Telegram Group Search
TIKVAH-ETHIOPIA
🆕 ካለፈው ከአርብ ጀምሮ ለሦስተኛ ቀን የቀጠለው የእስራኤል እና የኢራን ጦርነት እየተባባሰ ነው። ዛሬ በሁለቱም ወገኖች ጥቃቶች እየተፈጸሙ ናቸው። በእስራኤል የተፈጸሙ ጥቃቶች ፦ - እስራኤል በኢራን ውስጥ የሚገኙ ዒላማዎችን መምታቷን ቀጥላለች፤ የእስራኤል የመከላከያ ኃይል እንዳለው በዛሬው ዕለት 250 ዒላማዎችን መትቷል። -  የኢራን የመገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት አስከ ቅዳሜ ዕኩለ ቀን ድረስ 128 áˆ°á‹Žá‰˝â€Ś
🔄

የእስራኤል እና ኢራን ጦርነት 6ኛ ቀኑን ይዟል።

- ሁለቱም ወገኖች እርስ በርስ መታኮሳቸውን ቀጥለዋል።

- እስራኤል ትናንት ሌሊት በቴህራን የሚገኘውን የዩራኒየም ማብላያ እና ጦር መሣርያ ማምረቻ መምታቷን ገልጻለች።

- ኢራንም ማዕከላዊና ሰሜናዊ እስራኤልን በሚሳኤል ስትደበድብ ነበር። በዚህም ሰዎች ስለመጎዳታቸው ተሰምቷል።

- ኢራን ወደ እስራኤል ሚሳዔሎችን ማስወንጨፏን ብትገልጽም የጥቃቱ መጠን ግን እየቀነሰ መጥቷል ተብሏል።

- ሁለቱ አገራት አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ የሚሳዔል እና የአየር ጥቃት እየፈጸሙ ሲሆን ነዋሪዎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው መኖሪያቸውን ለቀው እንዲወጡ ቅድመ ማስጠንቀቂያ በተደጋጋሚ እየሰጡ ነው።

- እስራኤል ነዋሪዎች ከተለያዩ የቴህራን ክፍሎች ለቀው እንዲወጡ ስታስጠነቅቅ ቆይታለች። በዚህም ምክንያት ነዋሪዎች የቻሉትን ንብረት እየያዙ ከከተማዋ ለመውጣት በሚያደርጉት ጥረት በነዳጅ ማደያዎች እና በጎዳናዎች ላይ ረጃጅም ሰልፎች እና የትራፊክ መጨናነቆች እየታዩ ነው።

- ኢራን የቴላቪቭ እና ሃይፋ ነዋሪዎች የሚመጣው ከባድ ስለሆነ ለቃችሁ ውጡ የሚል መልዕክት እያስተላለፈች ነው።

- አሜሪካ ከእስራኤል ጋር ለማበር እያጤነች መሆኑ ተሰምቷል። አሜሪካ ከእስራኤል ጎን ተሰልፋ በኢራን ላይ በሚካሄደው ጥቃት የምትሳተፍ ከሆነ ግጭቱን ወደ አልተጠበቀ አቅጣጫ ሊወስደው ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።

- የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ " እኛ የኢራንን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒን አንገድልም ቢያንስ ለጊዜው አንገድላቸውም። አያቶላህ የት እንዳሉ በትክክል እናውቃለን ፤ ቀላል ዒላማ ነው፤ ግን እዚያ መልካም ነው " ብለዋል።

- የአሜሪካው መሪ ትራምፕ " ትዕግሥታችን እያለቀ ነው " ሲሉ አጠንቅቀው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ኢራን እጅ መስጠት እንዳለባት ተናግረዋል።


ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ እና ቲአርቲ ነው።

ቪድዮ ፦ የተጨናነቀ የተሽከርካሪ ሰልፍ የሚታይበት ቪድዮ ቴህራን ውስጥ እንደሆነና ነዋሪዎች ዋና ከተማውን ለቀው ለመውጣት እያደረጉ ባለው እንቅስቃሴ የተፈጠረ መሆኑን AFP ዘግቧል።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔄 የእስራኤል እና ኢራን ጦርነት 6ኛ ቀኑን ይዟል። - ሁለቱም ወገኖች እርስ በርስ መታኮሳቸውን ቀጥለዋል። - እስራኤል ትናንት ሌሊት በቴህራን የሚገኘውን የዩራኒየም ማብላያ እና ጦር መሣርያ ማምረቻ መምታቷን ገልጻለች። - ኢራንም ማዕከላዊና ሰሜናዊ እስራኤልን በሚሳኤል ስትደበድብ ነበር። በዚህም ሰዎች ስለመጎዳታቸው ተሰምቷል። - ኢራን ወደ እስራኤል ሚሳዔሎችን ማስወንጨፏን ብትገልጽም የጥቃቱ መጠን…
አሜሪካ በቀጥታ ወደ ጦርነቱ ትገባ ይሁን ?

እስራኤል በኢራን ላይ እያካሄደችው ባለው ጥቃት ውስጥ አሜሪካ ስለምትሳተፍበት ሁኔታ ለመወያየት ዶናልድ ትራምፕ በዋይት ሐውስ ውስጥ አስቸኳይ ስብሰባ ከከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው ጋር አድርገዋል።

አንድ ሰዓት ከ20 ደቂቃ በቆየው ስብሰባ ላይ ዋነኛ አጀንዳ የነበረው እስራኤል በኢራን የኒውክሌር ማዕከላት ላይ እየፈጸመችው ባለው ጥቃት ውስጥ አሜሪካ መሳትፍ እንዳለባት ለመወሰን ነበር።

የትራምፕ የቅርብ አማካሪዎች በተሳተፉበት በዚህ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ አሜሪካ በጥቃቱ ውስጥ ስለሚኖራት ተሳትፎ ሙሉ ስምምነት ላይ አለመደረሱ ተዘግቧል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለቀናት ኢራን ወደ ኒውክሌር ድርድር እንድትመለስ በተደጋጋሚ ሲወተውቱ ከቆዩ በኋላ ነው እስራኤል በኢራን ላይ በከፈተችው ጦርነት ውስጥ አገራቸው በቀጥታ መሳተፍ ሊኖርባት ይችል እንደሆነ ማጤን የጀመሩት።

በትላንት ማታው የአሜሪካ መንግሥት የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ትራምፕ እና አማካሪዎቻቸው የኢራንን የኒውክሌር ማዕከላትን ለማጥቃት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሪፖርት አቅርበዋል።

በዚህም ዋነኛ ዒላማ ሊሆን የሚችለው ከተራራ ስር ከመሬት በታች የሚገኘው ፎርዶ የተባለው የዩራኒያም ማበልጸጊያ መሆኑ ተነግሯል። ይህንን ከመሬት በታች የሚገኝን ማዕከል ለማውደም የሚያስችል ቦምብ ያላት አሜሪካ ብቻ ናት።

የፕሬዝዳንቱ አማካሪዎች አሜሪካን በጦርነቱ ውስጥ በሚኖራት ተሳትፎ ዙሪያ ከስምምነት ላይ መድረስ አልቻሉም።

የአሜሪካ እና የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ከአስቸኳይ ስብሰባው በኋላ ትራምፕ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በስልክ መነጋገራቸውን የዘገቡ ሲሆን፣ ነገር ግን በምን ጉዳይ ላይ እንደተወያዩ አልታወቀም።

ባለፉት ሦስት ቀናት የአሜሪካ የጦር ጄቶች እና ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን ነዳጅ የሚሞሉ ቢያንስ 30 ነዳጅ ጫኝ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ወደ አውሮፓ እንዲጓዙ ተደርገዋል።

ከአስቸኳይ ስብሰባው በፊት ዶናልድ ትራምፕ በተከታታይ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ኢራን " ያለ ቅድመ ሁኔታ እጇን እንድትሰጥ " መልዕክት ሲያስተላልፉ ነበር።

ለዚህም ምላሽ የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በተከታታይ በሰጡት ምላሽ አገራቸው " ከጽዮናውያን ጋር ፈጽሞ እንደማይስማሙ " ገልጸዋል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

▶️ @thiqahEth @tikvahethmagazine

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ጨመረ። እስራኤል ኢራን ላይ ከፍተኛ የአየር ጥቃት ከሰነዘረች በኋላ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 13 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ከ2020 በኋላ በቀን ውስጥ በዚህ ደረጃ ሲጨምር ከፍተኛው ነው ተብሏል። የአንድ በርሜል የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 78 ዶላር ገብቷል። አሁን ያለው ውጥረት በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ መቆራረጥ እንዳይፈጥር ተሰግቷል። ተንታኞች ውጥረቱ…
በኢራን እና እስራኤል ጦርነት ምክንያት የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ እንዳሻቀበ ነው።

ዛሬ ላይ አንድ በርሜል ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ 76.45 ዶላር እንዲሁም በአሜሪካ ነዳጅ ገበያ እንደመለኪያ በሚታየው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዴት አንድ በርሜል ነዳጅ 74.84 ዶላር እየተሸጠ ነው።

ጦርነቱ ከቀጠለ እና ሌሎችም ሀገራት የሚሳተፉበት ከሆነ የዓለም ነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ የገቢ ግብር ምጣኔ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ መንግስት ረቂቅ አዋጅ ማዘጋጀቱን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል። ሬድዮ ጣቢያው ከገንዘብ ሚኒስቴር አገኘሁት ባለው መረጃ በደመወዝተኛው ሆነ በንግድ የገቢ ግብር ምጣኔ ላይ ማሻሻያዎችን የያዘ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል። በመጭው ሰኞም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከባለሙያዎች ጋር ለመመካከር ጥሪ ማድረጉ ተሰምቷል። የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኮንፌዴሬሽንና…
#ኢትዮጵያ

የሠራተኞች መነሻ የደመወዝ ወለል 8,384 ብር እንዲሆን ተጠይቋል።

ወርኃዊ ደመወዛቸው እስከ 8,384 ብር የሆነ ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን ገለጸ፡፡

የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ፥ " ወርኃዊ ደመወዛቸው እስከ 8,384 ብር የሆነ ተቀጣሪ ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲደረጉ ለመንግሥት ጥያቄ አቅርበናል " ብለዋክ።

የገንዘብ ሚኒስቴር ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በሥራ ላይ ቆይቷል የተባለውን የገቢ ግብር አዋጅ 979/2008ን ለማሻሻል ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ከተባሉ ባለድርሻዎች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ እስከ ሁለት ሺሕ ብር የሚከፈለቸው ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ ተደንግጓል፡፡

ኢሠማኮ እስከ 8,384 ብር ድረስ የሚከፈለቸው ተቀጣሪዎች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ ለገንዘብ ሚኒስቴር በደብዳቤ እንደጠየቀ አስታውቋል፡፡

አቶ ካሳሁን በዓለም ባንክ መረጃ መሠረት ዕለታዊ ገቢው ከሦስት ዶላር በታች የሆነ ሰው ደሃ በመሆኑ፣ የመንግሥት የገቢ ግብር በዚህ ወለል ሥር ያሉ ተቀጣሪዎችን ታሳቢ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል፡፡

በማናቸውም ቀጣሪ ተቋማት የሚሠሩ ሠራተኞች በወር ከ8,384 ብር እስከ 22,974 ብር ደመወዝ የሚያገኙ ሠራተኞች፣ አሥር በመቶ ግብር እንዲጣልባቸው መንግሥትን መጠየቁን ኢሠማኮ ገልጿል፡፡

ከ22,975 እስከ 44,530 ብር ወርኃዊ ደመወዝ ተከፋዮች የ15 በመቶ፣ ከ44,531 እስከ 72,336 ብር የሚከፈለቸው ደግሞ 20 በመቶ፣ እንዲሁም ከ72,337 እስከ 107,449 ብር የ25 በመቶ ግብር እንዲጣልባቸው ኢሠማኮ በደብዳቤው አሳስቧል።

ከ107,450 እስከ 150,107 ብር ድረስ የሚከፈለቸው ሠራተኞች 30 በመቶ ግብር፣ እንዲሁም 150,108 ብር እና ከዚያ በላይ የሚከፈለቸው ተቀጣሪ ሠራተኞች ደግሞ 35 በመቶ ግብር እንዲከፍሉ ለመንግሥት ባቀረበው ደብዳቤ ኢሠማኮ መጠየቁን ገልጿል።

አሁን በሥራ ላይ ባለው የሠራተኞች የገቢ ግብ አዋጅ መሠረት እስከ 600 ብር ድረስ የሚከፈላቸው ሠራተኞች ከግብር ነፃ ሲሆኑ፣ ከ10,900 ብር ጀምሮ ደግሞ 35 በመቶ ግብር እንዲከፍሉ ይገደዳሉ፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ከአንድ ሳምንት በፊት ለውይይት ይፋ ባደረገው የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ 1,200 ብር፣ 1,600 ብር እና 2,000 ብር ወርኃዊ ደመወዝተኞች ከግብር ነፃ እንዲደረጉ ድንጋጌ መኖሩ ይታወሳል።

የመንግሥት የገቢ ግብር ማሻሻያው ሠራተኞች ያለባቸውን ወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ ታሳቢ ያላደረገ እንደሆነ የተለያዩ የውይይት ተሳታፊዎች አስተያየት መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

#ሪፖርተርጋዜጣ

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

የየእለቱን ዜናዎችን በSMS እናግኝ! 🗞📲
ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'A’ ብለን ወደ 30000 SMS አሁኑኑ በመላክ ወይም ወደ *799# በመደወል የቲክቫህ ትኩስ መረጃዎችን እናግኝ! በቀን 1ብር ብቻ! ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#MPESASafaricom
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት!

20% ጉርሻ!

ዛሬ የቶምቦላ ሎተሪ ለሚገዙ እድለኞች 20% ጉርሻ ይበረከታል!

በአዲስ አበባ ባለ  3 ወይም ባለ 2 መኝታ መኖሪያ ቤት እንዲሁም የቮልስዋገን ID 6 እና የBYD -SUV የኤሌትሪክ መኪናዎችን እርስዎን እየጠበቁ ነው።  

ለዓመታት በየወሩ ከሚያገኙት የብር ሽልማት ጋር - በቶምቦላ።

ቶምቦላ ሎተሪን www.ethiolottery.et ፣ በቴሌብር ሱፐር አፕ ላይ ወይም በወረቀት መግዛት ይችላሉ፡፡ 

ለበለጠ መረጃ በ+251977717272
TIKVAH-ETHIOPIA
የፕሬዜዳንቱን ፅ/ቤት ጥሰው የገቡት ሰልፈኞች ! " የማይተገበሩ ቃሎች መስማት ሰልችቶናል ፤ ለ5ኛ ክረምት በመጠለያ አንከርምም ወደ ቄያችን መልሱን " ያሉ በትግራይ ጦርነት የተፈናቀሉና መቐለ መጠለያ የሚገኙ ዜጎች ዛሬ ሰልፍ ወጥተው ነበር። ሰልፈኞቹ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ  አስተዳደርና የፌደራል መንግስት ወደ ቄያቸው እንዲመልሱዋቸው ጠይቀዋል። ሰልፈኞቹ ጥያቄያቸው በፅሁፍና በድምፅ ወደ ጊዚያዊ አስተዳደር…
#Tigray

" 1.2 ሚሊዮን ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ አልተመለሱም፤ የጦርነቱ ጦስ ዛሬያችን ብቻ ሳይሆን ነገያችንም እያጨለመው ነው "  - የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ኪሮስ ጉዑሽ (ዶ/ር) የፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት ሙሉ ሆኖ ባለመተግበሩ 1.2 ሚሊዮን ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ እንዳልተመለሱ ገልጹ።

" የጦርነቱ ጦስ ዛሬያችን ብቻ ሳይሆን ነገያችንም እያጨለመው ነው " ብለዋል።

ኃላፊው ይህንን ያሉት " ይበቃል ! " በሚል መሪ ቃል ተፈናቃዮች ዛሬ በመቐለ ማካሄድ የጀመሩትን ሰላማዊ ሰልፍ በመደገፍ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ነው።

ተፈናቃዮቹ በሁለት ሳምንት ለሦስተኛ ጊዜ ፤ ለሦስት ቀናት የሚዘልቅ ሰላማዊ ሰልፎ ዛሬ ሰኔ 11/2017 ዓ.ም ሮማናት አደባባይ ማካሄድ ጀምረዋል።  
 
" ለ5ኛ ክረምት በመጠለያ መኖር ይብቃ " ያሉ ሲሆን የትግራይ ክልል ቀድሞ ወደነበረበት ቅርጽ ተመልሶ ግዛታዊ አንድነቱ እንዲከበር፣ የተፈናቃዮች ድምፅ እንዲሰማ፣ በተፈናቃዮች ስም የሚሰራው የፓለቲካ ቁማር እንዲቆምና ሌሎችም ጥሪዎች አቅርበዋል።

ሰላማዊ ሰልፉን ያዘጋጀው በተፈናቃዮች የተመሰረተው " ፅላል ማሕበረሰብ ምዕራብ ትግራይ " የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ማህበር እንደሆነ ተነግሯል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የጉዞ ታሪክ በሌላቸው ሁለት ታዳጊዎች ላይ የMpox ምልክት መታየቱ ስጋት ፈጥሮብናል " - የሰገን ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዎች

➡️ " በኮንሶ ዞን የኤም ፖክስ(Mpox) በሽታ ምልክት በሁለት ሰዎች ላይ ታይቶ ናሙና ተወስዶባቸው ዉጤት እየተጠባበቅን ነዉ " - የዞኑ ጤና መምሪያ


ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ የሰገን ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዎች ስለዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) በሽታ ምልክቶች በተለያዩ አጋጣሚዎች እየተነገረ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት በአንዲት ተማሪ ላይ በፊቷ፣ በጀርባዋና በእግሮቿ ላይ ምልክቱን ያዩ የትምህርት ቤቷ መምህራን ለጤና ባለሙያዎች በማሳወቅ ታዳጊዋ  ተለይታ ክትትል እንድታደርግ መደረጉን ተናግረዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ ሀይሎታ አማራይታ በሚባል አከባቢ የአንድ ቤተሰብ አባላት በሆኑ የ16 እና 3 ዓመት ሴት ታዳጊዎች ላይ የዝንጀሮ ፈንጣጣ (ኤም ፖክስ) ምልክት መታየቱን ያረጋገጡት የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ግርማ በሌ ሁለቱም እህታማማቾች ተለይተዉ ክትትል እንደረግላቸዉና ናሙና ተወስዶ ወደ አዲስ አበባ መላኩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

ዉጤቱ እስኪገለፅ ድረስ ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ እያደረገ በትግዕስት እንዲጠባበቅ ያመላከቱት መምሪያ ኃላፊዉ ያልተገባና ሐሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት በሕዝቡ ዘንድ ፍርሃት እየፈጠሩ ያሉ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲቆጥቡ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አሜሪካ በቀጥታ ወደ ጦርነቱ ትገባ ይሁን ? እስራኤል በኢራን ላይ እያካሄደችው ባለው ጥቃት ውስጥ አሜሪካ ስለምትሳተፍበት ሁኔታ ለመወያየት ዶናልድ ትራምፕ በዋይት ሐውስ ውስጥ አስቸኳይ ስብሰባ ከከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው ጋር አድርገዋል። አንድ ሰዓት ከ20 ደቂቃ በቆየው ስብሰባ ላይ ዋነኛ አጀንዳ የነበረው እስራኤል በኢራን የኒውክሌር ማዕከላት ላይ እየፈጸመችው ባለው ጥቃት ውስጥ አሜሪካ መሳትፍ እንዳለባት…
#Update

እስራኤል በኢራን ላይ በፈጸመችው ጥቃት እስከ እሁድ ምሽት ድረስ 224 ሰዎች መገደላቸውን 1 ሺህ 277 መጎዳታቸውን ኢራን አስታውቃለች።

እስራኤል በበኩሏ በኢራን ጥቃት 20 ሰዎች እንደተገደሉባት ገልጻለች።

ተባብሶ በቀጠለው የሁለቱ ሀገራት ጦርነት ምክንያት ነዋሪዎች ከአካባቢያቸው እንዲወጡ በሁለቱም በኩል መልዕክት እየተላለፈ ነው።

ኢራን የእስራኤሏ ሃይፋ ከተማ በተወሰነው ክፍል ያሉ ነዋሪዎች ለህይወታቸው አደጋ ስለሚኖር አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።

እስራኤልም ነዋሪዎች ከተለያዩ የቴህራን ክፍሎች ለቀው እንዲወጡ እያስጠነቀቅች ነው። በዚህም ሰዎች በቻሉት አቅም ወደ አጎራባች ከተማ እየወጡ እንዳለ ተነግሯል።

መረጃው ቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኮሌጆች ወደ ጠቅላላ ትምህርት ለመግባት ዝግጅት ላይ ናቸው " -አስተያየት ሰጪ የዘርፉ ተዋናዮች ➡️ " አብዛኞቹ ኮሌጆች በራሳቸው መንገድ መክሰማቸው አይቀርም " አብዛኞቹ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መቀጠል ስላልቻሉ ትምህርት ቤት ከፍተው ለመስራት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ስማችን አይጠቀስ ያሉና በዘርፉ የተሰማሩ ተዋናዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ፣…
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት " ስጋት ላይ ጥሎናል " ያሉት አዲስ መመሪያ ምን ይዟል ?

የኢትዮጵያ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፣ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አሰራር ስርዓት ለማስያዝ በሚል ዳግም ምዝገባ በማካሔድ ላይ መሆኑን ከዚህ ቀደም በሰጣቸው መግለጫዎች አስታውቋል፡፡

በዚህ ሒደት 85 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአዲሱ መስፈርት መሰረት ዳግም ለመመዝገብ ፈቃደኛ ስላልሆኑ እንደሚዘጉም ተገልፆ ነበር፡፡

በመመሪያው መሰረት ዳግም ለመመዝገብ ያመለከቱት 287 ተቋማትም፣ አብዛኞቹ መስፈርቱን እንደማያሟሉ እየተገለፀ ይገኛል፡፡ ሆኖም እስካሁን ድረስ በአዲሱ መመሪያ ተመዝነው የትኞቹ እንደሚቀጥሉና እንደማይቀጥሉ አልተገለፀም፡፡

የዘርፉ ተዋናዮች በበኩላቸው፣ “ የዳግም ምዝገባ መመሪያውና የያዛቸው መመዘኛዎች የሚተገበሩና የሚያሰሩ አይደሉም፣ በዚህ መመሪያ ተመዝነው የሚቀጥሉት ተቋማት ጥቂቶች ብቻ ነው የሚሆኑት፣ አብዛኞቹም መዘጋታቸው አይቀሬ ነው ” ይላሉ፡፡ 

ለመሆኑ በዳግመ ምዝገባ መመሪያው ላይ የተቀመጡት ዋና ዋናዎቹ መመዘኛዎች ምን ይላሉ፣ የትምህርት ተቋማቱን ስጋት ላይ የጣሉትስ እንዴት ነው በማለት የጠየቅናቸው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተዋናዮች የሚከተለውን አስተያየት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል፡፡

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተዋናዮች ፦

“ በመመሪያ ላይ የተቀመጠውና የግል ተቋማትን አቅም ያላገናዘበው አንደኛው መመዘኛ የመማሪያ ህንፃን ይመለከታል፡፡ አንድ ተቋም አምስትና ከዚያ በላይ ፕሮግራሞችን የሚሰጥ ከሆነ አንድ ሙሉ ህንፃ ብቻውን መያዝ አለበት ይላል፡፡ አብዛኞቹ ኮሌጆች የሆነ አንድ ህንፃ ላይ የተወሰኑ ፎቆችን ተከራይተው የሚሰሩ ናቸው፡፡ ይህን ፎቅ ብቻችሁን ያዙት ሲባሉ አቅሙ የላቸውም፡፡

መንግስት እንዲህ አይነት መመሪያ ሲያወጣ በሊዝ መሬት እንድናገኝና የራሳችንን ህንፃ እንድንገነባ እንኳ ሁኔታዎችን አያመቻችም፡፡ ለትምህርት ዘርፍ የተመቻቹ ዕድሎች የሉም፡፡ ለምሳሌ ከውጭ የሚገቡ ለትምህርት አስፈላጊ የሆኑ መፃህፍት፣ ኮምፒዩተሮችና ቁሳቁሶች ከቀረጥ ነፃ መግባት ነበረባቸው፣ ይህ አልተደረገም፡፡

ሁለተኛው መስፈርት የሰው ሀይልን የሚመለከት ነው፡፡ አስተማሪዎችና የቢሮ ሰራተኞች የዶክትሬት ዲግሪ ያላቸው ይሁኑ ይላል፡፡

በእኛ ሀገር ያሉ ዶክተሮች ጥቂቶች ናቸው፡፡ ብዙዎቹ በመንግስት ድጋፍ በውጭ ሀገራት የተማሩ ናቸው፡፡ ቀደም ሲል የግል ኮሌጆች ከመንግስት ተቋማት መምህራንን እየተጋሩ ሲያስተምሩ ነበር፡፡

ይህም ጥያቄ ሲያስነሳ የመንግስት አካላት ባሉበት ውይይት ሲደረግበት ነበር፡፡ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን በሁለቱም ቦታዎች እንዲያስተምሩ/ዱዋል ኢምፕሎይመንት/ እንዲፈቀድላቸው ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በአንድ ፕሮግራም ውስጥ ብዙ ፒኤችዲ የያዙ መምህራን አሉ፣ ትርፍ ሰዓት አላቸው፣ ጫና አይበዛባቸውም፡፡ ስለዚህ በግል ኮሌጆችም ያስተምሩ የሚል ነበር ውይይቱ፡፡

ይህ ውይይት መጨረሻው ላይ ከደረሰ በኋላ ወደኋላ ተመለሰ፡፡ ምክንያቱ አይታወቅም፡፡ በዚህ ምክንያት ዶክተር መምህራንን አናገኝም፡፡

ከላይ ካለው ከዲኑ ጀምሮ እስከ ቢሮ ሰራተኞች ድረስ ዶክተሮች ይሁኑ ይላል መመሪያው፡፡ እስከ ማስተርስ ድረስ የሚያስተምሩት መምህራን ዶክተሮች ቢሆኑ እንስማማለን፣ ሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች ዶክተሮች ይሁኑ ማለት ግን አያስኬድም፡፡ በቂ የሰው ሀይል የለም ገበያው ውስጥ፡፡

ሶስተኛው ነጥብ፣ ከመውጫ ፈተና ጋር ተያይዞ የተቀመጠው ነው፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና፣ በትንሹ 25 ከመቶ ተማሪዎችን ያላሳለፈ ተቋም መዘጋት እንዳለበት ይገልፃል መመዘኛው፡፡ ይህን መስፈርት ልተግብረው ስትል ችግር ያመጣል፡፡

ለምሳሌ ፦ በ2016 ዓ.ም የነበረውን የመውጫ ፈተና ብነግርህ፣ 202 ተቋማት ተፈታኝ ተማሪዎችን አቅርበው፣ 25 ተቋማት አንድም ተማሪ አላሳለፉም፡፡ ከ25 በመቶ በላይ ያሳለፉትም 27 ናቸው፡፡ ከዚህ ውጭ ያሉት ይዘጋሉ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ መመዘኛ የሚደረስበት አይደለም፡፡ ይህ በሒደት ነው እንጂ በአንዴ ይተግበር መባል የለበትም፡፡

አራተኛው አስቸጋሪ መመዘኛ የምንለው የስፖርት ማዘውተሪያ በሚል የተቀመጠው ነው፡፡ ይህም በተወሰነ ደረጃ የሚያስኬድ አይደለም፡፡

አዲስ ተቋም ከሆነ ደግሞ ግማሽ ሚሊዮን ብር በዝግ አካውንት/የባንክ ሒሳብ ማስቀመጥ አለበት የሚልም አለ፡፡ ይህ በጣም ከባድ ነው፡፡ አዳዲስ ተቋማት ቁሳቁስ ነው ሊያሟሉበት የሚገባው ይህን ገንዘብ፡፡

ገበያው ላይ ያለው ተማሪም ዝቅተኛ ነው፡፡ በመመሪያው ላይ ያሉትን መመዘኛዎች ሁሉ አሟልተው ዳግም ተመዘገቡ እንኳን ብንል፣ ተቋማቱ ተማሪ የማያገኙ ከሆነ መዘጋታቸው አይቀርም፡፡ ስለዚህ ሞክሩት፣ ስርዓቱ በራሱ ከገበያ ያስወጣችኋል ነው እያሉን ያሉት በአጭሩ፡፡ ይህ ሁሉ ተደምሮ ሁኔታውን ከባድ ያደርገዋል፡፡

በአዲሱ መመሪያ ላይ ሀሳብ ሰጥተናል፡፡ በማህበራችን በኩል መሻሻል አለበት የምንለውን ጉዳይ በሰነድ አዘጋጅተን አስገብተናል፣ አንድም ማስተካከያ አልተደረገም፣ ጥያቄያችን መልስ አላገኘም፡፡

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ያዘጋጀው መድረክም፣ ይህን መመሪያ እወቁት የሚል እንጂ፣ በመመሪያው ላይ እንወያይ የሚል አልነበረም፡፡ የእኛን አስተያየት አካትቱ በሚል ብዙ ጭቅጭቅ ነበር፣ ሰሚ አላገኘንም፡፡ መጀመሪያ ያስተዋወቁን መመሪያ ፀድቆ ነው ወደ ትግበራ የተገባው፡፡

ጥያቄያችን ይህ እርምጃ በሒደት መወሰድ/መተግበር ነበረበት የሚል ነው፡፡ በአንዴ መደረግ የለበትም፡፡ በአንድ ቀን ሁሉንም ነገር ከመሰረቱ እንቀይረው ማለት አያስኬድም፣ አሉታዊ ተፅዕኖም ያስከትላል፡፡ ተማሪዎች ከአንድ ተቋም ወደ ሌላ ተቋም እየተዛወሩ በመንገላታት ላይ ናቸው፡፡ በርካታ ሰራተኞቻቸውን የበተኑ ተቋማት አሉ፡፡ የተቋማት አሰራር ስርዓት መያዝ አለበት፣ የትምህርት ጥራትም መረጋገጥ አለበት፣ ግን ደግሞ ይህ መሆን የሚችለው በሒደት ነው፡፡ ይህ መታየት አለበት፡፡ ”

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጣይ ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በዚህ ጉዳይ ዙርያ ምላሽና ማብራሪያ ይዞ ይቀርባል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
2025/06/19 01:52:06
Back to Top
HTML Embed Code: