Telegram Group & Telegram Channel
🛑 ፃማ 🛑

ክፍል አስራ ሶስት
ትዝታ ከቤት እንደወጣች ብሌን በእፎይታ ሶፋው ላይ ተወረወረች። እዮብ ቢሆን እንደዚች አይነቷን አይደለም ለጓደኝነት ለአይንም ቢሆን ይጠየፋት ነበር ስትል አሰበች። መልካቸው ብቻ ነው ለካ የሚመሳሰለው አለች በልቧ። ምንም ስለአልአዛር የግል ህይወት አያገባኝም! ግን ምን ሲሆን ከእንደዚች አይነቷ ጋር ሆነ? ብሌን ከቅሬታዋ በላይ የሚሰማት ብስጭት መንስኤውን አለማወቋ አሳሰባት። ምን አልባት አልአዛርን እንደ እዮብ ቆጥራው ይሆናል። ወይም የወንድሙ ውለታ ስለሱ እንድትጨነቅ አስገድዷትም ይሆናል። ብቻ ተበሳጭታለች። ማታ አልአዛር እስኪመጣ መታገስ አቃታት።

እንደምንም መሸና አልአዛር ቤት መጣ። እራት ካቀረበች በኃላ "ትዝታ የምትባል ሴት መጥታ ነበር።" እዚ ስታጣህ ሱቅ ይኖራል ብዬ ብነግራትም ነገ መጣለው ብላ ሄደች አለች በዝምታ የተዋጠውን ማዕድ በማደፍረስ። እና ምን አለችሽ? የሚያስቀይም ነገር ተናገረችሽ? ጥያቄውን አከታትሎ ጠየቃት። አይ ምንም አልተናገረችም የናትናኤል እጮኛ ነኝ ብዬ ስነግራት ያመነችኝ ትመስላለች ... ብሌን እናቷን ስትዋሻት ሁሌም ታውቅባት ነበር። ትዝታ ግን አለማወቋ አስደስቷታል።

አልአዛር የብሌን ትዝታን ማየት ረፍት ነሳው። የትዝታ መጥፎ ባህሪያቶች ብቻ ሳይሆን ብሌን ከነጭራሹ ከትዝታ ጋር የነበረውን ነገር ባታውቅበት ይመርጣል። ዛሬ ካለወትሮው ወደ ስራ ለምን እንደሄደ አሰበ "ሽሽት" አለ በሆዱ። እኮ ከምን? መልሶ ራሱን ጠየቀ። ከብሌን? እሱማ አይሆንም በሌላ ያሳበበው ስጋቱ እየተገለጠ ነው።

ጠዋት ይወጣል ማታ ይገባል። በሚገናኙበት ጊዜም ብዙም እንዲያወሩ አይፈልግም። የብሌን ትህትና መልክ አነጋገር ለወንዶች ቀዝቃዛ ወጥመድም ነው። በወጥመዱም ላለመያዝ ይሸሻል ግን ስሜቱ ባላወቀው መንገድ የተሸነፈ ይመስላል ወንድሙን እዮብን የከዳ ቃልኪዳኑን ያጠፈ ስሜት እስኪሰማው ያህል።

መሸሻ ፈለገ ከቤቱ የት ይሂድ? ብሌን ደግሞ እሷን ለአይኑ እንኳን የጠላት መስሏታል። ሊያናግራት አለመፈለጉ አይኖቹን ከእሷ ማሸሹ  ለወንድሙ ሞት ተጠያቂ እሷ የሆነች አድርጎ ያሰበ መሰላት። ትክክል ነው ከኔ ውጪ ለእዮብ ሞት ተጠያቂ ማነው? እዮብን ስታስብ በፀፀት ልትሞት ትደርሳለች። ስለ እሱም ላለመስማት ላለማሰብ ጥረት አድርጋለች ግን ከጭንቅላቷ ሊወጣላት አልቻለም። ቀስ በቀስ ድባቴ ውስጥ መግባት ጀመረች። ቀን ላይ ስለነበራት ህይወት አሁን ስላለችበት ስለወደፊቷ በማሰብ ራሷን ታስጨንቃለች። መሽቶም አልአዛር ሲመጣ ከአንድ ሁለት ቃላት ውጪ ንግግር ስለማይኖራቸው የመሰልቸት የተጠያቂነት ስሜቷ አየለባት።

✍️✍️✍️✍️ይቀጥላል...
@yabsiratesfaye ለወዳጅ ለዘመዶ ያጋሩ

group-telegram.com/yabsiratesfaye/129
Create:
Last Update:

BY አርያም - ARYAM

Warning: Undefined variable $i in /var/www/group-telegram/post.php on line 260

Share with your friend now:
group-telegram.com/yabsiratesfaye/129

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

One thing that Telegram now offers to all users is the ability to “disappear” messages or set remote deletion deadlines. That enables users to have much more control over how long people can access what you’re sending them. Given that Russian law enforcement officials are reportedly (via Insider) stopping people in the street and demanding to read their text messages, this could be vital to protect individuals from reprisals. Telegram Messenger Blocks Navalny Bot During Russian Election Stocks closed in the red Friday as investors weighed upbeat remarks from Russian President Vladimir Putin about diplomatic discussions with Ukraine against a weaker-than-expected print on U.S. consumer sentiment. The SC urges the public to refer to the SC’s I nvestor Alert List before investing. The list contains details of unauthorised websites, investment products, companies and individuals. Members of the public who suspect that they have been approached by unauthorised firms or individuals offering schemes that promise unrealistic returns Elsewhere, version 8.6 of Telegram integrates the in-app camera option into the gallery, while a new navigation bar gives quick access to photos, files, location sharing, and more.
from us

Telegram አርያም - ARYAM
FROM American