Telegram Group Search
🎧ይህንን ያውቁ ኖሯል

👉 Gloomy sunday የተሰኘውን ሙዚቃ በማዳመጥ ብቻ ብዙ ሰዎች እራሳቸውን አጥፍተዋል

👉 በ1930 ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ በሀንጋሪና አሜሪካ ብቻ 19 ከዚ ሙዚቃ ጋር የተያያዘ የራስ ማጥፋት ኬዞች ተመዝግበዋል።

😟 በሚገርም ሁኔታ የሙዚቃው ደራሲ እራሱ ሳይቀር እራሱን አጥፍቷል ! ! !

💢መሞከር የምትፈልጉ ከታች አስቀምጥላችኋለሁ።👍

#መልካም_እድል😁😁

#Share
@Silehuluum
✳️ Telegram አዲስ የማስታወቂያ ሥርዓት በሚቀጥለው ዓመት ዘረጋለሁ ብሏል!

🔻የቴሌግራም መደበኛ ተጠቃሚዎች ቁጥር ወደ 500 ሚሊዮን መጠጋቱ ተገልጿል። እስካሁን ግን የገቢ ምንጩ ምን እንደሆነ የብዙዎች ጥያቄ ሆኖ ቆይቷል።

🔻 ከዛሬ ሰባትና ስምንት ዓመት በፊት በሁለቱ ወንድም አማቾች ኒኮላይ እና ፓቬል ዱሮቭ የተጀመረው ቴሌግራም በገቢ ምንጭነት እስካሁን የሚጠቀመው የድርጅቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኃብት ነው። በዚህም ፓቬል ዱሮቭ ለቴሌግራም ሥራ ማስኬጃ በመቶ ሚሊዮን ዶላሮችን ወጪ አድርጓል።

🔻ሥራ አስፈጻሚው ዛሬ በቴሌግራም ቻናሉ እንዳሳወቀው ድርጅቱ ገለልተኛና ጥራቱን እንደጠበቀ እንዲቀጥል በመጪው ዓመት ገቢ የሚያስገኙ ሥራዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጀምር አስታውቋል።

🔻ቴሌግራም አንዳንድ ማሻሻያዎችን እንደሚያደርግም የገለጸ ሲሆን ተጠቃሚዎች እስካሁን በነጻ ሲያገኙ የነበሩትን አገልግሎት ያለ ክፍያ እስከመቼውም መጠቀም እንደሚችሉ አረጋግጧል።

🔻ድርጅቱ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ከማስታወቂያ ገቢ መሰብሰብ እንደሚጀምር ያስታወቀው ፓቬል ዱሮቭ የግላዊ መልዕክት ልውውጦች እንዲሁም በቡድን ልውውጦች ወቅትም ምንም አይነት ማስታወቂያ እንደማይለጠፍ ገልጿል።

🔻ቴሌግራም ማስታወቂያ አሳያለው ያለው በቻናሎች ላይ ሲሆን ለዚህም ከመደበኛ መልዕክቶች ለየት ያለ እንዲሁም ለተጠቃሚዎች ምቹ የሆነ የማስታወቂያ ስርዓት ዘረጋለውም ብሏል።

🔻ማስታወቂያዎቹ የሚነገሩበት ቻናል በተከታዮቻቸው ብዛት መሰረት ቻናላቸው ይበልጥ ተደራሽነቱ ከፍ እንዲል እድሉ ይመቻችላቸዋል ተብሏል። በተጨማሪም ቴሌግራም በልዩነት ለሚያዘጋጃቸው ምስሎች (stickers) የስነ ጥበብ ባለሞያው የትርፉ ተቋዳሽ ይሆናል።

✔️Join Us ፦ @Silehuluum
አንድን remove ያደረጋችሁትን ሰው እንዴት አርገን ግሩፓችን ውስጥ እንደበፊቱ #Access እንዲያረግ ማድረግ እንችላለን?

🔆እንደሚታወቀው remove ያረግነውን ሰው unban ብናረገው እንኳን እሱን ወደ ግሩፓችን add ማድረግ አንችልም ስለዚህ እንደበፊቱ እንዲጠቀም ከፈለግን ግሩፓችን ላይ ማስተካከል ያለብን ነገር አለ...

Group setting=>Permission ከዛ ወደ ታች ትወርዱና add exception የሚል አለ እሱን ነክታቹ usernaሙን አስገቡና #search አርጉት ከዛ የሰውየው profile ይመጣላችኋል ንኩት ከዛ የምትፈቅዱለትን ፍቀዱና ከላይ ✔️ንኩ👏👏👏

@Silehuluum
#tech_facts

👉 የጉግል የመጀመሪያ መጠሪያ "Backrub" ይባል ነበር።

👉 ጉግል ማፕን በመጠቀም የከርሰ ምድር ሒዎትን መመልከት ይችላል።

👉 ሰዎች ኢንተርኔት ላይ ያሉትን ነገሮች በፍጥነት የመርሳት ችግር "Google Effect" በመባል ይታወቃል።

👉 ፌስብክ ተጠቃሚዎቹ በሚሞቱበት ወቅት አካውንታቸውን የሚያስተዳድርላቸውን ሰው መሰየም የሚያስችል አሰራር አለው።

👉 እ.ኤ.አ 2013 ነሐሴ 16 ጉግል ለ 5 ደቂቃ አይሰራም ነበር።

👉 ከ ሶስት አንድ ሰው ፌስቡክ ተጠቅመው ሲጨርሱ በሒወታቸው ደስተኛ እንዳልሆኑ ጥናቶች ያሳያሉ።

👉 የፌስቡክ የ"like" በተን መጣሪያው "awesome" ተብሎ ሊሰየም ነበር።

#share

@Silehuluum
🐜🐜 😴

ጉንዳኖች በጭራሽ እንቅልፍ ተኝተው አያውቁም።

@Silehuluum
🔆ላፕቶፓችን💻 ላይ ያለውን #ኢንተርኔት እንዴት ያለምንም ሶፍት ዌር በሞባይላችን📲
መጠቀም እንችላለን

1️⃣ right click በማድረግ run as administrator የሚለውን በመጫን👆 #CMDን ይክፈቱ።

2️⃣. ላፕቶፓችን ኔትዎርክ ሼር ለማድረግ ብቁ መሆኑን ለማረጋገጥ ➡️ netsh
wlan show drivers የሚለውን ጽፎ ከሚመጣልን ዝርዝር ውስጥ Hosted network supported :Yes ይህ ከመጣ ላፕቶፓችን ይችላል ማለት ነው

3️⃣. በመቀጠል ይህንን ኮማንድ ማስገባት➡️ netsh wlan set
hostednetwork mode=allow ssid=Hotspotname key=password

⚠️ማሳሰቢያ: SSID የሚለውን በፈለግነው ስም መቀየር እንችላለን
⚠️KEY የሚለው የዋይ ፋይ ፓስዎርዳችን ስለሆነ የምንፈልገውን መስጠት እንችላለን።

4️⃣. በመቀጠል የኔትዎርክ አዳፕተራችንን በመክፈት እና እሱላይ right click
በማድረግ ➡️ Allow other network users to connect through this
computer's internet connection የሚለውን እንመርጥና ከስር ካለው ሊስት ውስጥ የፈጠርነውን የዋየርለስ ኔትዎርክ እንመርጥለታለን።

ከዛም #OK በለን እንወጣለን

5️⃣. በመጭረሻ ወደ CMD ተመልሰን:

ለማስጀመር netsh wlan start hostednetwork የሚለውን ኮማንድ
እናስገባለን ለማቆም netsh wlan stop hostednetwork የሚለውን እናስገባለን።

6️⃣. አሁን ሞባይላችንን📲 wifi ከፍትን SSID ላይ ያስገባነውን የኔትዎርክ ስም መርጠን ለሚለው KEY ላይ ያስገባነውን በመስጠት መጠቀም መጀመር✔️ እንችላለን።

💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢

⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ። ✔️Join Us ፦ @Silehuluum
✳️ Tech News...

🔻በቅርቡ ስልካችንን በእየ ሶስት ወሩ ብቻ ቻርጅ ማድረግ ነው የሚጠበቅብን ምክንያቱም ከሰሞኑ ተመራማሪዎች እንድ ነገር ይፋ አድርገዋል።

🔻ተመራማሪዎችም እንዳሉት ከሆነ Magneto Electric Multiferroic ተብሎ የሚጠራ ከአዲስ ቁስ የተገኘ አዲስ የ Smartphone ባትሪ በአንድ ጊዜ በተደረገ ቻርጀ ለሶስት ወር ያህል እንዲቆይ የማድረግ አቅም ያለው ነው ተብሏል።
@Silehuluum
💻 ኮምፒዉተር የሚዘጋበት ወይም ክራሽ የሚያደርግበት 5 ምክንያቶች 💻

💽📀የሀርድዌር መቃረን📀🔌

ለ Windows ክራሽ የማድረግ ዋነኛው ምክንያት የ Hardware መቃረን ነው፡፡እያንዳንዱ Hardware ክፍሎች ለመግባባት IRQ(interrupt request channel) ያስፈልጋቸዋል፡፡ እነዚህ IRQ ለየሀርድዌሩ የተለዩ ወይም የተነጠሉ መሆን አለባቸው፡፡ ለምሳሌ አንድ ፕሪንተር IRQ 7 ሲኖረው ኪቦርድ ደግሞ IRQ 1፡፡እያንዳንዱ ሀርድዌር የራሱ የሆን IRQ ለመያዝ ጥረት ያደርጋል፡፡ ግን ብዙ የሀርድዌር እቃዎች ስንጠቀም ወይም የሀርድዌሩ ሶፍትዌር በስርዓት ካልተጫነ ሁለት ሀርድዌሮች ተመሳሳይ IRQ ሊጋሩ ይችላሉ፡፡ በዚህም ሰዓት ሁለት የሀርድዌር ዕቃዎች በተመሳሳይ ሰዓት ለመጠቀም ስንሞክር ክራሽ ሊከሰት ይችላል፡፡

📼የተበላሸ ራም📼

ራም Ram (random-access memory) ችግሮች ዋናው የብሉ እስክሪን ኦፍ ዴዝ (blue screen of death) ዋና መንስኤ ሲሆን የሚያሳየው መልእክት ፋታል ኤክሰብሽን ኢረር( Fatal Exception Error) የሚል ነው፡፡ ፋታል ኢረር የሚነግረን አሳሳቢ የሀርድዌር ችግር አለ ማለት ነው፡፡ አንዳንዴ የሀርድዌር ክፍል ስለተጎዳ መቀየር እንዳለበት ይናገራል፡፡ በራም የሚመጡ ችግሮች ብዙ ግዜ የራሙ ከኮምፒዉተሩ ጋር ሳይጣጣም ሲቀር ነው፡፡ ይህም ማለት ለኮምፒዉተር የራም ስሎት ጋር ሳይመጣጠን ሲቀር ፤ የራሱ ያልሆነ ሞዴል ስንጠቀም እና የተለያየ አይነት ራም በአንድ Computer ውስጥ ስንጠቀም ነው፡፡ለምሳሌ 70ns ለይ 60ns ራም ስንጠቀም ኮምፒተሩን ፍጥነት ይቀንሳል፡፡ይሄ ደግሞ ራሙን ከአቅሙ በላይ ይጫነዋል በዚህ ግዜ window ክራሽ ያደርጋል፡፡

📟ባዮስ ሴቲንግ( BIOS settings)📟

እያንዳንዱ ማዘር ቦርድ ሲመረት የራሱ የሆነ የተለያዩ ቺፕሴት ሴቲንግ አብሮት ይጫናል፡፡ እነዚህን ሴቲንግ ለመጠቀም በኮምፒውተራችን ኪቦርድ ላይ F2 ወይም F10 (እንደ ኮምፒዉተሩ ይለያያል) ኮምፒዉተሩ ስንከፍት ከጥቂት ሰከንድ በኻላ በመንካት ሴቲንጉን አክሰስ ማድረግ ይቻላል፡፡ ነገር ግን አንዴ ባዮስ ዉስጥ ከገባን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ ማንኛውንም ሴቲንግ ከመቀየራችን በፊት ፎቶ ወይም ወረቀት ለይ ሴቲንጎቹን ማኖር አንድ ያበላሸነው ነገር ካለ በቀላሉ መቀየር ያስችለናል፡፡ብዙን ግዜ የባዮስ ችግር የራም ላተንሲ ችግር ነው፡፡ የድሮ ኮምፒዉተር ራም ላተንሲ 3 ሲሆን የቅርብ ግዜ ራሞች ደግሞ ላተንሲ 2 ናቸው፡፡ ይሄንን ሴቲንግ በምንቀይርበት ጊዜ ኮምፒዉተሩ ክራሽ ያደርጋል ወይም ፍሪዝ ይሆናል፡፡

🐞ቫይረስ🐞
ቫይረሶች የኮምፒዉተር ፕሮግራም ሲሆኑ እራሳችውን በማብዝት ወይም ኮምፒዉተር ፋይሎች ላይ በማጣበቅ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ ቫይረሶች የትእዛዞች ስብስብ ሆኖ እራሱን በሌላ የኮምፒዉተር ፕሮግራም ያጣብቃሉ(ብዙ ግዜ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን)፡፡ ኮምፒዉተራችን ውስጥ ቫይረስ ሲያጠቃ የኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ፋይል የመቀየር ሀይል ስላለው ኮምፒዉተሩን ክራሽ ወይም ፍሪዚ ሊያረግ ይችላል፡፡

⚡️መጋል⚡️
በኮምፒዉተራችን ዉስጥ ካሉ ሀርድዌሮች በጣም አስፈላጊው እና ዋናው ሲፒዩ ነው፡፡ ሲፒዩ በኤሌትሪክ ሃይል የሚሰራ ሲሆን ካለው ውስብስብ የትራዚስተር ብዛት አማካኝነት የሚፈጥረው ከፍተኛ ሙቀት ሲፒዩን ሊያበላሸው ወይም ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ሲፒዩ ብዙ ጊዜ ከማቀዝቀዣ ቬንትሌተር ከኮምፒዉተራችን አንድ ላይ ይመጣል፡፡ እነዚህ ቬንትሌተር ከተበላሹ ወይም ሲፒዩ ካረጀ የኮምፒዉተራችን ሲፒዩ መጋል ይጀምራል፡፡ ይህ ደግሞ በኮምፒዉተራችን ላይ የከርንል ኢረር ያስከትላል፡፡ ይሄ ችግር ብዙ ጊዜ የሚታየው በኦቩር ክሎኪንግ ጊዜ ነው፡፡ ይህ ማለት ሲፒዩን ከሚገባው በላይ በማሰራት ወይም ከፍተኛ ፍጥነት እንዲገባ በማድረግ ነው፡፡ሲፒዩ በጣም ሲግል ኮምፒዉተራችን ሳናስበው እራሱን ይዘጋል ወይም ክራሽ
@Silehuluum
እ.ኤ.አ. በ 1971 የመጀመሪያው የኮምፒዩተር ቫይረስ ተሰራ ፡፡ ክሬፐር የሚል ስያሜ የተሰጠው በኮምፒተርዎች መካከል እንዴት እንደሚሰራጭ ለማየት ብቻ እንደ ሙከራ ተደረገ ፡፡

ቫይረሱ መልእክቱን በቀላሉ አሳይቷል “እኔ ተጎጂው ፣ ከቻልክ ያዙኝ!”

ወደ ዱር የተለቀቀው የመጀመሪያው ቫይረስ አንጎል ተብሎ ይጠራ ነበር ፣ ይህ ደግሞ ምንም ጉዳት የለውም ፡፡

ሆኖም እሱ በጣም የመጀመሪያው IBM PC ቫይረስ ነበር ፡፡ Written By Tech Amo Dont Share Without Credit😡😡 📢: @Silehuluum
📲 ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ ሰባት ምልክቶች
▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃

1. #የስልክዎ ፍጥነት ከቀነሰ

#ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ከሌላው ጊዜ በተለየ ትዕዛዞችን ለማከናወን ረዘም ያለ ጊዜ የሚፈጅ ከሆነ፤ ባዕድ ሶፍትዌሮች #(ማልዌር) እያስቸገሩት ነው ማለት ነው።

እነዚህ #ማልዌር የተባሉት ቫይረሶች ዋነኛ ሥራቸው የስልክዎን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማዘግየት ሊሆን ስለሚችል፤ በአፋጣኝ #ማስወገድ ተገቢ ነው።

2. #ስልክዎ በጣም የሚግል ከሆነ

#ስልክዎት ከተለመደው ከፍ ባለ ሁኔታ #የሚግል ከሆነ፤ ችግር አለ ማለት ነው። በፍጥነት #እርምጃ ይውሰዱ አልያም #ባለሙያ ያማክሩ።

3. #የስልክዎ የባትሪ ኃይል ቶሎ የሚያልቅ ከሆነ

#ስልክዎ ከፍተኛ #ሙቀት አለው ማለት ደግሞ #የባትሪው ኃይል ቶሎ ቶሎ ያልቃል ማለት ነው።

#ምናልባት ስልክዎ አዳዲስ መተግበሪያዎችንና #ሶፍትዌሮችን ለማደስ በሚሞክርበት ወቅት የባትሪውን ኃይል #ሊጨርስ ይችላል። ነገር ግን ምክንያቱ #ይህ ካልሆነ ስልክዎ #ተጠልፎ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ አለብዎ።

4. #ወደ ማያውቁት ሰው መልዕክት ከተላከ ወይም ከማያውቁት ሰው መልዕክት ከደረስዎ

#ብዙ ጊዜ እርስዎ የማያውቋቸው #መልእክቶች የሚላኩት በዋትሳፕና በመሳሰሉ #መተግበሪያዎች በኩል ሲሆን፤ የሚላከው ደግሞ ወደ ጓደኛዎት አልያም ወደ #የማያውቁት ሰው ሊሆን ይችላል።

ወደ እርስዎ የሚላኩ #መልዕክቶች ደግሞ ብዙ ጊዜ #ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ የሚሉ ማሳሰቢያዎች ይበዟቸዋል።

5. #ከበይነ መረብ የሚመጡ ድንገተኛ መልዕክቶች

ስልክዎን በመጠቀም በይነ መረብን #(ኢንትርኔት) በሚያስሱበት ወቅት #ወደ ሌላ ድረ-ገጽ #የሚያሸጋግሩ መልዕክቶች በተደጋጋሚ የሚመጡ ከሆነ #የስልክዎ መጠለፍ ነገር እውን ሊሆን ይችላል።

#መልዕክቱን ሲጫኑ በአንድ ጊዜ ወደ #ሁለትና ሦስት የድህ-ረገጾች አድራሻዎች የሚመራዎ ከሆነ በፍጥነት ይውጡ።

6. #አጠራጣሪ መተግበሪያዎችና ገንዘብ ነክ ጥያቄዎች

አንዳንድ ጊዜ እርስዎ #ያልገዙት ወይም ከበይነ መረብ #ያላወረዱት መተግበሪያ ስልክዎት ላይ ሊመለከቱ ይችላሉ። ምናልባትም #የሞባይል ዳታ እና የጽሁፍ መልዕክት ላይ የዋጋ #ጭማሪም ሊያስተውሉ ይችላሉ።

የክሬዲት ካርድና የሞባይል ገንዘብ ማንቀሳቀሻ መንገዶችን የሚጠቀሙ ከሆነ ይህ ሁኔታ #ለጠላፊዎች ምቹ አጋጣሚ ሊፈጥርላቸው ይችላልና ይጠንቀቁ።

#ስለዚህ የይለፍ ቃሎችንና #የግል መረጃዎችን ስልክዎት ላይ ባያስቀምጡ ይመረጣል፤ አልያም #በጠላፊዎች እንዳይገኝ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

7. #ያልተለመዱ ድምጾች

#የድምጽ ጥሪ በሚያደርጉበት ወቅት ያልተለመዱና ከዚህ በፊት ያልነበሩ ድምጾች #የሚሰማዎት ከሆን ምናልባት ስልክዎ #የጠላፊዎች ሰላባ ሆኖ ሊሆን ይችላል። ይባስ ብሎም የስልክ ጥሪዎችዎ #እየተቀዱም ሊሆን ይችላል።

🏷 #መፍትሄዎች
━━━━━━
▫️የስልክ #ማጽጃዎችን ከታማኝ ምንጭ ማግኘት

▫️እርስዎ #የማያውቋቸውን #መተግበሪያዎች ከስልክዎ ማጥፋት

▫️ብዙ ሰው የሚጠቀማቸው #ነጻ የኢንተርኔት #አገልግሎቶችን አለመጠቀም

▫️ስልክዎን #በቀላሉ ሊታወቅ በማይችል #የይለፍ ቃል መዝጋት

▫️ከማይታወቁ #ምንጮች #መተግበሪያዎችን አለመጫን

▫️ስልክዎና በስልክዎ ላይ ያሉ #መተግበሪያዎችን ቶሎ ቶሎ #ማሳደስ (update)

▫️#የስልክ ክፍያዎንና #የዳታ አጠቃቀምዎን #ይቆጣጠሩ
@Silehuluum
@Silehuluum
ኢትዮጵያ ድሮኖችን በአገር ውስጥ ማምረት ልትጀምር ነው።
🛫🛫🛫🛫🛫🛫🛫🛫🛫🛫🛫🛫🛫🛫🛫🛫🛫🛫
የኢትጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖኖሊጂ ኢንስቲትዩት ድሮኖችን ለማምረት ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሁም ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን ወደ ስራ ለመግባት ስምምነት ላይ መደረሱም ተነግሯል፡፡

በአቪየሽን ዘርፉ ረጅም ታሪክ ላላት ሃገር ድሮን በራስ አቅም ማምረት ትልቅና ከባድ ባይሆንም አሁንም ጂማሬው መበረታታት ያለበትና ከዚህም በላይ መስራት የሚያስፈልገው ትኩረት የሚሻው ዘርፍ ነው።
🛬🛬🛬🛬🛬🛬🛬🛬🛬🛬🛬🛬🛬🛬🛬🛬🛬🛬
Join us 👇👇👇👇
@Silehuluum
@Silehuluum
ከYoutube ላይ Audioን ፋይል በቴሌግራም እንዴት ዳውንሎድ እናደርጋለን ?

1. @YTAudioBot ላይ ሄደን ቦቱን Start እናደርገዋለን።
2. YouTube ላይ ገብተን የምንፈልገውን video እንከፍተዋለን።
3. ከከፈትነው ቪድዮ ታች ላይ Share የሚለውን በተን እንጫናለን።
4. በመቀጠልም ዝርዝር ይመጣል ከዛው ውስጥ copy link ወይንም የቴሌግራም አፕ እንጫናለ።
5. እዚህ ላይ copy link ካልነው YouTube አፕ ዘግተን ወደ ቴሌግራማች እንመለሳለን።
6. የከፈትነው ቦት ላይ ሄደን paste እናደርጋለ።
7. ከዝርዝር ውስጥ የቴሌግራም አፕ ከመረጥነው ደግሞ አፑን ሲከፍት search ማድረጊያ ላይ @YTAudioBot ቦቱን ካገኘነው
8. Alert Notification ያማጣል Send የሚለውን እንመርጣለን።
9. ፋይሉን convert ተደርጎ Download የሚለውን እንመርጣለን።
10. Audio ፋይሉን ይልክልናል እዛው ላይ ዳውንሎድ እናደርጋለን ማለት ነው።

@Silehuluum
📲 ዩቲዩብ (You Tube)

◽️👉ቻድ ሀርሊ፣ ስቲቭ ቻን፣ እና ጃዉድ ካሪም በተሰኙ ሶስት ግለተሰቦች ቪዲዮን በድረ-ገጽ ለብዙሃን ለማሳየት ታስቦ የተሠራዉ ዩቲዩብ ለጥቅም የዋለዉ በ2005 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ነበር። በተፈጠረ በዓመቱ የጉግል ኩባንያ ዩቲዩብን በመግዛት የኢንተርኔት ዘርፉን ተቆጣጠረበት። የመጀመሪያዉ የዩቲዩብ ቪድዮ የተጫነዉ በ2005 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ጃዉድ ካሪም በተባለ ከዩቲዩብ መስራቾች አንዱ በሆነዉ ግለሰብ ነበር። ይህ ቪድዮ ከተጫነበት ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ በመቶ ሚሊዮኖች፣ የሚቆጠሩ ቪድዮዎች ተጭነዋል። ዩቲዩብን ተወዳጅና ስኬታማ ያደረገዉ በየትኛዉም የዓለም ክፍል የሚገኝ ማንኛዉም ሰዉ ቪዲዮዉን በቀላሉ እና በፍጥነት በመላዉ ዓለም እንዲታይ ማስቻሉ ነዉ። ይህ ደግሞ ግለሰቦች ፍጹም ኖሯቸዉ የማያዉቀዉን በዓለም አቀፍ ደረጃ በቢሊየኖች የመታየት ሃይልን አጎናጽፏቸዋል። በርካቶች የተለያየ ችሎታቸዉን አሳይተዉ ታዋቂና ባለጸጋ ለመሆንም በቅተዋል።

. 👉ከ1.5 ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚ ያለዉ ዩቲዩብ በየወሩ በአጠቃላይ ቢደመር ከ3.25 ቢሊዮን ሰዓት በላይ ርዝመት ያለዉን ቪድዮ ለእይታ ያቀርባል። ጉግል ሰዎች በሚጭኗቸዉ በእነዚሁ ቪድዮዎች ላይ ማስታወቂያን በማሳየት ከዩቲዩብ ብቻ በየዓመቱ ከ4 ቢሊዮን ዶላር (የ2016 ዓ.ም. መረጃ) በላይ ገቢ በየዓመቱ ያገኛል። ቪድዮዎቻቸዉን በዩቲዩብ የሚለቁ ግለሰቦችም ቪድዮዎቻቸዉ በታዩ ቁጥር ተያይዘዉ ከሚታዩት ማስታወቂያዎች ላይ ገንዘብን ያፍሳል።
@Silehuluum
😤 ❤️

ሰዎች ሲያስነጥሰን ይማርህ የምሉን ሲናስነጥስ ልባችን ለ Mili- Second ስለሚያቆም ነው።

@Silehuluum
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 11 months. If it remains inactive in the next 28 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 11 months. If it remains inactive in the next 8 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
The owner of this channel has been inactive for the last 5 months. If they remain inactive for the next 30 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The channel will remain accessible for all users.
The owner of this channel has been inactive for the last 5 months. If they remain inactive for the next 18 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The channel will remain accessible for all users.
2024/09/28 15:30:13
Back to Top
HTML Embed Code: