Telegram Group Search
ዕለተ አርብ (Good Friday)
ዜና ክርስቶስ || Christ Chronicles
ዕለተ አርብ (Good Friday)
ሐዋርያው ዮሐንስ በዓለም ታሪክ ውስጥ እጅግ አስደናቂ የሆነውን መስዋዕትነት በአንድ ቀላል ቃል ገልጿል። "ሰቀሉት" የሚለው ግሥ ስም ወይም አድራጊው ወታደሮቹ ብቻ እንዳልሆኑ ማሳየቱ ትኩረት የሚስብ ነው። ዮሐንስ ኢየሱስን የሰቀሉት “ የሮማ ወታደሮች” ናቸው ብሎ አልጻፈም፤ ምንም እንኳን በእንጨት ላይ ያዋሉት እነሱ ቢሆኑም። ኢየሱስን የሰቀሉትን “አይሁዶች” ብቻ ናቸው ብሎ አልጻፈም፣ ምንም እንኳን በሰው እይታ ለሞት ያበቃው የሕዝቡ ጩኸት ቢሆንም። በዚህ ዓለም የሕይወት ስጦታ የተሰጠው እያንዳንዱ ሰው ኢየሱስን በመስቀል እንጨት ላይ የመቸነከሩን ኃላፊነት ይጋራል (ኢሳ 53፡5፣6)። እያንዳንዳቹ በሀጥያታቹ ምክንያት ኢየሱስ ክርስቶስን ሰቅላችሁታል።

መስቀሉ የእግዚአብሔርን ከባድ ፍትህ እና የኃጢአት አስከፊ መዘዝ በግልፅ ያሳየናል(ሕግ)። እንዲሁም የጌታችንን ፍቅር እና ርህራሄ ለማይገባቸው ኃጢአተኞች ያሳየናል(ወንጌል)። እንደተለመደው ሁለቱም መልእክቶች ለአድማጭ መቅረብ አለባቸው። ህግና ወንጌል።

መስቀሉ፡ የአዳኛችን ሙሉ ስራ ማስረጃ
1. ትንቢትን ሁሉ ይፈጽማል
2. ፍጹም እና ቅዱስ የሆነውን ሕይወቱን ይመሰክራል
3. ሞቱን ያስታውሰናል

ንጉሥን ሰቀሉት!
1. ምንም ያላጠፋውን ንጉሥ
2. በሕዝቡ የተጠላ ንጉሥ
3. በፍቅር ተልዕኮ ላይ ያለ ንጉስ

[1] ጲላጦስ በኢየሱስ ላይ ምንም ዓይነት ሕጋዊ ክስ ሊያገኝ አለመቻሉን እናያለን።

[2] ብዙዎች ኢየሱስን ከእግዚአብሔር የተላከ አይደለም ብለው ክደውታል።

[3] ኢየሱስ ንጉሥ ሆኖ ያልተቀበሉትን ጨምሮ ለሁሉም ሰዎች መከራ ለመቀበልና ለመሞት በፈቃደኝነት በሐዘን መንገድ መጓዙን ለማስታወስ ይጠቅማል።

°ለኢየሱስ ሞት ተጠያቂ የሆኑ ውስን ቡድኖች ላይ ጣት አንቀስር። ከዚህ ይልቅ እኛ ኃጢአት ስለሰራን፣ ኢየሱስን እንደ ንጉሣችን ባለመቀበላችን ጥፋተኞች መሆናችንን እና እርሱ ለእኛ ሲል ወደ ጎልጎታ በህማም መንገድ መሄዱን ለማስታወስ ይሁን። ተባረኩ።
እዚያ ነበርህ ወይ

ጌታዬን ሲሰቅሉ እዚያ ነበርህ ወይ? (2x)
ኦ-ሆ-ሆ አንዳ-ንዴ (እንድርድ -3x) ያደርገኛል፤
ጌታዬን ሲሰቅሉ እዚያ ነበርህ ወይ?

ጌታን ሲቸነክሩ-ዚያ ነበርህ ወይ? (2x)
ኦ-ሆ-ሆ አንዳ-ንዴ (እንድርድ -3x) ያደርገኛል፤   
ጌታን ሲቸነክሩ-ዚያ ነበርህ ወይ?

ጌታዬን ሲቀብሩ እዚያ ነበርህ ወይ? (2x)
ኦ-ሆ-ሆ አንዳ-ንዴ (እንድርድ -3x) ያደርገኛል፤
ጌታዬን ሲቀብሩ እዚያ ነበርህ ወይ?


Hymn 456 - "Were you there” ከሚለው የእንግሊዝኛ መዝሙር የተተረጎመ


ዜና ክርስቶስ || Christ Chronicles
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ይህን ያውቁ ይሆን? ዮሐንስ ሴባስቲያን ባክ የተባለ በ18ኛ ክ/ዘመን የነበረው የሉተራን ሙዚቀኛ እና የሙዚቃ አቀናባሪ ትንሽ ሴት ልጁን እና ሶስት ወንድ ልጆቹን ከዚያም ሚስቱን አጣቸው። ከዚያም እንደገና አገባና በድጋሚ እሱ እና ሁለተኛ ሚስቱ አና-ማግዳሊና አራት ተጨማሪ ሴት ልጆችን እና ሦስት ወንድ ልጆችን አጡ። በአጠቃላይ አስራ አንድ ውድ ልጆችን...

ብዙ ተመራማሪዎች ባክ እነዚህ ሁሉ ሰዎች ሞተውበት እንዴት መቋቋም ቻለ? እንዴት መተንፈስስ አላቆመም፣ እንዴት ልቡ መምታት አልቆመም? እና ከሁሉም በላይ እንዴት ሙዚቃ መጻፉን ሊቀጥል ቻለ? ብለው ይጠይቃሉ። Cantatas, Cello Suites, Masses, Concertos ተብለው የሚጠሩትን አለም እንዲሰማው የታደለው አስደናቂ የሙዚቃ ቅንጅቶችንና ስራዎችን አበርክቷል። እነሱንም ለቤተ ክርስቲያን ቅዳሴያዊ አምልኮ እንጂ ለአለም ዘፈን አይደለም ተግቶ የሰራው። ይህን ሁሉ እንዴት እንዳደረገው ታውቃላችሁ?

በሙዚቃው መጨረሻ ላይ ሁል ጊዜ "ሶሊ ዴኦ ግሎሪያ/Soli Deo Gloria" (ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ) እና በመጀመሪያው ላይ ደግሞ "ጌታ ይርዳን" በማለት ይጽፍ ነበር። ስለዚህ፣ በባክ ሙዚቃ ወቅት መጸለይ ትችላላችሁ፤ ምክንያቱም ሙዚቃው ራሱ ጸሎት ነው፤ ታዲያ የባክን ሙዚቃ በሰው ልጅ እና በእግዚአብሔር መካከል የተደረገ ውይይት እንደሆነ አድርጋችሁ ማየት ትችላላችሁ። ህመምን እንዴት መቋቋም ትችላላችሁ? አምልኮ ከሁሉ የበለጠ ማጽናኛ ነው።

#Johan_Sebastian_Bach
ለመዝሙር ግጥሞች፡ https://zenakristos.org/hymns

ዜና ክርስቶስ || Christ Chronicles
አሁን፣ አንድ አለም፣ አንድ አምላክ፣ እና አንድ አዳኝ ብቻ እንዳለ ካወቃችሁ፣ የበለጠ ማወቅ ያለባችሁ ነገር ቢኖር አንድ ታላቅ ትእዛዝ አለ። ኢየሱስ ክርስቶስ “አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል" ብሏል። አንድ መቶ ብር ከነፍስ የበለጠ ዋጋ ያለው ይመስል ቅዱሳት መጻሕፍትን ለመመርመር ወይም ለማጥናት እና ለድነት ለመዘጋጀት ጊዜ የለኝም ብለው በማሰባቸው ብዙ ወንዶች እና ሴቶች ከመንግሥቱ እየራቁ ነው። ልክ የአሁኑ ጊዜ ከዘለአለም ህይወት የበለጠ አስፈላጊ የሆነ ይመስል! አሁን አርፈን ግልጽ የሆነውን የድነታችንን እቅድ እንደማዳመጥ በምድር ላይ ከምንም አይነት የበለጠ ስራ(business) የለም። ነገር ግን፣ በመጨረሻው ጊዜ፣ ለመዳን አንድ መንገድ ብቻ አለ፣ እናም ብቸኛው መንገድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።

—–The Way Made Plain , A Few Plain Sermons To Busy Adults Who Think They Have Not The Time To Take A Thorough Course Of Catechetical Instructions , By Rev. Simon Peter Long, A.M.


ዜና ክርስቶስ || Christ Chronicles
የነጻነት ፡ መዘዝ ፡ የአምልኮ ፡ ነጻነት
በበጐቹ ፡ መግቢያ ፡ ትኩሎች ፡ ዘው ፡ አሉበት
ሥርዓት ፡ የሌለበት ፡ ገደብ ፡ የሌለበት
የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ለንግድ ፡ ጨረታ ፡ የወጣበት
አወይ ፡ ነጻነት ፤ አወይ ፡ ነጻነት ፤ አወይ ፡ ነጻነት

ለአምልኮ ፡ ነጻነት ፡ ሱባኤ ፡ ተገብቶ
መሰደድም ፡ ቀረ ፡ ከላይ ፡ ትዕዛዝ ፡ ወጥቶ
መግቢያ ፡ በሩ ፡ ሰፋ ፡ ሰው ፡ ተግተለተለ
እንክርዳዱ ፡ ስንዴ ፡ ተኩላው ፡ በግ ፡ መሰለ
የድል ፡ አጥቢያ ፡ አርበኛ ፡ ዘለቀ ፡ ሆ ፡ ብሎ
ውጪያዊ ፡ ምስሉን ፡ ወጉን ፡ አስተካክሎ

በየጓዳው ፡ ፈላ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ሰሪ
ራሱ ፡ ፈላጭ ፡ ቆራጭ ፡ ባለሚኒስትሪ
ዶክትሪኑ ፡ በዛ ፡ መድረክ ፡ ጠበበ
ጥራት ፡ ሳይሆን ፡ ብዛት ፡ ስንቱን ፡ ሰበሰበ
ግርግር ፡ እንዳይሉት ፡ ወይ ፡ ዘመነ ፡ ጥፉ
የአምልኮ ፡ ነጻነት ፡ ብለውት ፡ አረፉ

ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ነጻነት
ነጻነት ፡ እያሉ
ሲያሞግሱሽ ፡ ዋሉ
ጉድሽ ፡ ግን ፡ ብዛቱ
ላወቀው ፡ ለስንቱ

[አዝማች]...

መጽሃፍ ፡ ቅዱስ ፡ ኮሌጅ ፡ አጠናቅቄያለሁ
ምስክር ፡ ወረቀት ፡ ቆቤንም ፡ ጭኛለሁ
አንግዲህ ፡ የቀረኝ ፡ ሀያ ፡ ሰው ፡ ሰብስቤ
ኪሳቸው ፡ ኪሴ ፡ ነው ፡ ለወጭ ፡ ለቀለቤ
እያሉ ፡ የሚያልሙ ፡ ወንጌል ፡ ተጡዋሪዎች
ዙሪያችን ፡ ፈልተዋል ፡ ሥራ ፡ ጠላቱዎች (፪x)

ቀላዋጮች ፡ ብዙ ፡ ተንባዮች ፡ ለእንጐቻ
መረቅ ፡ ላጠጣቸው ፡ ላበላቸው ፡ ብቻ
እንደ ፡ መተተኛ ፡ እዚህ ፡ እዛ ፡ እያሉ
ቅልጥም ፡ ላገኙበት ፡ ይተነብያሉ
የነጻነት ፡ ውልዶች ፡ ስንቱን ፡ ያሞኛሉ
በግርግር ፡ መጥተው ፡ የተቀላቀሉ ፡ የተቀላቀሉ

ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ነጻነት
ነጻነት ፡ እያሉ
ሲያሞግሱሽ ፡ ዋሉ
ጉድሽ ፡ ግን ፡ ብዛቱ
ላወቀው ፡ ለስንቱ

[አዝማች]...

ራሱን ፡ የሚያዳንቅ ፡ አገልጋይ ፡ሞልቶናል
ሥሙን ፡ ሲያስተዋውቅ ፡ ፎቶውን ፡ አይተናል
ስብከቴ ፡ ነክቶአቸው ፡ እልፍ ፡ ሰዎች ፡ ዳኑ
አጋንንቶች ፡ ወጡ ፡ ብሎ ፡ ማጋነኑ
ራሱ ፡ እንዳደረገው ፡ በኃይል ፡ በጥበቡ
እውቁልኝ ፡ ብሎ ፡ ሥሙን ፡ ማነብነቡ (፪x)

ባለድርጂቱስ ፡ በጐ ፡ አድራጊ ፡ መሳይ
በሙት ፡ ልጆች ፡ ነጋጅ ፡ ጫና ፡ ጫንቃቸው ፡ ላይ
በድሀ ፡ ሥም ፡ ዞሮ ፡ ባከማቸው ፡ ሁሉ
ፎቁን ፡ ገንብቶበት ፡ የሚታይ ፡ ለሁሉ
ምናልባት ፡ ሲተርፈው ፡ ከርሱን ፡ ካጠገበ
ትርፍራፊው ፡ ሲቀር ፡ ድሆቹን ፡ አሰበ

ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ነጻነት
ነጻነት ፡ እያሉ
ሲያሞግሱሽ ፡ ዋሉ
ጉድሽ ፡ ግን ፡ ብዛቱ
ላወቀው ፡ ለስንቱ ፤ ላወቀው ፡ ለስንቱ (፪x)

ጉድሽ ፡ ግን ፡ ብዛቱ
ላወቀው ፡ ለስንቱ ፤ ላወቀው ፡ ለስንቱ (፪x)


የአምልኮ ፡ ነጻነት (Yeamleko Netsanet) - ደረጀ ፡ ከበደ

ዜና ክርስቶስ || Christ Chronicles
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የብሉይ ኪዳን ሰዎች በመሥዕዋት፣ ህግን በመጠቅ እና በራሳቸው ስራ ነው የዳኑት ወይስ በእምነት እና በፀጋ ብቻ በመሲሁ አምነው ነው የዳኑት? (ከአንድ መልስ በላይ መምረጥ ይችላል)
Anonymous Poll
32%
በመሥዕዋት፣ ህግን በመጠቅ እና በራሳቸው ስራ
45%
በእምነት እና በፀጋ ብቻ
9%
ክርስቶስን አያውቁትም ነበር
12%
ፀጋ በብሉይ ኪዳን ዘመን አልነበረም
41%
የብሉይ ኪዳን ሰዎች በአብርሐም እቅፍ ውስጥ ሆነው ክርስቶስን ሲጠባበቁ ነበር
7%
አላውቅም።
ከበዓለ ሃምሳ በኋላ 7ኛ ዕሁድ

የዕለቱ ፀሎት
ብርቱ እና ኃያል የሆንኸው አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፤ መልካም የሆነውን ሁሉ የምትሰጥ አንተ ነህ፡፡ በሙሉ ልባችን እንድንወድህ ዕርዳን፣ በእውነተኛ ዕምነት አበርታን፣ የሚያስፈልገንን ሁለ እንደፈቃድህ ስጠን፣ በአንተ እንክብካቤ ውስጥ በሰላም እንድትጠብቀን ከአንተ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ አምላክ ሆኖ፤ አሁን እና ለዘላለም በሚኖረው እና በሚገዛው፤ የአንተ ልጅ እና የእኛ ጌታ በሆነው፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንለምንሀለን፡፡

@ZenaKristos
Audio
ስብሃት ለአምላክ መዝሙር 46
በመስቀል ሞተ መድኃኒቴ


፩፡ በመስቀል ሞተ መድኃኒቴ
እኔን ለማዳን ከኃጢአቴ፥
ሊመልሰኝም ከጥፋቴ።
ክብር ለስሙ፥

ክብር ለስሙ፥
ክብር ለስሙ፥
ነፃ ስላወጣኝ በደሙ፥
ክብር ለስሙ።


@ZenaKristos
Engeda Negne Ene
መዝሙር 437: እንግዳ ነኝ እኔ ስኖር በዚች ዓለም


፩፡ እንግዳ ነኝ እኔ ስኖር በዚች ዓለም
ሀብቴም በሰማይ ነው ከዚህ ምንም የለኝ።
የሱስ ይጠራኛል ከሰማይ በር ከፍቶ፥
ከእንግዲህ ይህ ዓለም ፍጹም ቤቴ አይደለም።
ታማኝ ወዳጅ እንዳንተ እንደሌለኝ፥
ጌታ ሆይ፥ ታውቃለህ እኔን የሚያጽናናኝ።
የሱስ ይጠራኛል ከሰማይ በር ከፍቶ፥
ከእንግዲህ ይህ ዓለም ፍጹም ቤቴ አይደለም።

፪፡ ወደፊት ልራመድ ይጠባበቁኛል
የሱስ ይቅር ብሎኝ በሩን ከፍቶልኛል።
ምንም ድሀ ብሆን እኔን አይተወኝም፥
ከእንግዲህ ይህ ዓለም ፍጹም አይረባኝም።
ታማኝ ወዳጅ . . .።

፫፡ አፍቃሪ አዳኝ አለኝ በላይኛው አገር
ናፍቆቴን አልተውም ፊቱን እስካይ ድረስ።
በሰማይ ደጅ ቆሞ ይጠባበቀኛል፥
ከእንግዲህ ይህ ዓለም ፍጹም ቤቴ አይደለም።
ታማኝ ወዳጅ . . .።

...
Lyrics src: https://zenakristos.org/hymns/374
YT song by G&B: https://youtu.be/4DFMOZnp7k4?si=GDPZ_vgK-HCgBtP_
መልካም አዲስ አመት ይሁንላችሁ! 🌼🌼🌼የበረከት ብቻ ሳይሆን የንስሃ አመት፣ በረከቱም ደግሞ መንፈሳዊ በረከቶች ይሁኑ (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1)

"ቅ ዱስ አምላክ ሆይ፣ ጻድቅ ፈራጅ ሆይ፣ የልጅነቴን በደል አታስብ(መዝሙረ ዳዊት 25:7) ያለፈውን ኃጢአቴን ከእንግዲህ ወዲህ አታስብ(ኤርምያስ 31፡ 34)።"

To read: https://zenakristos.org/articles/28
ቃሉ ብቻ እና ትውፊት Part 1

ብዙ ሰዎች ትውፊታዊ አብያተ ክርስቲያናት የቤተክርስቲያን አባቶችን አለን ስለሚሉ ብቻ ከጎናቸው እንደሆኑ ይመስላቸዋል። ይሁን እንጂ በእውነት የቤተክርስቲያን አባቶች ከማንም ጎን አይደሉም። እነሱ በራሳቸው አቋም ላይ ያሉ ናቸው። ብዙውን ጊዜ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን እናከብራለን የሚሉ ሰዎች ከትክክለኛው አውድ ውጪ በመጥቀስ ከክብራቸው ይሰርቃሉ።
የቃሉ ብቻን አቋም የቤተክርስቲያን አባቶች እንደሚቃወሙ የሚያምኑ ሰዎች የሚሰሩት ትልቁ ስህተት ቃሉ ብቻን ካለመረዳት የሚመጣ ነው። ስለዚህ ቃሉ ብቻን እና ከትውፊት አንፃር ያለውን አቋም እንወያይበት።


በሚከተሉት መንገዶች ማዳመጥ ይችላሉ

Website | Podcasters | Spotify | CastBox | Amazon Music


@Zenakristos
Notice:

The website ZenaKristos.org is down temporarily and currently under maintenance. We will launch it soon for the Reformation week.

-Admins
ዜና ክርስቶስ በTikTok ላይ 1000 followers ገብቷል!!!🎉
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የጌታ ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን

እንደሚታወቀው የተሐድሶ ቀን በዓል ቀርቧል። የእግዚአብሔር ቃል እና የተወደደችው የኢየሱስ አካል በሆነችው ቤተክርስትያን ላይ የሚደርሱትን በደሎች ለመቃወም የምንቆምበት የዓመቱ ጊዜ ነው። ቤተ ክርስቲያን ከተተከለችበት ጊዜ ጀምሮ፣ የቤተ ክርስቲያንን ንጹሕ አስተምህሮዎችና ልምምዶች ለማደፍረስ የሚሞክር አካል ሁልጊዜ ነበር። በመጀመሪያ የአይሁድ በሥራ በኩል መጽደቅ ትምህርት ነበረ፤ በኋላም በዶ/ር ማርቲን ሉተር ዘመን በጳጳሱ በኩል ተካሄዷል።

በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ከተለያየ አቅጣጫ ተመሳሳይ ስህተቶችን እናስተውላለን። ከአንዱ ከጎራ ዘመናዊ ፕሮቴስታንቲዝም እና የካሪዝማቲክ እንቅስቃሴዎች መስፋፋት ሲሆነ በሌላው በኩል ደግሞ ብዙ የውሸት ትምህርቶችን ወደ ቅዱሷ ቤተ ክርስቲያን ያፈለሰው ለትውፊት የተጋነነው ክብር እና ቦታ ነው። ሁለቱም ጎራዎች ቅዱስ የሆነውን እና እንደ እግዚአብሔር ቃል የሆነውን የቤተ ክርስቲያንን ንጹሕ አስተምህሮዎችና ልምምዶች የሚበክሉ ስለሆኑ ተሐድሶ የሚያስፈልጋቸው ጎራዎች ናቸው።

ዛሬም ቢሆን "Ad Fontes" ወይም "ወደ ጥንቱ" ማለትም ወደ ቅዱሳት መጽሐፍት እንመለስ ልንል ይገባናል፤ ተሐድሶ ይህ ነውና። ስለዚህም ዛሬም ቢሆን እኛም ሉተር የተናገረውን "Here I Stand" የሚለውን አቋም እንያዝ።

የተሃድሶውን ዜናን ለማሰራጨት በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያዎች ይህንን ምስል የፕሮፋይል ፒክቸራችሁ እንድታደርጉት በእግዚአብሔር ፍቅር እጠይቃችኋለው።

እግዚአብሔር ሁላችሁንም ይባርካችሁ።🙏

@ZenaKristos
2025/02/06 09:55:55
Back to Top
HTML Embed Code: