Telegram Group Search
” ማንም ሰው ሌላውን ሰው በዘሩ እና በቆዳው ቀለም ወይም በሃይማኖቱ እንዲጠላ ሆኖ አልተወለደም
ሰዎች መጥላትን ተምረውት ነው ።
የሰው ልጅ ጥላቻን ከተማረ ፍቅርንም መማር ይችላል ።
እንደውም ፍቅር ለሰው ልጅ ተፈጥሮ ከጥላቻ ይልቅ ቅርብ ነው ።

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
*ምን አለበት**** (ሳሙኤል አዳነ)
     አሁን ምን አለበት ...
 ሰው እንዳሻው ቢኖር
    በራሱ ዳር ድንበር ፣
በልበ ጥፉዎች
       ልብ ባይሰበር ።

እውነት ምን አለበት ...
    ሜዳውን ፈልጎ ዳገቱን ለወጣ፣
ሌላ መሰናክል
      ሌላ እክል ባልመጣ ።
ምን አለበት
      ሰው ከገንዘብ በላይ
ለፍቅር ቢታደል፣
   በምንዝር አለቃ ፍትህ ባይጓደል ።
ቢቻል ለፈጣሪ ባይሆን ለህሊና፣
     ምናል  ይሄ ትውልድ  ለክፋት ባይቀና።

እውነት ምን አለበት ...
        በውዥንብር አለም
ግራ ባይገባ፣
ቁማር ባይጫወት
       ሰው ከግዜሩ ጀርባ ።

ምን አለበት...
       ላዳም የተሰጠው
የማፍቀር  ልቦና ።
        ዛሬም በዚህ ጊዜ ቀጥሎ ቢፀና።

 እውነት ምናለበት ...
   ሰውን በ ሰውነት
              ሁሉ ባከበረ ፣
    ግን በሚል አንድምታ
               ተቃርኖ ባልኖረ  ።
.....
ይገርመኛል ....
    ሰው በትምህርት አለም
              ጎልቶ እየዘመነ ፣
     በጭላንጭል እውቀት
                በራሱ መስተዋል
                  እየተማመነ ፣
     ከጥቁር ሀሳብ ጋር
                አብሮ እየዳመነ ፣
    ትናንትን ተወና
               የባቶችን ፀጋ
                የበረከቷን ቀን ፣
      በጦር አውድማ ላይ
        ተጨንቆ  እየዋለ
         ያድራል በሰቀቀን ..

እና ምን አለበት
      ሰው መነሻውን ቢያቅ
                  ትናንትን በይረሳ ፣
       በአምላክ ፍጡር ላይ
                   እጁን ባያነሳ ፣
    አውነት ምን አለበት
             በአባቶች ልቦና ፤
             በአባቶች እግር ፤
             መራመድ ቢበጀው ፣
ይሄን ጭንቅ ጊዜ
             በጥበብ ቸሻግሮ
              በፍቅር ቢዋጀው።

ምን አለበት ??????????......
 
07/09/2011
 ከምሽቱ 2:45
አ.አ
@TIBEBnegni
@sam2127




            



             

          
              
  
               



 
💰ብዙዎች ባሁኑ ሰአት በስልካቸው ብቻ በሺዎች ብሎም መቶሺዎችን እያገኙበት ያለ ስራ💰

FIAS

በሀገራችን በቅርቡ የገባ እና በኮሚሽን የሚሰራ የማስታወቂያ ድርጅት ነው።
* ከተለያዩ የሶሻል ሚዲያ ኔትዎርኮች ጋር ይሰራል።

በቀን ውስጥ የተለያዩ ስራዎችን ለተመዘገቡ አባላቶቹ ይሰጣል። ስራዎቹ እጅግ በጣም ቀላል ናቸው። ክሊክ ማድረግ ብቻ ነው። በዛ ቢባል 5 ዲቂቃ ቢወስዱ ነው። አንድ አባል የሚሰጠው የስራ ብዛትና የሚያገኘው ብር እንደ ደረጃው ይለያያል። ደረጃዎቹ VIP-0, VIP-1, VIP-2, VIP-3, VIP-4, & VIP-5 ናቸው።

1. VIP 0
* አንድ አባል ገና እንደተመዘገበ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 3 ስራዎችን ብቻ ነው።
* ለአንዱ ስራ 5 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 15.00, በወር 450.00, ይሰራል
* ብር ለማውጣት አፕግሬድ ያደርጋል።


2. VIP 1 🥇
* ይህ ደረጃ አባሉ 1,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 4 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 6 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 24 ብር, በወር 724.00 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

3. VIP 2 🥇🥇
* ይህ ደረጃ አባሉ 3,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 6 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 16 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 84 ብር, በወር 2,520 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

4. VIP 3 🥇🥇🥇
* ይህ ደረጃ አባሉ 6,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 11 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 16 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 176 ብር, በወር 5,280 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።
5. VIP 4 🥇🥇🥇🥇
* ይህ ደረጃ አባሉ 10,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 17 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 18 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 306 ብር, በወር 9,180 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

6. VIP 5 🥇🥇🥇🥇🥇
* ይህ ደረጃ አባሉ 30,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 38 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 25 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 905 ብር, በወር 28,500 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም ፖኬጆች የ ሪፈራል (Invitation ) አዋርድ አላቸው ይሄም እስከ ሶስት ደረጃ ይሄዳል።

ባሁኑ ሰአት ቢዝነሱ ገና ሀገር ውስጥ በመታወቅ ላይ ያለ በመሆኑ ብዙዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ህይወታቸውን የሚቀይር ገቢ እያገኙበት ይገኛሉ

ከታች ባለው ሊንክ ገብተው መጀመር ይችላሉ
👉https://fias777.com/#/pages/register?invite_code=JY4jgVUR&t=1651659645281

➲ ስልክቁጥር ሲያስገቡ ከ 9 ይጀምሩ
➲ Verification Code ሚለው ላይከጉን ቦክሱ ውስጥ ያለውን ፅሁፍ ያስገቡ


በነዚህ የፈለጉትን መረጃ ማግኘት ይችላሉ

Remember
➲ ያለምንም ክፍያ መጀመር ይቻላል
➲ paid marketer ለመሆን በ 1000 ብር መጀመር ይቻላል
➲ በአሁኑ ሰአት 2 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በመቶ ሺዎች እያገኙ ያሉ ሰዎች አሉ

Dont miss the opportunity !
በነዚህ የፈለጉትን መረጃ ማግኘት ይችላሉ

➲ 0975361399
fias.worldbusiness.work
https://www.group-telegram.com/fiaseth - join
እርስዋም አንተ አይሁዳዊ ስትሆን ሳምራዊት ከምሆን ከእኔ ውኃ ትለምናለህ? አለችው፡፡ እንዲህ ነው ነገሩ፡፡ የቆሰለች ነፍስ ስለ ዘር ታወራለች፡፡ ተስፋ የቆረጠች ነፍስ የዘር ጉዳይ ሲሆን ልሳንዋ ይከፈታል፡፡ ውኃ ለማጠጣት ዘር መጠየቅን ምን አመጣው፡፡ ውኃው አይሁዳዊ ነው? ወይንስ ሳምራዊ? ውኃ ጠማኝ የሚል ሁሉ ውኃ ይገባዋል እንጂ ዘሩ አይጠየቅም፡፡ እርስዋ ግን ጠየቀችው፡፡ በእርግጥ ይህች ሳምራዊት ሴት ይህን ጥያቄ የጠየቀችው ክርስቶስ መሆኑን ከማወቅዋ በፊት ነበር፡፡ ክርስቶስ መሆኑን ካወቀች በኋላ ግን ስለ አይሁዳዊነትና ስለ ሳምራዊነት ስትናገር አልተሰማችም፡፡ ‘’አንተ አማራ ስትሆን ጉራጌ ከምሆን ከእኔ ውኃ ለምን ትለምናለህ?’’ ‘’አንቺ ኦሮሞ ስትሆኚ ትግሬ ከምሆን ከእኔ እንዴት ውኃ ትለምኛለሽ?’’ በሚል ጥያቄ ሀገሩን ያጨናነቁተ ክርስቶስን ያወቁ ክርስቲያኖች መሆናቸው ግን ልብን የሚሰብር እውነታ ነው፡፡ በዚህ ጠባያችን እንደ ክርስቲያን ሳንኖር እንደ ክርስቲያን ልንሞት መሆኑ ምንኛ ያሳዝናል?

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
+ ዝም ብለን የምንጠላው ሰው +

ከሩቅ የምናውቀው አንዳንድ ሰው የለም? ብዙም አናውቀውም:: ቀርበን አውርተነው አናውቅም:: ስናየው ግን እንዲሁ ደስ የማይለንና ያለ ምክንያት የምንጠላው ሰው የለም?

"እሱን ሰውዬ ጥሎብኝ አልወደውም"

"አይ እሱን ልጅ ቀልቤ ትከሻዬ አልወደደውም"

"እኔ እንጃ ለምን እንደሆነ ባላውቅም አልወዳትም:: ምክንያቴን አትጠይቀኝ ግን በቃ እንዲሁ አልወዳትም"

ምንም ምክንያት ሳይኖረን እንዲሁ የምንጠላው ሰው አለ::

እግዚአብሔር ግን
"አንድያ ልጁን እስኪሠጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአል" (ዮሐ 3:16)

ጠላቶቹ ሳለን በልጁ ሞት አዳነን እንደሚል እርሱ እኛን ለመጥላት ብዙ ምክንያት ነበረው:: እርሱ ግን እንዲሁ ወደደን:: ከእኛ ምንም ባያገኝም ስለ እኛ ያለው ፍቅር የእንዲሁ ፍቅር (unconditional love) ነበረ:: እርሱ እንዲሁ ወዶናል እኛ ግን እንዲሁ ሰው እንጠላለን::
ያለ ምክንያት መውደድ ቢያቅተን እንኳን ያለ ምክንያት መጥላታችን (unconditional hate) ቢቀር ምናለ?
የሚያሳዝነው ያለ ምክንያት የጠላናቸውን ሰዎች የበለጠ ለመጥላት በልባችን እስር ቤት ውስጥ በጥላቻ ሰንሰለት እናስራቸውና የበለጠ ለመጥላት ስለእነርሱ ክፉ ክፉ ማስረጃ ለመስማት እንተጋለን:: ጥሩ ነገራቸውን ለመስማት አንፈልግም:: ክፉ ስንሰማ ግን "እኮ እኔ እኮ ዝም ብሎ ትከሻዬ ይነግረኝ ነበር" ብለን በደስታ እንፈነድቃለን:: እንዲሁ የጠላነውን ሰው በምክንያት ለመጥላት በመቻላችን ደስ ይለናል::

እኛ ሰውን ለመጥላት ምክንያት የምንፈልገውን ያህል እንዲሁ የወደደን እግዚአብሔር ግን እኛን ለመማር ሰበብ ይፈልጋል:: ትንሽ በጎነት ቅንጣት ቅንነት ሲያገኝ እጅግ ይደሰታል:: ባለቅኔው "እግዚአብሔር መንግሥቱን በርካሽ ዋጋ ሸጠው:: በቀዝቃዛ ውኃ በዘለላ ዕንባ እና ማረኝ በሚል የወንበዴ ጩኸት!" እንዳሉት እሱ እኛን ይቅር ለማለት የሚታይ በጎነት ቢያጣ ልባችን ውስጥ ገብቶ ትንሽ መጸጸት ካለ ይፈልጋል:: እንዲሁ ወዶናልና እንዲሁ ሊተወን አይፈልግም::

"እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለሆነ
ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳን በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወትን ሠጠን"
ኤፌ 2:4

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 30 2013 ዓ ም
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ! በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
በቸርነትህ አመታትን ታቀዳጃለህ
መዝ ፷፭፡፲፩
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
አንተ ቸር ጌታዬ ምህረትህ በዛና
መርቀህ ሰጠኸኝ
ዕድሜ ለንስኃ ዕድሜ ለምስጋና
ተመስገን አምላኬ ተመስገን ኤልሻዳይ
ቸል አላልክም እና
የልመናዬን ቃል የኔነቴን ጉዳይ
መልስ የለኝምና ስላደርክልኝ፡
እንዳመሰግንህ ልቤን ክፈትልኝ ።

በቃ ይቅር በለን
ዳግም አይመለስ  ያለፈው ሰቆቃ
በሰላም ተኝተን በሰላም እንንቃ
እባክህ ጌታ ሆይ
በሰላም በፍቅር
እንዲኖር ሁሉም ሰው
ዘመነ ሉቃስን ባርክና ቀድሰው

💙💙💙💙💙💙💙💙💙
መልካም አድስመት ይሁንልን።
💙💙💙💙💙💙💙💙💙

ሳሙኤል አዳነ

፩/፩/፪፻፲፭

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
በጥቂቱ መታመን

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ "በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ!.." ማቴ 25፥21፡፡ ይህም ማለት በምድራዊ ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ በሰማያዊ ነገሮች ላይ እሾምሃለሁ ማለት ነው፡፡ በዚኛው ዓለም ታማኝ ሆነ ከቆየህ በዘለዓለማዊነት ውስጥ እሾምሃለው ማለት ነው፡፡ ይህ መመሪያ በብዙ መስኮች ላይ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል... ዘመዶችህን በመውደድ ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ጠላቶችህንም በመውደድ ላይ ይሾምሃል፡፡ ጠላትህን የምትወድበት ጸጋ ያድልሃል ማለት ነው፡፡

በትርፍ ጊዜዎችህ እግዚአብሔርን የምታገለግል ከሆንህ በሕይወትህ ጊዜ ሙሉ በእርሱ ላይ ትኩረት የምታደርግበትን ፍቅር ያድልሃል፡፡ የፈቃድ ኃጢአቶችን ከአንተ በማስወገድ ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ያለ ፈቃድ ከሚመጡ ኃጢአቶች ነጻ ያወጣሃል፡፡

ንቁ ኅሊናህን ከክፉ አሳቦች የምትጠብቅ ከሆንህ እግዚአብሔር ንቁ ያልሆነው ኅሊናህን ንጽሕና ያድልሃል፤ ከዚህ በተጨማሪ የህልሞችህን ንጽሕናም ያድልሃል፡፡ ልጅ እያለህ ታማኝ ከሆንህ እግዚአብሔር ውጊያዎች በሚበዙበት በወጣትነትህ ዘመን ውስጥም ታማኝነትን ያድልሃል ሌሎች ሰዎች ላይ በቃላት ብቻ የማትፈርድባቸው ሆነህ በመገኘትህ ታማኝ ከሆንህ ይበልጥ አስቸጋሪ በሆነው በአሳብ እንዳትፈርድባቸው ያስችልሃል፡፡ ልክ እንደዚሁ ራስህን ከውጫዊ ንዴት በመጠበቅ ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አውስጣዊ ቁጣ፣ንዴትና ቅናት ነጻ ያወጣሃል፡፡

በተለመዱ መንፈሳዊነቶች (በመንፈስ ፍሬዎች) ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የመንፈስ ስጦታዎችን ያድልሃል፤ በመጀመሪያው ላይ ታማኝ ሆነህ ካልተገኘህ ሁለተኛውን ፈጽመህ ልታገኘው አትችልምና፡፡

እግዚአብሔር በመጀመሪያ የሚፈትሽህ በጥቂት ነገር ነው፡፡ በዚህች በጥቂቷ ነገር ላይ ታማኝ መሆንህ ካረጋገጥህ እርሱ በሚበልጠው ነገር ላይ ይሾምሃል፡፡ ውድቀትህንና አለመታመንህን በጥቂቷ ነገር ላይ ከገለጽህ ግን እግዚአብሔር በሚበልጠው ነገር ላይ አይሾምህም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላልና፦ "ከእረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱህ ቢደክሙህ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ?" ኤር 12፥5 ብዙ ሰዎች ዝቅተኛውን ኃላፊነት መወጣት ሳይችሉ ከፍተኛውን ኃላፊነት ለመቀበል ማሰባቸው እጅግ አስደናቂ ነገር ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች በተሰጣቸው ጸጋ ሳይጠቀሙ ተጨማሪ ጸጋ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ ናቸው፡፡ ይህን ሲያደርጉም "በጥቂቱ ታምነሃል፤ በብዙ እሾምሃለሁ" የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል በመዘንጋት ነው፡፡

"መንፈሳዊ ቃላትና ጥቅማቸው" ከሚለው #አያሌው_ዘኢየሱስ ከተረጎመው #የብጹዕ_አቡነ_ሽኖዳ መጽሐፍ
💙💙🌿💙🌿💙🌿💙
@TIBEBnegni
ታቦት እና ጣኦት ((Samuel Adane))

ሲያሻኝ እጠጣለሁ
ሲያሻኝ እሰክራለሁ
ሲያሻኝ እሰጣለሁ
ሲያሻኝ እነጥቃለሁ
ሲያሻኝ እወዳለሁ
ሲያሻኝ እጠላለሁ
ሲያሻኝ እሰርቃለሁ
ሲያሻኝ እሰራለሁ
ሲያሻኝ አድናለሁ
ሲያሻኝ እገላለሁ
አያልቅም ተነግሮ: ይቅር አይወራ
ታቦትና ጣዖት:ሆኗል የኔ ስራ
አልኖር ለዘላለም: ዳግም አልወለድ
ምን ያህል ዉርደት ነው
ከሰውነት ዙፋን :ከክብር ላይ መውረድ
ደግነት ነው እንጅ : ክፋት እያፀድቅም
እኔ ስካራም ነኝ
ድቅል ነው ሂወቴ : ምርጫየን አላቅም
ታቦትና እና ጣዖት
አንድ ላይ ከሆነ የለውም ታከታይ
እኔም እንደዛ ነኝ
ወይ ሞቃት አይደለሁ ወይ ቀዝቅዤ አልታይ
ቀዘቀዘ ሲሉኝ ዳግም እሞቃለሁ
አቃጠለ ሲሉኝ :እቀዘቅዛለሁ
ይህ ነው የኔ ሂወት
እንዳው በድፈናው
እርባናቢስ ሆኘ እወዛወዛለሁ

19/08/2012

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
#በፍቅር_እንኑር

መነሻ ከሌለው ዝንተ ዓለም ወደ ማይደረስበት ዘላለም ተጓዥ ነን፡፡በሁለቱ መካከል ትንፋሽ መውሰጃ ጊዜ የለም፡፡ምን አልባትም ማይክሮሰከንድ አይኖርም ይሆናል፡፡ነገር ግን ሽርፍራፊዋም ብትሆን ያው የኛ ዕድሜ ነች፡፡በዚህ ዓለም አረፍ የምንልባት(የምንኖርባት እንዳልል ከመጣንበት ዝንት ዓለም እና ከምንሄድበት ዘላለም አንፃር የዕድሜያችን ርዝማኔ መለኪያው ስለማይነፃፀር እና ከዓይን ጥቅሻ ያነሰ በመሆኑ ነው)አንዳአንዴ ያንኑው የጥቅሻ ዕድሜ ያሰለቸናል፡፡ያነጫንጨናል፡፡ምክንያቱም እንደማረፊያ ሳይሆን እንደ ቋሚ መኖሪያ እናስባታለን፡፡እናም ቋም ነገሮችን ለመገንባት እንጣጣራለን...ወደ ውስጥ የሳብነውን አየር መልሰን ወደ ውጭ ሳንበትን የረፍት ጊዜያችን ይገባደድ እና እረጂም..በጣም እረጂም የፀጥታ እና የማይታወቅ ጉዦችንን እንጀምራለን፡፡
እና የዘላለም ተገጓዦች ነን፡፡በምድር ምንገነባው ህንፃ ማረፊያ ድንኳን እንጂ ቋሚ ሀውልት አይደለም፡፡ዘና ብሎ መሳቅ ...በፈገግታ መደሰት እንጂ ፊታችንን አጨማደን… ልባችንን አኮማትረን ..ስለ ኒዩኪሌር ቦንብ መጠበብ በህይወት ስለት ትርጉመ ቢስ ነው
ህይወት እኮ ምትሰለቸን እረፍታችን ምቸት ስለሌለው ነው...ለዚህ ነው የሚቀነቅነን፡፡የአብዛኞቻችን ኑሮ በችግር የታጠረበት ዋናው ምክንያት የጥቂተች ስግብግብነት ነው፡፡መቶ ሺ ዓመት በዚህች ምድር እንደሚኖር ..አንድ ሺ ሰዎች እድሜ ልክ ማኖር የሚችን ንብረት ብቻውን ታቅፎ እና ቀብሮ...እሱ በምቾት እና በስግብግብነት ቅዠት ውስጥ እየኖረ ..ሌሎች ሺ ዋችን በችግር እና በሰቀቀን ቅዠት ውስጥ እንዲኖሩ ማድረግ ትርፉ ምንድነው፡፡
እና እስቲ እንተሳሰብ፡፡ በፍቅር እንኑር፡፡ ጠብታ ጊዜያችንን በክፋት አናጨማልቃት፡፡በፈገግታ ጀምረን...በሳቅ አዋዝተን....በዜማ አጅበን...በደስታ ዘለን...በፍቅር ሰክረን..በእርካታ እንሰናበታት፡፤መጨረሻችን መድረሻ የሌለው ዘላለም አይደል፡፡
ስለዚህ መልካም አልመን ...መልካም ተግብረን...በመልካም ሁኔታ ኖረን..ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ፀፀት አልባ ሆነን እንድንገጓዝ ከፀለምተኛ አስተሳሰባችን...ከስግብግብ ባህሪያችን...ከመጠላለፍ ምግባራችን እንላቀቅ፡፡ትናንትን አክባሪ...ዛሬን አፍቃሪ...ነገን ናፋቂ እንደሆን ህይወትን ሳንሰለች ሩጫችንን በጥሩ አነሳስ ጀጀምረን በድንቅ አጨራረስ ማጠናቀቅ ይገባናል

#መልካም_ቀን

🔘ከዘሪሁን🔘
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
~ስንፈተ-ጥምረት
*
ገመድ ነው ምላስሽ
ሁሉን ያነካካል ፣
አለንጋ ነው ጣትሽ
ያልበላውን ያካል ።
*
ወታደር ነው እግርሽ
ጠረፍ ይሰደዳል ፣
ደንበርን ተሻግሮ
ሀገሩን ይከዳል ።
*
ልቅ ነው እይታሽ
አይጠነቀቅም ፣
ከሳሽ ነው ልቦናሽ
የሰው ልክ አያውቅም ።
*
እኔ ሆደ ጠባብ
አንች ልብ አውላቂ ፣
እኔ ለዘብተኛ
አንች ወሬ አዋቂ ።
*
ሳቅሽ ጉራማይሌ
ደስታ አያመጣ ፣
ምኑን ረስቸ
ምን ፈልጌ ልምጣ ።
*
እናም ይቅር በይኝ
አልተገናኘንም ፣
አይደለም ጎረቤት
ሀገር አይዳኘንም ።
***
14/05/2011

#ሳሙኤል አዳነ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ

❤️🌿🌿❤️🌿❤️🌿❤️❤️🌿❤️
@TIBEBnegn
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
ምርጥ ምርጥ አባባሎች(ወርቃማ መርሆች)

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌿“ምናብ ሁሉም ነገር ነው። ሕይወት ይዛቸው
የምትመጣቸው ማራኪ ኹነቶች ቅድመ ምልከታ
ማለት ነው። ምናብ ከእውቀትም የበለጠ ኃይል
አለው።” አልበርት አንስታይን
🌿 “ነፃነት አልባ ሕይወት እንደ ግዑዝ አካል ነው፡፡”
ካህሊል ጂብራን

🌿 ‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም
አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም››
ቅዱስ አርሳንዮስ
🌿 “ንፉግነትን ከሚጠየፉ የሰው ልጅ ጉዳዮች
ዋናው እውቀት ነው፡፡ እውቀት ያለቸርነት ሊኖር፣
ሊቀጥልም አይችልም፡፡ እውቀት ማኅበረሰብን
እስካልመራ ድረስ ስልጣኔ ምኞት ሆና
ትቀራለች፡፡” ዲ/ን ዳንኤል ክብረት በብራና
የሬድዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራም

🌿" ለማንኛውም ተንኮል ሁለት መፍትሔዎች
አሉት ፤ ጊዜና ዝምታ" አሌክሳንደር ፑሽኪን
🌿" ብልህ ሰው አንድ ቃል ሰምቶ ሁለት
ይረዳል።" አይሁዶች
🌿 " ራሳችንን መፈለግ ካልጀመርን የትም
አንደርስም " ወደ ምንጬ ሥረ መሠረቱ
መመለስ ጉዳያችን ሊሆን ይገባል ኣራት ነጥብ፡፡
ያልታወቀ
🌿 “በሰዎች ላይ የምትፈርድ ከሆነ ልትወዳቸው
ጊዜ የለህም” ማዘር ቴሬዛ
🌿" ወንድ ልጅ ሚስት ለማግባት ሽሜግሌ
ይልካል ፣
ሴት ደግሞ ባል በጊዜ እንዲገባ ሽማግሌ
ትልካለች።" Unknown

🌿" ዝቅተኛ እውቀት ባለህ ቁጥር የምትተኛው
እንቅልፍ ከፍተኛ ይሆናል።" ማክሲም ጎርኪ
🌿“ ህልምና ምኞት በሌላቸው ሰዎች መሃል ታላቅ
ከመሆን ይልቅ፣ህልምና ምኞት ባላቸው ሰዎች
መሀል ደካማ መሆንንእመርጣለሁ፡፡”ካህሊል#
ጅብራን
🌿" የሰውን አስተሳሰብና ልቦና ለመረዳት
ያሳካውን ሳይሆን የሚያልመውን ተመልከት"
ካህሊል ጅብራን
🌿“በሕይወት ውስጥ የተለመዱ ነገሮችን
ባልተለመደ መንገድ ስታከናውን የዓለምን ቀልብ
ትቆጣጠራለህ፡፡”
ጆርጅ ዋሺንግተን ካርቨር

🌿💥🌿💥🌿💥🌿💥🌿💥🌿
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

" የፍቅር ትንታኔ

እንኳን ምድራዊ ሀብትና እውቀት ይቅርና ሰማያዊ ጸጋዎች ያለፍቅር ከባድ ናቸው፡፡
ፍቅርን ስትይዝ ሁሉንም ጸጋ ያዝክ ማለት ነው፡፡
የሃይማኖት ፍቅርና ጉልላት ፍቅር ነው፡፡
ፍቅር ካለህ እግዚአብሔር ባንተ ልብ አለ፡፡
አንተም በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ አለህ፡፡

ፍቅር ድል አለው፡፡ ስለፀጋ ስጦታዎች ብዙ ጭቅጭቅ አለ ስለሚበልጠው ጸጋ ስለፍቅር ግን ስብከት ጠፍቷል፡፡ ስለፈውስ ብዙዎች ይለምናሉ ነፍስን ስለሚፈውሰው ፍቅር ግን አይፀልዩም፡፡
ማንኛውመ መንፈሳዊ ነገር በእውቀት በእምነት በፍቅር ካልተደረገፈ ሀጢያት ነው፡፡

ትንፋሽ ድንገት የሚቋረጥ ሲመስልህ ፣ የልብህ ምቾት የቀዘቀዙ መስሎ ሲሰማህ ፣ ተስፋህ ጭልጥ ሲልብህ የምትድነው በፍቅር ብቻ ነው፡፡
እንጨት በምስጥ ፣ እህል በነቀዝ ፣ ልብስ በብል ይበላል ፣ ሰውን ጥላቻ ይገዘግዘዋል፡፡
ሌሎች በኃይል እንዲሰሩ ሞተሩ ፍቅር ነው፡፡

ፍቅር ከሌለ ሰማዕትነት ሊኖር አይችልም፡፡
በየዕለቱ ሰማዕትነት ላይኖር ይችላል፡፡
በየዕለቱ መስዋዕትነት ግን አለ እርሱም ጥላቻን እንቢ ማለት ነው፡፡ በሁሉም ቦታ ፣ በሁሉም ደረጃ ፣ በሁሉም ፀጋ ውስጥ በሁሉም ዘመን ደግሞም ለዘለዓለም የሚፈለግ ፍቅር ብቻ ነው፡፡
በፍቅር የማይቃጠሉ ልቦች ወንድማቸውን ለመስቀል ይጨክናሉ፡፡

ቤተክርስቲያን የቆመችበቶ ምሶሶ ፍቅር ነው ፣ ያለፍቅር ትወድቃለች፡፡

ፍቅር ራሳችንን በሰው ውስጥ ሰዎችን በራሳችን ውስጥ የምናይበት መስታወት ነው፡፡
ፍቅር ያላቸው ሌሎችን የማስተካከል አቅም አላቸው፡፡
ፍቅር በቀላሎች ሰፈር ያላት ስያሜ ምስኪንነት ፍርሃት ነው፡፡
መንገዶችን ከመስራት ፍቅርን መገንባት ይቀድማል፡፡
የተሰሩት መንገዶች በጥላቻ ይዘጋሉ፡፡
ትልቁ ርዕዮተ አለም ፣ የማይከሽፍ መሳሪያ ፍቅር ብቻ ነው፡፡
ፍቅር ትልቁ ስጦታ ፣ ትልቁ መንገድ ፣ ትልቁ መሪ ነው፡፡

ዓይን ያለ ፍቅር ምን አገባኘ ይላል፡፡ ጆሮ ያለ ፍቅር ከሰማ ይፈርዳል፡፡ ምላስ ያለፍቅር ከወጣ ይሰብራል፡፡ እጅ ያለ ፍቅር ከተዘረጋ ይጥላል፡፡
እግር ያለ ፍቅር ከሔደ ድልድይ ያፈርሳል፡፡
ፍቅር የሌለው ሰማዕት ክርስቶስን አላወቀምና በከንቱ ይሞታል፡፡ ብዙ ነገሮች እንደጎደለን ብንናገርም በዋናነት የጎደለንፍቅር ነው፡፡

ፍቅርበመጨረሻው ዘመን ይቀዘቅዛል እንጂ አይጠፋም፡፡
ያለፍቅር የተሰበኩ ነፍሰ ገዳይ ይሆናሉ፡፡ ለማፍቀር የልብ ፈቃድና የእግዚአብሔር ፍቅር ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
ፍቅር በግልፅነት የምትከብር ናት ፍፁም የምትሆነውም ፍርሃትን ስታሸንፍ ነው፡፡

#ፍቅር_እራሷ_ጌጥ_ናትና_ጌጥ_አትፈልግም፡፡
#ፍቅር_ጽንፍ_የለሽ_ናትና_ዘረኘነት_አይስማማትም፡፡
#ተብራርቶ_ያላለቀ_ትንታኔ_ፍቅር_ብቻ_ነው፡፡
በፍቅር ያጌጡ በወርቅ ከተኝቆጠቆጡ ይበልጣሉ፡፡

ምኞት ዳርቻ ጥማትም እርካታ የሚያገኘው በፍቅር ብቻ ነው፡፡ ያለፍቅር የተዘረጉ ምፅዋቶች ከዱላ አይተናነሱም፡፡
#ኅሊናውን_አጉድለን_ሆዱን_የሞላንለት_ከሰጠነው_የሰረቅነው_ይበዛል፡፡

ፍቅር ሁሉም የሚሰጠው ምፅዋት ነው፡፡
ፍቅርን የማይሰጥ ድሃ የማይቀበል ሀብታምም የለም፡፡ ጎዶሎዎቾ መልካም የሚሆኑት በፍቅር ብቻ ነው፡፡
ሩጫህን የጀመርከው ያለ ጭብጨባ ብቻህን መሮጥ የጀመርህ ቀን ነው፡፡

#የታየህን_እይ_እንጂ_የሚያዩህን_አትይ_ትወድቃለህና፡፡"

የሆነ መፅሐፍ ሳነብ አገኘሁትና ላካፍላቹ ብዬ አሰብኩኘና እንዲህ ለንባብ እንዲመች አድርጌ ቀነጨብኩት፡፡

መፅሐፉን ርዕስ የፈለገ በውስጥ መስመር ያናግረኘ፡፡

በፍቅር እንኑር እላለሁ😍😍😍

@jahABP ነኘ መልካም አዳር ተመኘሁ
😍🙏😍

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
በአይኔ እያየሁት ነግቶ እየጨለመ፣
ይሄ ብኩን ልቤ ፤
ከጭፈራው ማግስት፤
የለቅሶውን መምጣት ለምን ተቃወመ?
እኔ እየጠበብኩኝ መንገዱ እየሰፋ ፣
በቋቋሜ ምክኒያት አካሀዴ ጠፋ ፡፡
ስጋዬ ነውና ፤
ከከፍታዬ ለይ ስቦ እሚዘርረኝ፣
አንተ መሀሪ አምላክ፤
እጀን ያዘው እና በቤትህ አኑረኝ ፡፡
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
💚💙💚💙💚💙💚💙💚💙
                  @sam2127
በመንፈግ ውስጥ ስየህ ያኔ ትናንትና
በማይሆነው መንገድ የሆነው ሆነና
ተወሳስቦ እያለ የህሊናየ በር የልቤ ቁመና
ሳትሰስት ወደህኝ
ሁሉም ለበጎ ነው ብየ በመቀበል
ቆምኩኝ ለምስጋና ።
ሰውማ ላመሉ ቃሉን እየበላ ልቡን እያጠፋ
ተሰጠኝ ያለውን ኑሮውን ሲገፋ
ቀን እያጎደለ ቀን የኖረ መስሎት
በስጋ ቢሰፋ
ባንተ ግን ጌታ ሆይ
ተፈፅሞ አይተናል የሽ ዘመን ተስፋ።
እንጅማ፦
እንደምታየው ነው
ሰው እምነቱን ጥሏል ውሸት እያበጀ
በቃሉም አይፀና
ዳግም በይቅርታህ ባንተ ካልተዋጀ።

Samuel Adane
@Sam2127

🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
አስታውስ

ደካማነትህን አስታውስ፦ ያን ጊዜ በጣም ጠንቃቃ ትሆናለህ፣ ሊጎዱህ በሚችሉ በትምክህትና በውዳሴ ከንቱም አትሸነፍም።

የተሰጠህን በፍቅር የተሞላ የእግዚአብሔርን ቸርነት አስታውስ፦ ይህም በምስጋና የተሞላ ሕይወት እንድትመራ ያደርግሃል። በእግዚአብሔር ፍቅርና ሥራ ላይ ስትታመን ፍጹም የሆነ እምነት በልብህ እያደገ ይመጣል። ከእግዚአብሔር ጋር ያሳለፍከው ጊዜ ደግሞ በእምነት እንድትኖር ያበረታታሃል።

የሰዎችን ፍቅርና ካንተ ጋር ያሳለፉትን መልካም ጊዜ አስታውስ፦ የሰዎችን ቀናነት ትጠራጠር ዘንድ ወይም ያደረጉብህን ክፉ ነገር ታስብ ዘንድ ይገባሃልን? የቀደመ ፍቅራቸው ስለ እነርሱ ይማልዳል ያንተንም ቁጣ ያበርዳል።

ሞት እንዳለ አስታውስ፦ እንዲሁ በዓለም ያለ ፈተናም እንደሚያልፍ። “ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እነሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።” መክብብ 1፡14 ማለትን ትረዳለህ።

በእግዚአብሔር ፊት መቆምህንና እርሱም እንደሚመለከትህ አስታውስ፦ ያኔ ኃጢአት አትሰራም እግዚአብሔርን ታየዋለህና።

ስለ አንተ የፈሰሰውን የክርስቶስን ክቡር ደም አስታውስ፦ በዚህም ሕይወትህ ያለውን ዋጋ በእርግጥ ታውቃለህ፤ በዓይኖችህ ፊት የከበረ ይሆናል፣ ስለዚህም በከንቱ በመኖር አታጠፋውም “በዋጋ ተገዝታችኋልና” 1ኛ ቆሮ. 6፥20 እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ።

በወላጆችህ እምነት በተጠመቅህባት ቦታ ለእግዚአብሔር የገባኸውን ቃል አስታውስ፦ ዲያብሎስን፣ ሥራዎቹን ሁሉ፣ ሐሳቦቹንና ጥበቡን፣ ኃይሉንም ትክድ ዘንድ ኃይል ታገኛለሕና።

በዚህ ዓለም እንግዳ መሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ ዘወትር አስታውስ፦ ያን ጊዜ በዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ።

በጠባቡ በር መጓዝ ወደ መንግስተ ሰማያት እንደሚያደርስህ አስታውስ፦ ሰፊው ደጅ ፊት ለፊትህ ተከፍቶ ብታየው፣ አልፈኸው ሂድ ከእሱም ራቅ፣ በእርሱ የሄዱ እንዳሉ አልቀዋልና።

ዘላለማዊውን ሕይወትህን አስታውስ፦ ሁልጊዜም ስለዚህ ትጋ።

የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህንና እርሱን መምሰል እንዳለብህ አስታውስ፦ እውነተኞች ከሆኑት ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር አካሄድህን አስተካክል።

የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆንህን አስታውስ፦ በውስጥህ ያለውንም ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝን። ዘወትርም ቅዱስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ሁን።


ብፁእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿

@TIBEBnegni
@TIBEBnegnj
@TIBEBnegni
ትሑትና ትዕግሥተኛ ሁን

በምድረ ገጽ ላይ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት የነበረውን ነቢዩን ሙሴን ምሰል “ሙሴም በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት ሰው ነበረ።” ዘኁ 12፥3።

ሁል ጊዜ መሐሪ እና ይቅር ባይ ለመሆን ሞክር ሐዋርያው “ለማንም ስለ ክፉ ፋንታ ክፉን አትመልሱ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ... ተወዳጆች ሆይ ራሳችሁ አትበቀሉ ለቁጣ ፋንታ ስጡ እንጂ ...” ሮሜ 12፥17-19 ብሏልና። እንዲሁም ቁጣን ጊዜያዊ ስሜትን እና ንዴትን እንድናስወግድ “ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ” ሮሜ 12፥21 በማለት ይጠይቀናል።

በእርግጥ መታገስ የሚችል ሰው ዕድለኛ ሲሆን ይህንን የማይችል ግን ደካማ ነው። ለዚህ ነው ሐዋርያውም “እኛም ኃይለኞች የሆንን የደካሞችን ድካም እንድንሸከም ራሳችንንም ደስ እንዳናሰኝ ይገባናል።” ሮሜ 15፥1 ያለው።

ሌሎች አንተ እንዳሰብካቸው ፍጹም የሚስማሙ እንዲሆኑ አትፈልግ። ነገር ግን መሆን እንዳለባቸው ሳይሆን እንደሆኑት አድርገህ ተቀበላቸው ሁላችንም ተፈጥሮን እንደራሷ አድርገን ተቀብለናል። ወቅቶችን ዝናባማ፤ ማዕበላማም ይሁን ሞቃታማ ተፈጥሮ ራሱን እንዲለውጥ ሳንጠይቅ ተቀብለነዋል። ከሰዎችም ጋርም ልክ እንዲሁ እናድርግ።

ሰዎች ሁሉ ጻድቅና መልካም አይደሉም። ብዙዎቹ ድክመቶች ወይም የተወሰኑት ባሕርያቸውን ተቆጣጣሪ የሆነ አመሎች አሉባቸው። ሰዎች የተለያዩ ዓይነቶች ናቸው። ከእነዚህ አንዳንዶች ሁከተኞች ናቸው። ስለዚህ በጠባያቸው ተጽዕኖ እንደማይደረግበት ተመልካች እንሁን። ባሕሪያቸውንም በጥበብ እንቀበላቸው።
አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል በመከራ ውስጥ ይመጣል

አንድ ሰው መፍትሔ የሌለው የሚመስል መከራ ሊገጥመው ይችላል። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ መከራው የገጠመው ጥቂት ኃጢአቶችን ስለ ፈጸመ መሆኑን ከማስጠንቀቂያ ጋር ይነግረዋል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ቃሉ ንስሓ ከገባህ መከራው ፍጻሜ ያገኛል እያለ ውስጡን ሲመክረው ይሰማል። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ስለ ንስሓው ሲል ለሰውየው ይራራለታል።

የእግዚአብሔር ድምፅ አንድ ሰው ሲታመም ወይም እርሱ የሚወደው ሌላ ሰው ሲታመም ሊመጣ ይችላል። በዚህ ጊዜ እንዲጸልይ ወይም ስዕለት እንዲሳል የሚመክረውን ድምፅ ከውስጡ ይሰማል ይህ ድምፅ የእግዚአብሔር ድምፅ ነው።

የዮሴፍ ወንድሞች እህል ሊገዙ ወደ ግብጽ ከወረዱ በኋላ በዚያ ችግር ሲገጥማቸው እርስ በእርሳቸው እንዲህ በማለት ተነጋግረው ነበር “በእውነት ወንድማችንን በድለናል እኛን በማማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውና። ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን።” ዘፍ. 42፥21። ከዚህ በኋላ ለዮሴፍ እንዲህ ብለውታል “ለጌታዬ ምን እንመልሳለን? ምንስ እንናገራለን? ወይስ በምን እንነጻለን? እግዚአብሔር የባሪያዎችህን ኃጢአት ገለጠ...” ዘፍ. 44፥16። ኃጢአታቸውን እንዲያስታውሱ ኀላም እንዲገሰጹ ያደረጋቸው የእግዚአብሔር ድምፅ ነው።

ነቢዩ ዳዊት የጌራ ልጅ በሆነው በሳሚ ሲሰደብ የእግዚአብሔር ድምፅ ውስጡን ስላለፈ ኃጢአቱ እየወቀሰው መሆኑን አዳምጧል። ስለሆነም በዙሪያው ለነበሩ ሰዎች “እግዚአብሔር ዳዊትን ስደበው ብሎታልና ይርገመኝ።” 2ኛ ሳሙ. 16፥10 በማለት በግልጽ ተናግሯል።

ረሀብና የመሬት መንቀጥቀጥ በዓለም ሲደርስ የእግዚአብሔር ድምፅ በመላው ዓለም ውስጥ ይሰማል። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ የሚናገረን “ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ።” ሚል. 3፥7 እያለ ነው። ይህ ድምፅ በረሀቡ ወይም በመሬት መንቀጥቀጡ ጉዳት ለደረሰባቸው ሀገሮች የሚሆን የእርዳታ ጥሪ ለማሰማት ወይም ሌሎቹ ከእነርሱ ትምህርት በመውሰድ ንስሓ እንዲገቡ ለማድረግ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኝት ዝግጅት እንዲያደርጉ ነው።

ስለዚህ ማንኛውም ዓይነት መከራ ውስጥ ስትገቡ ከውስጣችሁ ያለውን የእግዚአብሔር ድምፅ አድምጡት እርሱ ለእናንተ ሊነግራችሁ የሚወደው ምን እንደ ሆነ ታውቃላችሁና።

ብፁእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
ራስን መንቀፍ

ራሱን የማይነቅፍ ሰው እርሱ ትክክል እንደሆነና እንዳልተሳሳተ አድርጎ ስለሚያስብ ምንም አይነት ስህተች ቢሰራ እንኳ ይቅርታ አይጠይቅም። ከወንድሙ ጋር ሲጋጭ ከእርሱ ጋር ለመታረቅ ራሱን አያነሣሣም። እርቁ እንዲመጣ የሚፈልገው ከሌላ ወገን ነውና። ግን ለምን? ይህን የሚያመጣው ማንነት ነው! ሌላው ቢቀር እኔነቱ ምንም አይነት ስህተት እንዳልሠራ አድር ስለሚያሳምነው ስህተቱንም በእግዚአብሔር ፊት እንኳ እይናዘዝም።

ራስን መንቀፍ የሚመጣው ከትሕትና ሲሆን ትሕትና ደግሞ ራስን ወደመካድ ይመራል። ትሑት ያልሆነ ሰው ራሱን አይነቅፋም አይኮንንም። ሁልጊዜ የሚነቅፈው ሆነ የሚኮንነው ሌሎችን ነው። እንዲህ ዓይነቱን ሰው ለምን ሌሎችን እንደሚነቅፍ ብትጠይቁት ይህን በማለታችሁ ብቻ እንኳ ይገሥጻችኋል።

አንድ ራሱን ምንጊዜም በዓለማዊ ዘዴዎች የማያጎላና የማያከብር ሰው ዋናውና ተቀዳሚው ዓላማው ራሱን ከስህተትና ከጥፋት ማንጻት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሰው ሁልጊዜ ራሱን ይወቅሳል፣ ስህተቶቹን ይመረምራል፣ ለስህተቶቹም ማስተካከያ ይወስዳል፡፡

በአንድ ወቅት ጳጳሱ ቴዎፊለስ መነኮሳት አባቶች የሚኖቱበትን በአት ሲጎበኙ የዚያ ቦታ አስጎብኚ ለሆኑት መነኩሴ በዚህ ሳሉ ስለገኟቸው ቅዱስናዎች ሲጠይቋቸው “እመኑኝ አባቴ! ከሁሉም ነገር በላይ ራስን ከመውቀስ የሚበልጥ ቅድስና የለም!” በማለት መልሰውላቸዋል፡፡ ይህ አንድ ሰው ራሱን ብቻ እንጂ ሌሎች ሰዎችን፣ አካባቢውንና እግዚአብሔርን የማይወቅስበት መንፈሳዊ መንገድ ነው፡፡

ራሱን በዚህ ዓለም ሳለ የወቀሰ ሰው በወዲያኛው ዐለም ከመወቀስ ይድናል። ሰው ራሱን የሚወቅስበት ምክንያት ወደ ንሰሐ ለመቅረብ ነው። ንሰሐ ከገባ ደግሞ እግዚአብሔር ሐጢያቱን ይቅር ይለዋል። ራሱን ከማክበር አንጻር ራሱን የማይወቅስ ሰው ግን ሳይሻሻል በሐጢያት ውስጥ በመወቀስ ይኖራል።

ቅዱስ እንጦንስ “እኛ ራሳችን ከወቀስን ዳኛው በእኛ ይደሰታል።” ብሎ የተናገረው ምንኛ እውነት ነው! ከዚህ በመቀጠልም “እኛ ሐጢያቶቻችንን የምናስታውሳቸው ከሆነ እግዚአብሔር በንሰሐ ይረሳልናል፤ እኛ ሐጢያቶቻችንን የምንዘነጋቸው ከሆነ ግን እግዚአብሔር ያስታውሰናል፡፡” በማለት ተናግሯል።

ራስን መውቀስ ከሰዎች ጋር ለመታረቅ ይረዳናል፡፡ ሰውን “አንተ ትክክል ነው፡፡ ይህን ጉዳይ አስመልክቼ የተሳሳትሁት እኔ ነኝ . . . ” በማለት ይቅርታ መጠየቅ ትችላላችሁ፡፡ እነዚህ ቃላት የወንድምህን ቁጣ ሰለሚገቱት ይታረቅሃል፡፡ ይህን ሳታደርግ ራስህን ነጻ ለማውጣት የምትከራከር ከሆነ ግን ጠላት ስህተትህን ለማጋለጥ ማንም አይደርስበትም፡፡

ይህን አስመልክቶ ቅዱስ መቃርስ የተናገረው አባባል ምነኛ ድንቅ ነው! “ወንድሜ ሆይ! ሌሎች ሳይወቅሱህ አንተ ራስህን ውቀስ!”

ብፁእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
2024/10/03 06:27:12
Back to Top
HTML Embed Code: