስሎኝ አውጠነጥናለው። አንዳንዴማ ስጋቴ ልኩን አልፎ እታመማለው...ለምን ነው? እንደዛ የሚሰማኝ አልወዳትም እኮ ሰው ፊት በድፍረት እናቴ ናት ማለትን ከጎኗ እየሄድኩ ልጇ መባልን አልወደሁም እጠላዋለው. ...ልጅነትን እፈራለው ለዛች ሴት ልጅ መሆንን ባስ ሲል መባልን እፈራለው።
አንድ ቀን.......ተኛሁ.....ልጅ ሆንሁ። ልጅነትን ወደድኩት እጆቼን አንስቼ ዳሰስሁ...አጠገቤ ነበረች ነካዋት. ....ጠረኗ ይጣራል እናት እናት ትሸታለች። እናት እናት ትላለች። ከወደ አንገቷ ተወሽቄ ማግሁት! ደስ ይላል! ለዘላለም እዛ መኖሪያን ላሰናዳ ተመኘው።
የልቧ ትርታ ፍቅርን ፍቅርን ያወራል፣ ፍቅሯ ተጋባብኝ። .....ነጋ ከጎኗ በኩራት እየሄድኩ እቺ ናት የእኔ እናቴ አለሁ.......ወደድኳት፣ ከጎኔ ሆና ናፈቀችኝ፣ አላመንኩም! ዛሬ ጥላኝ አልሄደችም ፀሃይ በጨረቃ ተተክታ መልሳ በፀሀይ እስክትሰየም ከጎኔ ነበረች። ታቅፈኛለች፣ በእጆቿ ትዳብሰኛለች......አይኖቼን እያየች ልጄ ትለኛለች!
.... ፍቅር ናት ፍቅር ራሱ አካል ለብሶ እሷ ላይ አየሁት።ድንገት ግን ሁሉም ነገር ሩቅ እየሆነ ፣ መልኳ እየደበዘዘ ሄደ። ቀስ ቀስ እያለ ጠፋ። ...ነቃው ፈለግኳት ከጎኔ አገኛት ይመስል ግን የለችም! ህልሜ ነበረች! ህልሜን አየኋት። ህልሜን በህልሜ አየኋት! ልጅነቴን እናቴን አየኋት! ከህልሜ ፍቅር ያዘኝ ህልሜን አፈቀርኳት!
✍ አርያም ተስፋዬ (2013)
BY አርያም - ARYAM
Warning: Undefined variable $i in /var/www/group-telegram/post.php on line 260
Share with your friend now:
group-telegram.com/yabsiratesfaye/116