Telegram Group Search
ስላሴ በእስልምና መነፅር በሚል ከስላሴ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥያቄዎች ላይ የቀረበ ተከታታይ ምላሽ ነው።



ክፍል አንድ
https://vm.tiktok.com/ZMk9XJydT/

ክፍል ኹለት

https://vm.tiktok.com/ZMk9CT2YG/

ክፍል ሶስት

https://vm.tiktok.com/ZMk9XhmS9/

ክፍል አራት

https://vm.tiktok.com/ZMk9XAfS9/

ክፍል አምስት

https://vm.tiktok.com/ZMk9XeFpa/

ክፍል ስድስት

https://vm.tiktok.com/ZMk9XJYpQ/

ክፍል ሰባት

https://vm.tiktok.com/ZMk9XLVPX/

ክፍል ስምንት

https://vm.tiktok.com/ZMk9Xhx1L/

ክፍል ዘጠኝ

https://vm.tiktok.com/ZMk9XFMKH/

ክፍል አስር

https://vm.tiktok.com/ZMk9CooHD/

ክፍል አስራ አንድ

https://vm.tiktok.com/ZMk9XrwaA/

ክፍል አስራ ኹለት

https://vm.tiktok.com/ZMk9XBT8S/

ክፍል አስራ ሶስት

https://vm.tiktok.com/ZMk9X2KyT/
Eliyah Mahmoud
محاضرة : المخطط السري لإدارة العالم | خريطة العالم 2050 تحت إشراف الشيطان https://youtube.com/watch?v=RUJiOPmD8o4&feature=shared
ዶር ሐይሰም 2050 ዓለም ምን ላይ እንደምትደርስ በዚህ የሓምሳ ደቂቃ ቪዲዮ ላይ ይተነትናል።

እኛም እዚህ ቤት ውስጥ ኢንሻአላህ በዚህ ጉዳይ ላይ በተከታታይ የምናወጋ ይኾናል።
ነብይ ለመኾን (፮)

ይህ ክፍል በዚህ ርዕስ ለያዝነው ሐሳብ የመጨረሻ ይኾናል፡፡ ቀጥለንም ዶር ሐይሰም ባነሳቸው ጉዳዮች ላይ የምናወራ ይኾናል፡፡
….
በኢስላም አላህ ከአደም (ዐለይሂ አሰላም) በኋላ ነብያትን ሲያስናሳ አራት መሰረታዊ ምክንያቶች ነበሩት፡-

፩ኛ) ቀድሞ የነበረው ነብይ አስተምሮ ያለፈው መለኮታዊ ትምህርት ከስሞ ሲገኝና ያንን ትምህርት ሕያው ማድረግ ሲያስፈልግ አላህ በተመሳሳይ መልዕክት ላይ አተኩሮ የሚሰብክ ሌላ ነብይ ያስነሳል፡፡

ከዚህ ሐሳብ አኳያ ከሙሳ (ዐለይሂ አሰላም) በኋላ የተነሱትን በርካታ ነብያት ዋቢ አድርጎ መጥቀስ ይቻላል፡፡

፪ኛ) ቀድሞ የተሰበከው መለኮታዊ አስተምህሮ አኹን ካለው ትውልድ ጋር መራመድ ሳይችል ሲቀር አላህ አዲስ ነብይ በአዲስ መለኮታዊ ግልጠትና አስተምህሮ ያስነሳል፡፡ ከዚህ አኳያ ዳውድ፣ሙሳ፣ዒሳንና ነብዩ ሙሐመድን (ሰለላሁ ዐለይሂም ወሰለም) ዋቢ ማድረግ ይቻላል፡፡

ከላይ የዘረዘርናቸው ነብያት ሲነሱ ቀድሞ ከነበሩ መለኮታዊ አስምህሮዎች አኳያ የተለወጡና በዘመናቸው ለነበሩ አማኞች ከባለፈው የቀለሉ ሕግጋትና በጥቅሉ ይዘው መጥተዋል፡፡ ለምሳሌ ዒሳ በአንድበቱ ሲናገር አንዳንድ እርም የተደረጉባችኹን ላበቃላችኹ መጣኹ ብሏል፡-
وَلِأُحِلَّ لَكُم بَعْضَ الَّذِي حُرِّمَ عَلَيْكُمْ

፫ኛ) አላህ አንድን ነብይ ለሌላኘው ነብይ አጋዥ ኾኖ እንዲነሳ የሚያደርግበትም ኹኔታዎች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ነብዩ ሃሩን ለነብዩ ሙሳ (ዐለይሂማ አሰላም) አጋዥ ኾኖ ተነስቷል፡፡ ገና ሙሳ ነብይ ኾኖ ሲነሳ ወንድሙን ሃሩንን አጋዥ እንዲያደርግለት አላህን ለምኗል፡-
وَاجْعَل لِّي وَزِيرًا مِّنْ أَهْلِي (29) هَارُونَ أَخِي (30) اشْدُدْ بِهِ أَزْرِي

፬ኛ) አንድ መለኮታዊ አስተምህሮ አንድ ቦታ ላይ ከቀረና መስፋፋት ካለበት አላህ በተመሳሳይ አስተምህሮ ሌላ ቦታ ላይ ሌላ ነብይን ያስነሳል፡፡በአንድ ዘመን የሚነሱ ነብያት እንደየ አካባቢው ኹኔታ በስብከታቸው ትኩረት የሚያደርጉበት ኹኔታ ሊለያይ ይችላል፡፡ ከዚህ አኳያ ነብዩ ሉጥንና ኢብራሂምን ማንሳት ይቻላል፡፡

እንግዲህ በጥቅሉ ከላይ ያነሳናቸው አራት ነጥቦች ነብያት እንዲነሱ ገፊ ምክንያት ተደርገው የሚታሰቡ ናቸው፡፡

ታዲያ ወዳጄ እነዚህ አራት ነጥቦችን ይዘን ከነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በኋላ ሌላ ነብይ ያስፈልጋልን? ብለን ስንጠይቅ መልሱ በጭራሽ አያስፈልግም የሚል ይኾናል፡፡

የነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አስተምህሮ እያበራ እንጂ እየከሰመ አይደለም! ስለኾነም በመጀመሪያው መስፈረት መሰረት ሌላ ነብይ አያስፈግም፡፡

የነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አስተምህሮ ከኹሉም ዘመን ትውልድ ጋር የሚስማማ ስለኾነ እነሆ ዛሬም ከሺህ አራት መቶ ዓመታት በኋላ እንኳ እየኖርንበት ነው፡፡ ስለዚህ ሌላ ነብይ አያስፈልግንም!!

ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሕይወት እንኳ እያሉ በአስትምህሮአቸው አጋዥ ኾኖ የተነሳ ሌላ ነብይ አልነበረም፡፡

በሃያ ሶስት ዓመታት ውስጥ ብቻቸውን ነብይ ኾነው ለኛም ጭምር የደረሰ መለኮታዊ ራዕይ ድልድይ ኾነው አድርሰውናል፡፡ ያኔ ነብይ ካላስፈለገ ዛሬ አጋዥ ሊኾናቸው የሚችል ሌላ ነብይ አያስፈልግም!!!
https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ከጉረባዕ ኢስላማዊ ድርጅት ጋር በመተባበር ላለፉት 6 ሳምንታት ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል። በስልጠናው መሠረታዊ የንጽጽር አስተምህሮ የተዳሰሰ ሲሆን በቀጣይ በትብብር ስለሚሰሩ ስራዎችም ውይይትና ስምምነት ላይ ተደርሷል። ማዕከሉ ከሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር የሚሰጣቸው ስልጠናዎችም በአላህ ፍቃድ ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

© ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል
https://youtu.be/wJ8isMRD_xQ?feature=shared
ነብያት ኃጢአት ካልፈጸሙ ነብዩ ሙሳ ሰው ለምን ገደለ?
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እስልምና ላይ የሚቀርቡ ጥያቄዎችንና በሀይማኖት ንጽጽር ዙሪያ የሚሰሩ ስራዎችን ጥልቅ በሆነ መልኩ ስራዎችን ለመስራት እንዲያግዝ በማሰብ ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በስሩ የጥናትና ምርምር ዘርፍ አቋቁሟል።

በዚህ ዘርፍ ውስጥ የንጽጽር ዱዓቶችን ጨምሮ ተተኪ ወንድምና እህቶች ሰፊ ጊዜዎችን በመውሰድ ስራዎችን እንዲያጠኑ፣ በየቋንቋቸው የጥናት ውጤታቸውን እንዲያዘጋጁ በማመቻቸት ላይ ይገኛል።

ለስራውም በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ አረብኛ እና እንግሊዝኛ የተጻፉ መጽሀፍትን ለማሟላት ጥረት እየተደረገ ሲሆን ለዚህ የሚያግዙ እናንተ ጋር የተቀመጡና ለተቋማችን ይጠቅማል የምትሏቸው መጽሀፍት ካሉ በሚከተለው ስልክ ቁጥር ለአስተባባሪዎች በመደወል መስጠት የምትችሉ ሲሆን ቢሮ መጥቶ መስጠት የሚችሉም ይበረታታሉ።

አድራሻ፦ ቤተል
ስልክ፦ 0910858830
ዓለም በ2050 ምን ትመስላለች?
ክፍል (፩)
….
አደም (ዐለይሂ አሰላም) ምድርን ተረክብ መኖር ከጀመረበትና መሰሉን ከተካበት ማግስት አንስቶ “አልባጢኒዩን” “esoterics” በአማርኛችን “ሚስጠረኞች” የሚባሉ ኅቡእ- ሕዋሶች እንደነበሩ ይነገራል፡፡

በኢስላም ታሪክ ውስጥ “አልባጢኒያ” የሚለው ቃል በተለያየ ዘመን የተነሱ አኹንም ድረስ ሕልውና ያላቸው ከኪታብና ሱና አኳያ ያሉ ማስረጃዎች ወይም አስተምህሮዎች በጥቅሉ ከላይ ከላይ ያለው ትርጓሜያቸው ሳይኾን የሚፈለገው ጥቂት ሰዎች ብቻ የሚያውቁት ለየት ያለ ትርጉም አላቸው ብለው የሚያምኑ ጭፍሮችን የሚወክል ነው፡፡ ከባጢኒያዎች አኳያ ከዚህ ቀደም የበሻር ቤተሰቦች -ኑሰይሪያዎችን አንስተን ሰፋ ያለ ወግ አውግተናል፡፡

ዛሬ ላይ ይህ “አልባጢኒያ” የሚለው ኃይለ-ቃል ሰፋ ባለ መልኩ ኹሉንም በውስጣቸው ሌላ አስተምህሮ ይዘው ከላይ ከላይ በሌላ መልካም በሚመስል ስም የተቀቡ ኅቡእ (ሚስጢራዊ) ቡድኖችንና እንቅስቃሴዎችን በሙሉ የሚያካትት ኾኖ እናገኘዋለን፡፡

ዘመናዊው “ሚስጠረኛነት” በውስጡ አምስት ልምምዶችን በተለያዩ ስያሜዎች አቅፎ ይገኛል፡፡ በዚህ ተከታታይ ጽሑፍ እነዚህን አምስቱንና ሌሎችንም በውስጡ የሚጠቃለሉ ሕሳቦወችን እናነሳለን፡፡

፩ኛ) ጥንቆላ-ትንቢት--ስነ-ከዋክብት

ይህ ለምምድ ቀደም ሲል ከመናፍስት ጋር እንገናኛለን በሚሉና በትክክልም በሰይጣናት በሚታገዙ አካላት ይፈጸም የነበረ ነው፡፡ በምዕራቡ የሚዘወረው አልባጢኒያ አኹን ላይ ይህንን ልምምድ እጅግ በማዘመን በተለያየ መልኩ ትንበያና ጥንቆላ ሲፈጽም እናያለን፡-

ሀ) ሰው ሰራሽ ክሕሎትን (AI) በመጠቀም
የከዋክብትን መውጫና ተጽእኖ ማጥናት
....

ይህ ዘመናዊው ልምምድ ከዋክብት የሚወጡበትን ጊዜ ካጠና በኋላ መውጣታቸውን ተከትሎ የሚያመጡትን ተጽእኖ የሚተነብይ ነው፡፡ ይህ ተጽእኖ እንደ አልበጢኒያዎች ሕሳቤ ግለሰባዊም ሐገር አቀፋዊም ሊኾን ይችላል፡፡

መታወቅ ያለበት ነገር ይህን ዘዴ ዘመናዊና በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ያደረገው ቀደም ሲል የነበሩ ዳታዎችን በመጠቀምና የከዋክብቶችን አዋጣጥና አጠላለቅ ከፕላኔቶች አቀማመጥ ጋር በማጣመር የሚፈጸም ትንቢት መኾኑ ነው፡፡

ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከመነሳታቸው ቀደም ሲል በጃሂሊያ የነበረው ማሕበረሰብ የኾነ የወጣ ኮከብ ካለ ዝናብ ይዘንባል፤ የጠለቀ ኮከብ ካለ ደግሞ የኾነ ነገር ሊከሰት ይችላል እያለ ያምን እንደነበረ ልብ ይሏል፡፡

ከዚህም አኳያ ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በከዋክብት መጠጣት (إستسقاء بالنجوم) በአላህ ላይ ማጋራት መኾኑን አስተማሩ፡-

صَلَّى لَنَا رَسولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ صَلَاةَ الصُّبْحِ بالحُدَيْبِيَةِ علَى إثْرِ سَمَاءٍ كَانَتْ مِنَ اللَّيْلَةِ، فَلَمَّا انْصَرَفَ أقْبَلَ علَى النَّاسِ، فَقالَ: هلْ تَدْرُونَ مَاذَا قالَ رَبُّكُمْ؟ قالوا: اللَّهُ ورَسولُهُ أعْلَمُ، قالَ: أصْبَحَ مِن عِبَادِي مُؤْمِنٌ بي وكَافِرٌ، فأمَّا مَن قالَ: مُطِرْنَا بفَضْلِ اللَّهِ ورَحْمَتِهِ، فَذلكَ مُؤْمِنٌ بي وكَافِرٌ بالكَوْكَبِ، وأَمَّا مَن قالَ: بنَوْءِ كَذَا وكَذَا، فَذلكَ كَافِرٌ بي ومُؤْمِنٌ بالكَوْكَبِ

ዘይድ ቢን ኻሊድ በሚያወራው ሐዲስ “መልክተኛው ሑደይቢያ ላይ የሱብሂን ሷላት አሰገዱን፡፡ ያን ለሊት ዝናብ ዘንቦ ነበርና ዝናቡን ተከትሎ መልክተኛው “ጌታችኹ ዛሬ ምን እንዳለ ታውቃላችኹን?” ብለው ጠየቁ። ሰሓባውም አላህና መልክተኛው የበለጠ ያውቃሉ ብለው መለሱ፡፡ መልክተኛውም ቀጠሉና “አላህ ከባሪያዎቼ በኔ አምኖ በኔም ክዶ ያደረ አለ፡፡ በአላህ ትሩፋት ተዘነብን ያለ በኔ አምኖ በኮከብ የካደ ነው፡፡ በኾነ ኮከብ ምክንያት ተዘነብን ያለ ደግሞ በኔ ክዶ በኮከብ ያመነ ነው ብሎ ተናገረ”

በስነ-ፈለክ ( علم الفلك) ትምህርት እንደምንማረው ከዘፍጥረት ጀምሮ በእያንዳንዱ ወር የሚወጡ ከዋክብት አሉ፡፡ ለምሳሌ በያዝነው በሻዕባን ወር አጋማሽ ላይ “አልሃንዓ” የሚባል ኮከብ ይወጣል፡፡ በዚህ ኮከብ መውጣት ምክንያት እንደ ስህተተኞቹ ኮከብ ቆጣሪዎቹ አመለካከት የኾነ ለውጥ በምድር ላይ ሊመጣ ይችላል ተብሎ ያታሰባል፡፡

ኮከቡን ለይተው የሚያውቁ ቆጣሪዎች ታዲያ የኮከቡን መውጣት ተከትለው በርካታ ውሸቶችን ይተነብያሉ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የዛሬዎቹ ተንባዮች ሰው ሰራሽ ክሕሎትን ተጠቅመው መሰል ትንበያዎችን ያደርጋሉ፡፡
….
ይቀጥላል

https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
ዓለም በ2050 ምን ትመስላለች?
ክፍል (፪)
…..

ቀደም ሲል በዚህ ርዕስ ክፍል አንድ ላይ በሻዕባን አጋማሽ ላይ ስለምትወጣው “አልሃንዓ” ስለምትባል ኮከብ የተወሰነ ነገር አንስተን ተነጋግረናል፡፡

ኮከብ ቆጣሪዎች በአጠቃላይ የሰማዩን ቀበሌ በአስራ ኹለት ክፍሎች (አብራጅ)ከፋፍለው ያጠኑታል፡፡ እነዚህ በአስራ ኹለት የተከፋፈሉት ቡሩጆች ሲገጣጠሙ የክብ ቅርጽ ይሰራሉ፡፡ እያንዳንዱ ቡሩጅ ከኾነ ወር አንስቶ እስከ ሚቀጥለው ወር ድረስ ያለ ጊዜን ያካትታል፡፡ ለምሳሌ “አልሓምል” የሚባለው ቡሩጅ ከመጋቢት 21 እስከ ሚያዝያ 19 ድረስ ያለውን ይወክላል፡፡ በእያንዳንዱ ቡርጅ ውስጥ የተለያዩ ከዋክብት በተለያየ ጊዜ ሊወጡ ይችላሉ፡፡

በዚህ ስነ-ፈለክ ትምህርት ውስጥ በአጠቃላይ 10 የከዋክብት ዓይነቶች ሲገኙ እነዚህ ከዋክብት ደግሞ በ12 ቡሩጆች ውስጥ በተለያየ ጊዜ ሊወጡ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ “ዓጣርድ” የምትባለው ኮከብ “አልጀውዛእ” በምትባለው ቡሩጅ ስትታይ ኮከቧ “የማሰላሰል” ና “የብቃተ ሕሊና” መገለጫ ስለኾነች፣አልጀውዛእ የምትባለው ቡሩጅ በምትወክለው የወራት ጊዜ ውስጥ (ግንቦት 21 -ሰኔ 20) የተወለደ ሰው በቀጣይ ቀናት የበለጠ የማሰላሰልና የሕሊና ብቃት ላይ እንደሚደርስ ብሎም በሕይወቱ የተሻለ አማራጮችን እንደሚጎናጸፍ ይታሰባል፡፡

ኢስላም ቡሩጅን በተለያዩ ወራት ከፋፍሎና ከዋክብትንም በስም ለይቶ ማጥናት ዘመንና አቅጣጫን ከማወቅ አኳያ እንደሚቻል ያስተምረናል፡-

وَعَلَامَاتٍ ۚ وَبِالنَّجْمِ هُمْ يَهْتَدُونَ /النحل 16

ከዋክብት በራሳቸው ተጽእኖ ኣላቸው ብሎ ማሰብና መውጫቸውን እየጠበቁ የወደፊት ገጠመኞችን መጠባበቅ ወይም ይከሰታሉ ተብሎ ከሚታሰቡ ግምቶች አኳያ ጥንቃቄዎችን ለማድረግ መሞከር በአላህ ላይ በግልጽ ማጋራት ነው፡፡

ዛሬ ላይ ይህ የኮከብ ቆጠራ አስቀድመን እንዳየነው እጅግ ዘመናዊ በኾነ መልኩ በእደ- ጥበብ (ቴክኖለጂ) በመታገዝ ጭምር በሰፊው እየተሰራበት ይገኛል፡፡ እዚህ ጋር አያይዘን ስለ አየርና የርዕደ-መሬት ትንበያዎች እናወጋለን፡፡

የአየር ንብረት ትንበያዎችን ምንም ውስብስብ እደ-ጥበቦችን ሳንጠቀም በግላችን ወደ ኋላ ኼድ ብለን የተወሰኑ ዓመታት ዳታዎችን መሰብሰብ ከቻልን ለምሳሌ በያዝነው የጥር ወር መጨረሻ አካባቢ ሙቀቱ ምን ያሕል ሊኾን እንደሚችል መናገር እንችላለን፡፡ ምናልባትም ዝናብም ካለ ያለፈውን መረጃ መሰረት አድረገን ልንተነብይ እንችላለን፡፡

ይህ ቀላል አካሄድ በእደ-ጥበብ ከታገዘ ደግሞ የተሻለ ትንበያ መኾን ይችላል፡፡ መታወቅ ያለበት የአየር ንብረት ትንበያ ዳታዎች ላይ ብቻ የሚንጠለጠልና ሊኾን ይችላል የሚል ሒሳባዊ (ስታቲስቲክሳዊ) ጥቆማ ብቻ ነው፡፡ ስለኾነም ሊሳካም ላይሳካም ይችላል፡፡

ከርዕደ-መሬት አኳያም ያለው ትንበያ ከዚህ የዘለለ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ቀደም ሲል እ.ኤ.አ 2023 ፍራንክ ሁገር ቢትስ (Frank Hoogerbeets) የሚባል የሆላንድ ተወላጅ ከበድ ያለ ርዕደ-መሬት ምድር ላይ እንደሚከሰት ተናግሮ ነበር፡፡ ኾኖም ግን የግለሰቡ ትንቢት ቦታን ነጥሎ እዚህ ሐገር ላይ ርዕደ-መሬት ይከሰታል የሚል አልነበረም፡፡

በኋላ ላይም ፍራንክ እንደተነበየው በሶሪያና ቱርክ ላይ ከበድ ያለ ርዕደ-መሬት ተከስቷል፡፡ ሁገር ይህንን ትንቢት እንዴት አስቀድሞ መናገር ቻለ? የሚል ጥያቄ ከተነሳ፣ በዘርፉ ልሒቃን ዘንድ ብዙም ተቀባይነት የሌለውን ምድራዊ-ዘዋሬ (planetary geometry) የሚባል ኅልዮትን (ቲዮሪ) በመጠቀም ነበር ትንቢቱን የተናገረው፡፡

ይህ ምድራዊ-ዘዋሬ የተሰኘው ኅልዮት የፕላኔቶች፣ጸሐይና ጨረቃ አቅጣጫ በምድር ንጥነጣዊ ገጽ ላይ (tectonic plates) ጫና ያሳርፋል፡፡ ጫናው ደግሞ በተዘዋዋሪ በፕላኔታችን ምድር ላይ ርዕደ-መሬት ያስከትላል የሚል ነው፡፡

ሁገር ምንም እንኳ ያ ጥቅላዊ ትንቢቱ ቢሳካም በተመሳሳይ መልኩ የተናገራቸው በርካታ ያልተሳኩ ትንቢቶች ነበሩት፡፡ ለምሳሌ በ2019 በምድር ላይ የኾነ ቦታ በሬክተር ስኬል 8 የሚደርስ ኃያል ርዕደ-መሬት ይከሰታል በሚል አሰፈራርቶ ነበር፡፡ ኾኖም ግን በዛ ዓመት የተመዘገበው ትልቁ ርዕደ-መሬት ዲሴምበር 24 በኮሎምቢያ የነበረው ሲኾን በሬክተር ስኬልም 6 ብቻ ነበር፡፡

የፍራንክ ትንቢቶች ጥቅላዊና ዝርዝር ትንተና የሌላቸው ስለነበሩ ተቀባይነት አልነበራቸውም፡፡ ምክንያቱም የፍራንክ ዓይነት ትንበያን ማንም ሰው ያለምንም መሳሪያና ቴክኖሎጂ እግዛ መናገር ይችላል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በዚህ ዓመት ርዕደ-መሬት ይከሰታል ብሎ ቦታና ጊዜ ሳይለይ ቢናገር በትክክልም የኾነ ቦታ ርዕደ-መሬት ቢከሰት ተናጋሪውን ትክክለኛ አያደርገውም፡፡ አካሄዱም ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ፍራንክም እያደረገ ያለው ከዚህ የዘለለ አይደለም፡፡
….
ይቀጥላል
https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አማካኝነት የተዘጋጀውን ይህንን ስልጠና መውሰድ ለምትሹ ከዚህ በታች በተቀመጠው ሊንክ መመዝገብ ትችላላችሁ። እያንዳንዱ ስልጠና ለአንድ ቀን የሚሰጥ ሲሆን ከተመዘገባችሁ በኃላ በሚደወልላችሁ የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ስልክ ቁጥር አማካኝነት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በቴሌግራም ወይንም በዋትስአፕ ቀድመው መላክ ይኖርብዎታል።

- ለስልጠናው የምንፈልገው 15 ሰልጣኝ ብቻ ስለሆነ ስልጠናውን የመውሰድ እርግጠኛ እቅድ ከሌለዎት አይመዝገቡ።

https://bit.ly/4aK4Pq5
ሰውዬው እንዲህ አለ:-
إني وقتلي سليكا ثم أعقله
كالثور يضرب لما عافت البقر

ሰውዬው በኾነ ነገር ተናዶ ነበር። ንዴቱን ለመወጣት ሱለይክ የሚባል ባሪያ ገደለና ጉማውን ከፈለ።

ከክፍያው በኋላ ራሱን የታዘበ በሚመስል ቃል:-

"ሱለይክን ገድዬ ጉማ የሰጠኹ መቶ
ላሙ አልበላ ብትል ድንገት ተቆጥቶ
በሬውን የቀጣ ሰው ነኝ እንጂ ከቶ"

በማለት የምትታለበው ላሙ አልበላ ብትለው በቁጣ በሬውን ምንም ሳያጠፋ እንደቀጣ ሰው ብጤ መኾኑን ተናግሯል።

ታዲያ ወዳጄ ስንቶቻችን በሌሎች ጥጋብ ምክንያት ፈጽሞ በማናውቀው ነገር እየተቀጣን እንደኾነ ኹሉም ያውቃል።

ክልል እንኹን በሚሉ ወጣቶች ዩኒቨርሲቲ በመረበሹ ምክንያት ተማሪ አልማርም ብሎ መማሪያ ክፍል ባዶ ሲኾን ጥለኽ የተመለስኸውና ቀጥሎም ተባብረኻል በሚል የተከሰስኸው ወዳጄ እንደምን ከረምኽ?!

ከመኝታ በፊት ይህችን ለአንተ ማስታወሻ ከተብዃት። መቼም ደህና ነኽ ብዬ እገምታለኹ።

ደህና ባትኾንም መቼም በቁሙ ኑሮ ለቀበረውም ዘመዶቹ ዐፈር ምሰው ለቀበሩት ሰላምን መመኘት ደግ ነው።

አንተን ሳስብ ከቤት ቁጭ ብዬ "ዲስታንስ"፣"አክስለሬሽን" ወዘተ ...እያልኹ የማሰለቻት ልጄ ታሳዝነኛለች።

አኹን ላይ ማንም እኔና አንተን አርዐያ እንደማያደርግ በትክክል ስረዳ ሕጻን እያለን ደብተራችን ላይ "ትምሕርቲ ንሓፋሽ" የምትለው መፈክር ትዝ ትለኝና "እጭ! ውሸት ነው ...አያስፈልግም" እላለኹ።

አንዳንዴ ደግሞ የመመረቂያ ጽሑፋችንን ለማዘጋጀት ትግራይ ገጠር ውስጥ በዛ ክረምት ጸዳል ሻማ አብርተን ቆማጣ በሚያሳቅፍ ብርድ ከአልጋችን ላይ ቁጢጥ ብለን ስንሞነጭር በዓይኔ ይመጣል።

አዎ! ኹሉም አልፏል። አኹን ያለውም ያልፋል። እኛም እናልፋለን።

ወዳጄ የኾነ ቀን ጸሐይ ከነ ሙቀቷ ስትወጣ ደንዝዘኽ የቆምክበት መሬት ሲሞቅኽ መንቀሳቀስ ትጀምራለኽ ብዬ አስባለኹ።

አሳብ ብቻ እንጂ መች እንደሚኾን ግን አላውቅም። ይህንን ማሰብ ከጀመርኹም ኃያል ቀናት ነጉደዋል።

ይህችን ፍልስፍናዬን ስንከራከርባት ትዝ ካለኽ እነሆ ልገርብልኽ:-

የተማረ በሚገድል ስርዓት ውስጥ "የተማረ ይግደለኝ" የሚለው ብሂል ውሸት ብቻ ነው።

ለመኾኑ መች እድሉን አግኝቶ ነው አስኳላ የቀመሰ ሰው የሚገድለው? ያልተማረው አይደለም እንዴ ይህችን ምድር የተልባ ምጣድ ያደረጋት!?

በዚህች ሐሳቤ ስንነታረክ ሻማችን ቀልጣ በማለቋ ወደ አልጋችን እንድንሄድ ምክንያት ኾናናለች።

ፍልስፍናዬን ያኔ ባትቀበልኝም ግን ዛሬ እለት እለት እየሞትኽ አረጋግጠኸዋል።

ጨረስኹ!!!
ባለኽበት ኾነኽ ሰላም ለአንተ ይኹን ወዳጄ! ሰላም ለአንተ!!!
https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
Dual reality

Some people live on their planet, with their soul as their closest companion—finding joy in lighthearted fun.

Meanwhile, others experience daily and night as a struggle against themselves and the world around them.

Some rebel against established rules and others are oppressed by them.

For some, their days are darker than the darkest night, while for others, their nights shine brighter than the day.

The human race finds this duality of realities hard to accept, yet it has existed since the very beginning of our universe—and, if there are any, all universes.

Consider a cat playing with a dying rat: for the cat, those moments offer delight, but for the rat, each minute brings it closer to its end.

Every challenge has its value, no matter its intensity. However, some challenges are like poison—if they don’t kill you outright, they leave lasting harm.

In this fragile bubble, we call the world; some friends are as steadfast as mountains and as deep as oceans of love and joy. In contrast, many friends resemble volatile volcanoes and raging hurricanes, robbing you of happiness and replacing it with sorrow.

Very few friends stand by you through every situation, while most people tend to forget their past—especially the days marked by starvation and poverty. Instead, they build new relationships with those they perceive as matching their standards, resonating at the same frequency.

There are times when I feel content in my own company and enjoy wandering alone into unknown places. However, the innate need to share experiences ultimately compels me to interact with others.
...
This is just my feeling -Eliyah Mahmoud no hard feeling dears!

https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
ትልልቅ ጉዳዮች ትንንሽ ሐሳብ ባሏቸው ሰዎች ሲያዙ ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ይከፋል።

ግዙፍ ጉዳዮች በቁመታቸው ልክ እጅግ ትዕግስትንና ስሜት መጫንን ይጠይቃሉ።

መልዕክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ያ ኹሉ መከራ መሰደድና ሞት ድረስ በዓማኞች ላይ ሲደርስ ታላላቅ ነብያት እንደ ታገሱ ታገስ ነበር የተባሉት :-

فاصبر كما صبر أولوا العزم من الرسول


የነብያት ገድል እንደሚነግረን ኢስላምን ያለ ኹሉ በክብሩ፣በንብረቱና በሕይወቱ ጭምር ይፈተናል።

ታዲያ በፈተናዎች መካከል ስንዴና እንክርዳድ ይለያል። የተንከረደደ ዓላማ ያለው ኹሉ ገና በማለዳው ምንትስዬ ተነካ ብሎ ክብሩን ከዓላማው በላይ ሰቅሎ ሲጮኽ ይታያል።


አንድ ትልቅ ሰው ገና ወደ ዳዕዋው ለመቀላቀል የሚያስስብን ወጣት ሲመክር (ወዳጄ ረጋ ብለው ጎርነን ባለ ድምጽ ቀጣዩን ያንብቡት)

" ራስኽን ከክስተቶች በላይ አድርግ እንጂ ድብድብ ውስጥ ገብተኽ አታንቦራጭቅ።

በዳዒዎች መካከል አለመግባባት ካለ፣አስታራቂ ኹን እንጂ ወግነኽ አትናገር።

መርሳት የሌለብኽ ኹሉም ራሱን ጥግ ላይ አስቀምጦ በነብይ ልኬት ይመዝናል እንጂ በፍጹም እዚህ ጋር አጥፍቼአለኹ፣ ተሳስቼአለኹም አይልም። ስለዚህ ወግነኽ ማጥቃት ሳይኾን እየተጠለዘች ያለችውን ኳስ ለማስቆም ጣር።

በአንተ ምክንያት በዳዕዋው መስክ አዋራ ከተነሳ፣ከሜዳው ወጣ በልና ራስኽን ፈትሽ።

ምናልባት አንተ ገለል በማለትኽ አዋራው ሊቀል ሊቆምም ይችል ይኾናልና።

ልብ ብለኽ ስማኝ! ዛሬ አንተን የወገኑ ኹሉ በእጥፍ ነገ የአንተ ቀበኛዎች ሊኾኑ ይችላሉና ደጋፊኽ ስለበዛ ትክክለኛነት አይሰማኽ።

ኹሌም አንተ አጥፋም ትክክልም ኹሉ አስታራቂ ሐሳብ ያላቸው ሰዎች መልካምኽን የሚፈልጉ ናቸውና እነዚህን አጥብቀህ ያዝ። የወገኑሉኽን ሰዎች ግን በፍጹም አትመናቸው።

ኢስላማዊ ዳዕዋ ሰብሰብ ማለትን እንጂ በቡድን መካፈልንና መጫፈርን ጨርሶ አያበረታታምና ለመገነጣጠል የተመቸ አትኹን።

ወጣቱ ልጅ ሆይ! የነፍስያኽን ግግር ጣጣ ይዘኽ ወደ ዳዕዋው ሜዳ እንዳትገባ ተጠንቀቅ።

የነፍስያ ጣጣ ቦታ ከመፈለግ ጋር የተቆራኘ ነውና አንተንም ዳዕዋውንም ክፉኛ ሊጓዳ ስለሚችል አውጥተኽ ጣለው።
....

የሰውዬው ምክር ራሴን እጅግ እንድፈትሽ አድርጎኛል።

ራሴን ያልገራኹ÷ ለማለፍና ለይቅርታ ክብሬን የማስበልጥ ሰው ነኝ በዬም አሰብኹ።

ትንሽ ነፍስያዬን ያዝ ባለማድረ ትልልቅ ጥፋት እየሰራኹ እንደኾነ ተሰማኝ!!!

رب اغفر وارحم وانت خير الراحمين

https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
አንድ እብድ መስጂድ ገብቶ ኹጥባ ካላደረግኹ ሞቼ እገኛለኹ አለ፡፡ ብዙ ካስቸገረ በኋላ የመስጂዱ አስተዳዳሪ እስኪ ያድረግና እንገላገል አላቸው፡፡
እብዱ ሚንበር ላይ ወጣና፡-
"السلام عليكم ورحمة الله.
إن الله خلقكم من اثنين، وقسمكم قسمين، وجعل منكم أغنياء لتشكروه، وجعل منكم فقراء لتصبروا.
لا أغنياؤكم شكروا، ولا فقراؤكم صبروا!
لعنة الله عليكم أجمعين... قوموا إلى صلاتكم

“አላህ ከኹለት ነገር ፈጠራችኹ፤
ለኹለትም ከፋላችኹ፤
ታመሰግኑ ዘንድ ሐብታም አደረጋችኹ ፤
ትታገሱም ዘንድ ድሓም አደረጋችኹ፤
ሓብታሞቻችኹ አላመሰገኑም፤
ድሓዎቻችኹም አልታገሱም፤
የአላህ እርግማን በእናንተ ላይ ይኹን፤
ወደ ሰላት ቁሙ!!!”

በቀን አምስት ጊዜ የሚበላው ሐብታም፣ስድስት ሰባት ፍንጃል ቡናና ሻይ እየጠጣ እነ እገሌ ተቸግረዋል ሲባል “ትዕግስት ማድረግ አለባቸው…” እያለ የሰብር ዓይነቶችን ለማውራት ሲዳዳው ስታይና በሌላ ጊዜ ደግሞ “መንግስት ዕቃ ያዘብን ስራ መስራት አልቻልንም ወዘተ…” እያለ ሲያማርር ስታይ፣ ይህ ኹጥባ በትክክል ለኛ ዘመን ሰው ይመጥናል ትላለኽ፡፡

እድሜ ልኩን በሩን ዘግቶ ውሎ የሚያድረው ሐብታም በራቸው ቢከፈት እንኳ ውል የሚል ነፋስ የማይገባባቸው ድሆችን ስለ ትዕግስት የሚያስተምርበት ዘመን ላይ መድረሳችን በጀርባቸው ዱቄት ተሸክመው ለሊት ከድሆዎች ደጃፍ ማንም ሳያውቅባቸው ያስቀምጡ የነበሩት ሰለፎችን እንድንናፍቅ ያደረገናል፡፡

"اللهم أحيني مسكينًا، وتوفني مسكينًا، واحشرني في زمرة المساكين يوم القيامة."
ንጉሱና እብዱ
...

ንጉሱ እብዱን ይጠይቀዋል፦
በኢስላም ሕግ የሰረቀ ሰው ፍርዱ ምንድን ነዉ?

እብዱም፦ ሌባው የሚሰርቀው ስርቆትን እንደ ሙያ ይዞ ከኾነ እጁ ይቆረጣል። ተርቦ ከኾነ ግን የሚሰርቀው የንጉሱ እጅ ይቆረጣል!!! አለው።
...

ወዳጄ ይህንን ቃለ-ምልልስ ልብ ካሉና ወደ መሬት አውርደው ካሰቡት ጠኔ ገፍቶአቸው ከሰው ኪስ የተገኙ በርካታ ሰዎች አሉ።

በተለይ ዛሬ ዛሬ መንግስት ራሱ ድሐ እየፈጠረ ባለበት ተጨባጭ ስርቆት ቢበዛ መቆረጥ ያለበት እጅ የማን እንደኾነ ግልጽ ነው።

በየመስኩ ያለውን ሙስናና ዝርፊያ ለማስቀረት መንግስት ምጣኔውን (ኢኮኖሚ) ማረጋገት የቅድሚያ ስራው ካልኾነ በቀጣይ ችግሩና ስርቆቱ የበለጠ መናሩ አይቀርም።

በዑመር ኸሊፋነት ዘመን እጅግ ድርቅ የተከሰተበት አጋጣሚ ነበር።

ድርቁን ተከትሎ እጅግ ስርቆት በዛ። ኾኖም ግን ኸሊፋው ዑመር የሌቦችን እጅ መቁረጥ አልፈለገም።

ዑመር እጅ መቁረጥ ያልፈለገበት ምክንያት ግልጽ ነዉ። ሌቦቹ ችግር ገፋቸው እንጂ ሌብነት ሙያቸው ኾኖ አልነበረም።

በተመሳሳይ መልኩ ዛሬም ላይ ያለው "ሌባ" ኹሉ "ሌባ" ኾኖ እንዳልኾነ ልብ ይሏል።

በፕሮፌሽን ደግሞ ሌቦች የኾኑ ኅልቆ መሳፍርት ናቸው።

መቆረጥ ያለባቸውም ከደቂቅ እስከ ትላልቅ ሹማምንት በየቀበሌው አሉ። የነዚህ እጅ ካልተቆረጠ የዚህች ሐገር ነዋይ ኹሉ ተበዝብዞ መሟጠጡ አይቀርም።

https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
Look Not for Beauty
.....

Look not for beauty, nor fairness of skin,
But seek the heart that’s loyal within.
Beauty may fade, and youth grow old,
Yet a faithful heart stays true and bold.
Wrinkles may come, and colors may change,
But love that’s pure will never estrange.
For time may steal the glow of youth,
Yet steadfast love remains the truth.

...

For those who are crazy about skin color and beauty

https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
ዓለም በ2050 ምን ትመስላለች?
ክፍል (፫)
….
የካርድ ጥንቆላ - “አታሩት”
….
ጥንቆላ ከተጀመረበት ዘመን አንስቶ እስካለንበት ዘመን ድረስ የተለያየ መልክ ይዞ ቀጥሏል፡፡ በከዋክብት መጠንቆልን አስቀድመን በክፍል ኹለት ተነጋግረንበታል፡፡

በዚህ ከፍል ደግሞ “አታሩት” እየተባለ የሚታወቀውን የካርድ ጥንቆላ እንመለካታለን፡፡ “አታሩት” በአውሮጳ በ15ኛው መቶ ክፈለ ዘመን ካርዶችን በመምዘዝ የሚከናወን የጨዋታ ዓይነት ሲኾን በኋላ ላይ ግን በተለይ ከ18ኛው መቶ ክፈለ ዘመን ወዲህ አንስቶ ወደ ጥንቆላዊ ልምምድ ከፍ ብሎ እየተሰራበት ይገኛል፡፡

“አታሩት” በአጠቃላይ 78 ካርዶችን የሚይዝ የጥንቆላ ልምምድ ነው፡፡ እነዚህ 78 ካርዶች “ዐቢይ አርካና” እና “ንዑስ አርካና” በሚል በኹለት ይከፈላሉ፡፡

“ዐብይ አርካና” የሚባለው በሕይወት ውስጥ ላሉ ትላልቅ ክስተቶች ለምሳሌ ሞትን፣ሕይወትን፤ፍቅርንና ሌሎችንም የሚወክሉ 22 ካርዶችን ያጠቃልላል፡፡

“ንዑስ አርካና” የሚባለው ደግሞ በጦር፣ዋንጫ፣ሰይፍና ሳንቲም የሚከፋፈሉ 56 ካርዶችን ያጠቃልላል፡፡ ይህ ንዑስ አርካና በየቀኑ ያሉ ክስተቶችን የሚወክሉ ካርዶችን ስለሚይዝ ዕለታዊ ትንቢቶችና ጥንቆላዎችም ይፈጸሙበታል፡፡

ምናልባት ይህ በጨዋታነት የተጀመረው አታሩት እንዴት ወደ ጥንቆላ ሊያድግ ቻለ? የሚል ጥያቄ ከተነሳ አስቀድመን እንዳነሳነው አታሩት በ18ኛ መቶ ክፍለ ዘመን ወደ ጥንቆላው ልምምድ ከፍ ብሏል፡፡ በ19ኛውና 20ኛው ከፍለ ዘመን ላይ ደግሞ አይሁዶች በሱለይማን (ዐለይሂ አሰላም) ዘመን ድግምት ይሰራባቸው ከነበሩት “ካባላስ” ከሚባሉ መጣጥፎችና ከባጢኒያ ጋር እየተዋዛ በከፍተኛ “እድገት” የጥንቆላ ልልምምዶሽ ውስጥ ተቀላቅሏል፡፡

ዛሬ ደግሞ ይሕ አታሩት በስነ-ልቦና ልሒቃል ዘንድ ከሐርምሞና (meditation) ማሰላሰል ጋር አያይዘው ውስጠ-ልቦናን “ለማከም” እየተጠሙበት የሚገኝ ዘመናዊ ጥንቆላ ነው፡፡

አታሩትን እንዴት ነው ለጥንቆላ የሚጠቀሙበት?
….
አታሩትን ለጥንቆላ የሚጠቀሙ ግለሰቦች እነሱን ለማስጠንቆል የሚጎበኝ ሰው ካለ ካርታዎቹን በመጣል ካርታው የሚጠቁመውን ነገር ለግለሰቡ ይነግረውና ከዛ አኳያ ቀጣይ የሕይወት ጉዞውን እንዲያስብበት ያደርገዋል፡፡

በመልክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘመን አታሩት እንደ ዛሬው ካርታ በመጣል ሳይኾን “የገድ እንጨቶችን” በመጣል የሚደረግ የጥንቆላ ዓይነት እንደነበር ልብ ይሏል፡፡ ይህንን አካሄድ ቁርኣን ከመጠጥ፣ከቁማርና ጣዖት አምልኮ ጋር በማጣመር የሸይጧን ስራ እንደኾነ ልንርቀውም እንደሚገባ ነግሮናል፡-

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّمَا الْخَمْرُ وَالْمَيْسِرُ وَالْأَنصَابُ وَالْأَزْلَامُ رِجْسٌ مِّنْ عَمَلِ الشَّيْطَانِ فَاجْتَنِبُوهُ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
90/المائدة

እነዚያ በመልከተኛው ዘመን ይጣሉ የነበሩ እነጨቶች (አዝላም) ሶስት መልክ ነበራቸው፡፡ አንደኛ “ይሳካል”፣ኹለተኛው “አይሳካም” ሶስተኛው “የታወቀ ነገር የለም” የሚል ነበር፡፡ ዕጣው እንዲጣልለት የፈለገ ዕጣው ወደ ሚጥለው ሰው መጥቶ የሚከፍለውን ይከፍልና እንዲጣልለት ያደርጋል፡፡

ዕጣው ሲጣል “አይሳካም” የሚል ከወጣ ዳግም ሌላ ገንዘብ ከፍሎ እንዲጣልለት ያደርጋል፡፡ በዚህ መልኩ የሚፈለገው ዕጣ እስኪወጣ ድረስ እያስጣለ ይቀጥላል፡፡

አልባጢኒያ ዛሬ ላይ በበርካታ መልኮች ራሱን ሰውሮ እየሰራ የሚገኝ ኅቡዕ ሕዋስ ነው፡፡ ብዙዎቻችን ግን መረዳት ባለብን ልክ የተረዳነው አይመስልም፡፡ በአላህ ፈቃድ በዚህ ተከታታይ ጽሑፍ መነሳት ያለበትን ኹሉ እያነሳን እንሄዳለን፡፡ ግን ወዳጄ አንድ ነገር ላሳስቦ እወዳለኹ፡፡ ይህንን ጽሑፍ ሳዘጋጅ አስቀድሜ በዓቂዳ ኪታቦች በኡስታዞቼ የተማርኹትን ይዤ አዳዲስ ነገራትንም አንብቤ እንጂ እኔ በዚህ ልምምድ ውስጥ ስላለኹ ወይም ስለነበርኹ አይደለም፡፡

ኣንዳንዶች ከሩቅ በምጽፋቸው ልምምዶች የጠረጠሩኝ አልጠፉም፡፡ እንግዲህ ሰው ለምን ጠረጠረ ባይባልም በኩፍር መጠርጠር ግን አደጋ አለውና አንዳንዶች ግልምጫችኹን ብትቅነሱ መልካም መስሎ ይታየኛል፡፡ ካልኾነ መሰል ጽሑፎቼን አለማንበብ ሙሉ መብት አሎትና መብቶን ይጠቀሙበት፡፡ እኔ ግን ገና ብዙ የማወራው አለና እንዲህ በአጓጉል ግልምጫ አልቆምም፡፡

ወዳጄ እርሶ ከቻሉ ይህንን ጽሑፍ ሌሎችም እንዲያነቡት በማድረግ ዓቂዳን ከሚሸረሽሩ ጉዳዮች በዙሪያዎ ያሉትን ለመታደግ ይሞክሩ፡፡
والله الموفق

https://www.group-telegram.com/E_M_ahmoud.com
2025/02/22 00:55:55
Back to Top
HTML Embed Code: