Telegram Group Search
IMG_20250420_134628_200.jpg
4.9 MB
#ዜና ውሉደ ብርሃን

በአጥቢያው የሚገኙ  አቅመ ደካሞችን እና ነዳያንን የማስፈሰክ መርሐ ግብር ተካሔደ።

የእንጦጦ መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ውሉደ ብርሃን ሰ/ት/ቤት ከልማትና በጎ አድራጎት ክፍል ጋር በመተባበር ከሚያከናውናቸው ልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎች  መካከል አንዱ  በአጥቢያችን ዙሪያ ለሚገኙ ነዳያንን እና አቅመ ደካሞች ልዩ ልዩ ድጋፎችን ማደረግ ነው። የአጥቢያውን ምእመናን እና የሰንበት ትምህርት ቤቱን አባላት በማስተባበር በዐበይት በዓላት ነድያንና እና አቅመ ደካሞችን  የማስፈሰክ መርሐ ግብር ከሚያከናውናቸው ድጋፎቹ መካከል  የሚጠቀስ ረጅም ዓመታት ያስቆጠረ አገልግሎት ነው ።

በዛሬው ዕለትም የጌታችንን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ፣ ከምዕመናንና ከአባላት ከተሰበሰበው ገንዘብ ከአጥቢያችን ከሚገኙ  አቅመ ደካሞችን እና ነዳያን  የማስፈሰክ  መርሐ ግብር  ተከናውኗል።

በመጨረሻም ይህን  በጎ ተግባር በማጠናከር እና በማስፋት ነድያንን በዘላቂነት ለማቋቋም ሰንበት ት/ቤቱ  የበጎ አድራጎት ሥራዎች ምእመናን በልዩ ልዩ መንገድ በመደገፍ የበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ሰ/ት/ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል ።


የውሉደ ብርሃን ሚድያ👇

ለመቀላቀል  ➠

🧷YouTube
https://www.youtube.com/@WuludeBirhan7

  🧷Facebook  https://www.facebook.com/1880533115515403/posts/2831103630458342/?app=fbl  
 
🧷Telegram
https://www.group-telegram.com/weludebirhane.com


  🧷Tiktok https://www.tiktok.com/@weludebirhan1?_t=ZM-8t8Bq1Nt0vV&_r=1

🧷Website
https://wuludebrihan.org.et
ልዩ የአጋፔ መርሃግብር በእናት ዉሉደ ብርሃን ሰ/ት/ቤ
በዕለተ ሰኑይ 13 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ አይቀርም።
በፍቅር በአንድ ማዕድ!!!

መልካም በዓል

አዘጋጅ፡ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ክፍል
#ዜና ዉሉደ ብርሃን

"ወተንሥአ እግዚያብሔር ከመ ዘንቃህ እም ንዋም........"
“እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ....."
( መዝሙር ፸፰፥፷፭ )
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል አደረሳቹ።

የእንጦጦ መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ዉሉደ ብርሃን ሰ/ት/ቤት የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በማስመልከት   13/08/2017 ዓ/ም  የአጋፔ (የፍቅር ማዕድ ) መርሃ ግብር በኦዲት እና ኢንስፔክሽን ክፍል አዘጋጅነት በትንሿ አዳራሽ ክፍል በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ።

    በመርሃ ግብሩም
ጉባኤውን በፀሎት በመክፈት  ፣ በቪዲዮ የተደገፈ በቃለ ወንጌል ፣ ውይይት በማድረግ ፣ አዝናኝና ቁም ነገር ያላቸውን ጥያቄና መልስ በማድረግ ፣ በዝማሬ እና የፍቅር ማዕድን በጋራ በማድረግ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል ።


የውሉደ ብርሃን ሚድያ👇

ለመቀላቀል  ➠

🧷YouTube
https://www.youtube.com/@WuludeBirhan7

  🧷Facebook  https://www.facebook.com/1880533115515403/posts/2831103630458342/?app=fbl  
 
🧷Telegram
https://www.group-telegram.com/weludebirhane.com


  🧷Tiktok https://www.tiktok.com/@weludebirhan1?_t=ZM-8t8Bq1Nt0vV&_r=1

🧷Website
https://wuludebrihan.org.et
2025/06/26 13:41:17
Back to Top
HTML Embed Code: