#TikTok
" ግለሰቦቹ ለሕግ ቀርበው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ተመጣጣኝ ቅጣት ይቀጡ፤ መላው መስማት የተሳናቸው ማህበረሰብን በሕግ ፊት ይቅርታ ይጠይቁ " - መስማት የተሳናቸው ማሕበረሰቦች
መስማት የተሳናቸው ማሕበረሰብ እና ምልክት ቋንቋ ላይ " በማሾፍ " ቪዲዮዎችን በ #ቲክቶክ ላይ ያጋሩ፣ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ቢጠየቁም ፈቃደኞች ባለመሆናቸው በሕግ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙና ለሌሎች ማስተማሪያ እንዲሆኑ ያሰባሰቡትን ፊርማ ለአዲስ አበባ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስገብተው ምርመራ እንዳስጀመሩ ስሞታ አቅራቢዎቹ ገለጹ።
ወጣቶቹ መስማት የተሳናቸው ማህበረሰቦችንና የሚግባቡበትን ምልክት ቋንቋ ክብር የሚነኩ፣ በሕግ የሚያስጠይቁ ተግባራትን በመፈጸም ቪዲዮ ያሰራጩ መሆናቸውን ከሳሾቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የክሱ ሂደት አስተባባሪ መስማት የተሳናነው ጋዜጠኛና መምህር ናትናኤል ሽፈራው፣ " ድርጊቱ መስማት ለተሳነን፣ ለቤተሰቦቻችን፣ ለሀገራችን እንደማንጠቅም አድርጎ የሚያስገነዝብ ነው " ሲሉ ወቅሰዋል።
" በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የነቃ ተሳትፎ እንዳናደርግ የተሳሳተ ግንዛቤ የሚፈጥር፣ 'መስማት የተሳናቸው አይችሉም' የሚለው የቆየ እሳቤ በዚህ ዘመን እንዲንጸባረቅ በር የሚከፍት አደገኛ ድርጊት በመሆኑ በርካቶቻችን አስቆጥቷል " ነው ያሉት።
" ድርጊቱ የግንዛቤ ማነስ ይሆናል ብለን ያጋሩትን እንዲያጠፉ ብንጠይቅም ንቀው በማለፋቸው መብታችን ለማስከበር ጠንከር ያለ ዘመቻ ስንገባ ጥቂቶቹ ይቅርታ ቢጠይቁም ሌሎቹ ግን ልንቆጣጠረው በማንችለው ሁኔታ እያስፋፉት በመሆኑ ሕጉ በሚያዘው መሰረት ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ለሌሎች ማስተማሪያ እንዲሆኑ የሚመለከተው አካል የድርሻውን ይወጣልን " ሲሉ አሳስበዋል።
"ግለሰቦቹ ለሕግ ቀርበው ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ተመጣጣኝ ቅጣት ይቀጡ፤ መላው መስማት የተሳናቸው ማህበረሰብን በሕግ ፊት ይቅርታ ይጠይቁ " ሲሉም ገልጸዋል።
ጉዳዩን ለአዲስ አበባ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ በደቤዳቤና ባሰባሰቡት ፊርማ ማሳወቃቸውን ገልጸው፣ አስነዋሪ ድርጊቶች እንዳይስፋፉ ሚዲያዎች ትኩረት ሰጥተው እንዲዘግቡ በአንክሮ ጠይቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#ThikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
" አቶ አለማየው ጢሞቴዎስ ለ2 ዓመታት በጥብቅ ዲሲፕሊን ተገምግመው በማስጠንቀቂያ እና በሂስ እንዲታለፉ ተደርገዋል " - በሲዳማ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ያለ መከሰስ መብታቸው የተነሳው የቀድሞው የሲዳማ ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየው ጢሞቴዎስ በህግ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ። በክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ዛሬ ባሰራጨው መረጃ ፥ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ በተከታታይ 2 ዓመታት…
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ከስልጣን መነሳታቸው ተሰማ።
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ሽመልስ ቶማስ ከስልጣን መነሳታቸዉን የክልሉ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት እና የፖሊስ ኮሚሽኑ ምንጮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
" ከስልጣን ከመነሳታቸዉ በስተቀር በሕግ ስለመጠየቃቸዉ የደረሰን መረጃ የለም " ያሉን ማንነታቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጮች ፥ የፖሊስ አመራሮች ከእሳቸው መመሪያ እንዳይቀበሉ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።
ኮሚሽነሩ ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ከተማ በቁጥጥር ስር ከዋሉት የቀድሞ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ ጋር ጥብቅ ግንኙነትና እንደነበራቸዉ የገለፁት ምንጮቹ ከስልጣን ለመነሳታቸው ይህ ዋነኛ ምክንያት ስለመሆኑ አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኮሚሽነሩን ከስልጣን መነሳትና ከሕግ ተጠያቂነት ጋር በተያያዘ ከክልሉ ፍትሕ ቢሮ መረጃ ለማግኘት ያደረገዉ ጥረት ለጊዜዉ አልተሳካም።
ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የክልሉ መንግስትም ሆነ የፖሊስ ኮሚሽኑ በጉዳዩ ዙሪያ ያወጣዉ መግለጫ የለም።
ጉዳዩን እየተከታተልን የምናቀርበው ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

#ይነበብ🚨 " በወንጀል የተገኘን ንብረት #ህጋዊ_ማስመሰልና #ሽብርተኝነትን_በገንዘብ_የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር " የወጣ ረቂቅ አዋጅ ለሕ/ተ/ም/ቤት ቀርቧል። በዚሁ ረቂቅ ላይ በክፍል 5 ' ስለ ምርመራ ' ሰፍሯል። ረቂቁ ስለ #ምርመራ ምን ይላል ? - በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል ወይም ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ወይም የወንጀል ፍሬን ተከታትሎ ለመለየት…
#ኢትዮጵያ
በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን የሚመረምር ሰው፤ በምርመራ ወቅት ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ከ #ግድያ ውጪ የትኛውንም ዓይነት ወንጀል ቢፈጽም ተጠያቂ የማያደርግ አዋጅ ጸደቀ፡፡
በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል፡፡
አዋጁ በሽፋን ስር የሚደረግ ምርመራ (Under cover investigation) እንዲያስፈጽም የተመደበ ሰው፤ በግዴታ ላይ እያለ ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያትና ከፈቃዱ ውጪ በሆነ ከግድያ ወንጀል በስተቀር ለሚፈጽመው የወንጀል ድርጊት የወንጀል ክስ አይቀርብበትም ይላል።
የምክር ቤት አባሉ አለሙ ጎንፋ (ዶ/ር) በአዋጁ 5/15 ላይ የቀረበው ዐረፍተ ነገር ትንሽ ከባድ መስሎ እንደታያቸው ተናግረው አዋጁ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
" እንደዚህ ዓይነት አዋጅ በተለይ ሽብርን ለመከላከል ለሀገራችን ያስፈልጋታል " ሲሉ የምክር ቤት አባሉ ተናግረዋል፡፡
‘’ የሆነው ሆኖ ግን ' አንድ ሰው በግዳጅ ላይ እያለ ከግድያ በስተቀር ለሚፈጽመው ወንጀል አይጠየቅም ' ይላል፡፡ አንደኛ ወንጀል ፈጽሟል ይላል፣ ወንጀል ፈጽሞ አለመጠየቅ ትክክለኛ አይመስለኝም፡፡ ወይም ድርጊቶቹ ተዘርዝረው ህጋዊ መብት የተሰጠው ሰው ሚወስዳቸው እርምጃዎች ወንጀል አይደሉም ብለን ማለፍ እንጂ አንድ ሰው በግዳጅ ላይ እያለ ለሚፈጽመው ወንጀል ከግድያ በስተቀር የሚለውን ሰው እንደፈለገ እንዲሆን የሚያደርግ ነው’ " ሲሉ አለሙ (ዶ/ር) ሃሳበቸውን አስረድተዋል፡፡
ሌላ ሙሉቀን አሰፋ የተባሉ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው " እኔ በግሌ እንደተፎካካሪ የፖለቲካ ሰው አዋጁ ባለሀብቶችን፣ ጋዜጠኞችን፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን እና የታዋቂ ሰዎችን መብት የሚገድብ ነው " ብለዋል፡፡
" እንዲያውም የመናገር መብትን ይከለክላል የሚል እምነት ነው እኔ ያለኝ " ያሉት የምክር ቤት አባሉ ‘" ምክንያቱም አዋጁን ስናየው በ10 ዓመት ገድቦ ነው የወጣው’ " ሲሉ ተናግረዋል፡፡
" ህግ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ነው ተግባራዊ መደረግ ያለበት’ " ያሉት አቶ ሙሉቀን " ስለዚህ ከ10 ዓመት ወዲህ ብሎ ማውጣቱ የተወሰኑ ግለሰቦችን ወይም ቡድኖችን ለማጥቃት ያሰበ ስለሆነ ለሀገራችንም ጥሩ አይደለም የሚል እምነት አለኝ " ብለዋል፡፡
" በአለም አቀፍ ስምምነቶች ላይ እንደተገለጸው ሀይልን በመጠቀም፣ ንጹሃንን በማስገደድ አላማቸውን ለማስፈጽም የሚሳተፉ ተዋናዮችን ተጠያቂ ለማድረግ ሳይሆን አዋጁ እየዋለ ያለው በዋነኝነት የመንግስት ተቃዋሚዎችን፣ መንግስት ውስጥ ሆነው መንግስትን የሚተቹትን እና ጋዜጠኞችን ነው " ያሉት ደግሞ ሌላው የምክር ቤት አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ናቸው፡፡
" የአዋጁን ዝርዝር ካየንው በጣም አስገራሚ የሆኑ ድንጋጌዎችን ይዟል " ያሉት የምክር ቤት አባሉ " ለምሳሌ የፋይናንስ ድህንነት አገልግሎት አጠራጣሪ ግብይትን ለ7 ቀን አግዶ ማቆየት ይችላል ይላል ያውም ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ " ብለዋል፡፡
" አዋጁ በሽፋን ስር ምርመራ የሚያካሄድ መርማሪ ከግድያ ወንጀል ውጭ በሌላ ወንጀል አይጠየቅም ይላል " ያሉት ደሳለኝ ጫኔ(ዶ/ር) " ለምሳሌ መርማሪው በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ተደራድሮ ከሆነ ከወንጀለኛው ጋር መቀበሉን ብናውቅ አይጠየቅም ማለት ነው? ማሰቃየት ቢፈጽም፣ የመብት ጥሰት ቢፈጽም አይጠየቅም ማለት ነው? መሆን ያለበት ግን ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው አለም አቀፍ ድንጋጌዎች የተካተቱ ወንጀሎችን አለመፈጸሙ ነው " ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሌላው አቶ ዘካሪያስ የተባሉ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው " አዋጁ አንዳንድ የምክር ቤት አባላት እንደሚሉት ተቃዋሚን እና የሚዲያ ሰዎችን ለማፈን አይደለም " ብለዋል፡፡
አቶ ሳዲቅ አደም የተባሉ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው " አዋጁ ጠንከር ያለ መሆኑን ተናግረው ጠንከር ያለበት ምክንያትም ግልጽ ነው " ሲሉ ተናግረዋል፡፡
" ያለንበት ቀጠና አስቸጋሪ ነው፤ ሽብርተኝነት የሚበዛበት በመሆኑ የአዋጁ ከበድ ማለት ተገቢ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ከመብት አንፃር ሊታዩ የሚችሉ ነገሮች አሉ ያሉት አቶ ሳዲቅ ከህገ መንግስታችንም ስንነሳ ፍጹም የሚባል መብት የለም " ብለዋል፡፡
" ከመብቶች ሁሉ የላቀ ዋና መብት የሚባለው በህይወት የመኖር መብት ነው ይህ መብትም ፍጹም አይደለም " ሲሉ የተናገሩት የምክር ቤት አባሉ " ስለዚህ መብት የሚባለው ነገር ለህዝብ፣ ለማህበረሰብ እና ለሀገር ድህንነት ሲባል በየትኛውም ሀገር መብቶችን ፍጹማዊ አድርጎ የሚያስቀምጥ የለም " ሲሉ ተናግረዋል፡፡
" ስጋት አድርጎ የሚወስድ ወገን ሊኖር ይችላል ግን ለምን ይሰጋል? " ሲሉ የጠየቁት የምክር ቤት አባሉ " ይህ አዋጅ ሲወጣ ለመጠርጠርም መሟላት ያለበት ነገር አለ ማንኛውም ወገን እነዚህ በአዋጁ የተቀመጡ ነገሮችን ካሟላ አይነካም ዋናው መስፈርቱን ማሟላት ነው " ብለዋል፡፡
" አዋጁ የወጣው በንድፍ ሃሳብ የምንፈራቸውን ለመከላከል ሳይሆን በተግባር እያየን እየኖርንበት ያለውን ነው " የሚሉት አቶ ሳደቅ " ሽብርተኝነት በሀገራችን በስፋት አለ ኤ ቤ ሲ ብለን ልንጠራቸው የምንችላቸው ግለሰቦች እና ወገኖች አሉ ስለዚህ ይህን ለመከላከል ለምን እንሰጋለን " ብለዋል፡፡
የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኢሳ ቦሮ በበኩላቸው በሰጡት ምላሽ የሚደረገው ምርመራ ልዩ መሆኑን ተናግረው አዋጁ አንድን ቡድን ለማጥቃት ታስቦ የወጣ አይደለም ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው በማሻሽያ ረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ በሶስት ተቃዉሞ በአንድ ድምጽ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል፡፡
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።
#ShegerFM

" ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናውን ሲጨርስ Finish and Submit ሳያደርግ መውጣት የለበትም " - ትምህርት ሚኒስቴር የ2017 ዓ/ም ሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና ዛሬ ጀምሯል። አጠቃላይ 190 ሺህ ተፈታኞች ፈተናቸውን በኦንላይን ይወስዳሉ። ዛሬ የመጀመሪያ ቀን የኦንላይን ፈተና ውሎን ተከትሎ ከትምህርት ሚኒስቴር ማሳሰቢያ ሰጥቷል። በዚህም ፤ " ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናውን ሲጨርስ Finish and Submit…
#ExitExam : ከሰኔ 02 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል።
ከ190 ሺህ በላይ ተፈታኞች በ51 ዩኒቨርሲቲዎች በተዘጋጁ 87 የፈተና ማዕከላት የመውጫ ፈተናውን እንደወሰዱ ይጠበቃል።
ከእነዚህ ውስጥ 88 ሺህ የሚሆኑት ዳግም የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ናቸው።
በዛሬ ዕለት በተጨማሪም በክረምት የመምህራን ስልጠና መርሐግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለቆዩ ከ5 ሺህ በላይ መምህራን የመውጫ ፈተና ተሰጥቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመውጫ ፈተና ውጤት መቼ ይፋ እንደሚደረግ ከሚመለከታቸው አካላት በመጠየቅ ያቀርባል።
Via @tikvahuniversity

Photo
#Update
ኮማንደር ተስፋዬ ዴቢሶ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።
የሲዳማ ክልል ከሰሞኑ በፀጥታዉ ዘርፍ እየወሰደ እንደሆነ በተገለፀዉ ተቋማዊ ሪፎርም ዛሬ የቀድሞ የክልሉ ኮሚሽነር የነበሩትን ሽመልስ ቶማስ በዛሬዉ ዕለት ከስልጣን ማንሳቱ የተሰማ ሲሆን ማምሻዉን ኮማንደር ተስፋዬ ዴቢሶን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርጎ ሾሟቸዋል።
አዲሱ ኮሚሽነር ተስፋዬ ዴቢሶ ሲዳማ በዞን መዋቅር ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ በልዩ ልዩ ፖሊሳዊ አመራሮች ተቋሙን ያገለገሉና በአሁኑም ወቅትም የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ሆነዉ ሲሰሩ እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተለያዩ ምንጮች አረጋግጧል።
ይህ መረጃ በተዘጋጀበት ወቅት ስለ ቀድሞዉ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ከኃላፊነት መነሳት ዙሪያ ይፋ የተደረገ መግለጫ የሌለ ሲሆን የፖሊስ ኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የአዲሱን ኮምሽነር ሹመት ከደቂቃዎች በፊት ይፋ አድርጎታል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ አዳዲስ መረጃዎችን እየተከታተለ የሚያቀርብ ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በነጻ ይመዝገቡ !
Big 5 Construct Ethiopia እና East Africa Infrastructure & Water Expo
በኢትዮጵያ ትልቁ የኮንስትራክሽን እና የመሠረተ ልማት አውደ ርዕይ በዚህ ሰኔ ይመለሳል። Big 5 Construct Ethiopia እና East Africa Infrastructure & Water Expo ከሰኔ 19–21፣ 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።
🔥 ምን ይጠብቁ፦
✅ ከ20 በላይ አገራት የተውጣጡ 180+ ተሳትፊ ኩባንያዎች
✅ በኢትዮጵያ አዲስ የሆኑ ምርቶች
✅ በነፃ የሚሰጡ 20+ የCPD ሰርተፊኬት ያላቸው መድረኮች
ይህ ልዩ የኔትዎርኪንግ እድል እንዳያመልጥዎ፤ አሁኑኑ በነፃ ይመዝገቡ።
👉 https://www.big5constructethiopia.com/Tikvah_Ethiopia

#Addis_Bank
የባንካችን አርማ ትርጓሜ !
አዲስ ባንክ አ.ማ.
ለስኬትዎ የታመነ
Follow us
Website | Telegram | LinkedIn | Facebook | Instagram
#Addisbank #logoconcept #WhereTrustMeetsSuccess

#ትግራይ
በትግራይ ክልል ከሁለት ወር በፊት የተሾሙ የቢሮ ሃላፊ ተሽረው በሌላ ሃላፊ ተተኩ። እንዲህ ያለው ሹመት ያልተለመደ ነው ተብሏል።
አስተያየት ሰጪዎች " ሹመቱ ህወሓት መካከል ቡድናዊ ሽኩቻ መፈጠሩ ያሳያል " ብለዋል።
ከሹመት የተሻሩና የተተኩ እነማን ናቸው ?
አቶ ተወልደ ገ/ፃድቃን ነባር የህወሓት ታጋይ ናቸው።
ባለፉት 34 ዓመታት ከትግራይ የተለያዩ የዞን አስተዳዳሪነት እስከ የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ፅሕፈት ቤት ሃላፊ በመሆን ሰርተዋል።
በታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) የሚመራ ጊዚያዊ አስተዳደር ወደ ሃላፊነት ሲመጣ በህወሓት እጩ አቅራቢነት ባይቶና በተባለ ተቃዋሚ ፓርቲ አባል ሲመራ የነበረውን ተክተው የክልሉ የውሃ ሃብት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሾሙ።
የአቶ ተወልደ ሹመት በአቶ ጌታቸው ረዳ ሲመራ የነበረው ጊዚያዊ አስተዳደር ለተቃዋሚ ፓርቲ ሰጥቶት የነበረው ሁለት የቢሮ የሃላፊነት ቦታ ወደ አንድ የሚያሳንስ በመሆኑ ተቃውሞ ገጥሞት ነበር።
ከፓለቲካ እንቅስቃሴ በተሰረዘው ህወሓት መካከል " ቡድናዊ ሽኩቻ አለ " ከሚል አስተያየት ውጪ የቢሮ ሃላፊው በሁለት ወር ውስጥ በምን ምክንያት ከሃላፊነት እንደተሻሩ በይፋ የተገለፀ ነገር በሌለበት ተነሱ።
የቢሮ ሃላፊው አቶ ተኽላይ ገ/መድህን በተባሉ የህወሓት የስራ አስፈፃሚ አባል መተካታቸው ተገልጿል።
አቶ ተኽላይ ገ/መድህን የሹመት ደብዳቤያቸው ከፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) እጅ መቀበላቸው የክልሉ የውሃ ሃብት ቢሮ ምንጮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

#Ethiopia #USA
በአሜሪካ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ ትራምፕ ጋር በነጩ ቤተመንግስት የመጀመሪያ ግንኙነታቸዉን አካሂደዋል።
አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ነጩ ቤተመንግስት ሲደርሱ በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የሚያንጸባርቅ ዲፕሎማሲያዊ አቀባበል እንደተደረገላቸው በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቋል።
" ይኸው ግንኙነት በቀጣይ ጊዜአት ለሚደረጉ በርካታ ውይይቶች መጠናከር ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል " ያለው ኤባሲው " ኢትዮጵያና አሜሪካ ከ120 ዓመታት በላይ የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው ናቸው በሁለቱ አገራት መካከል እንደ ሰላም፣ ጸጥታና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ጠንካራ አጋርነት ከመፍጠር አንጻር ያሉ ዕድሎችም ሰፊ ናቸው " ብሏል።
አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም በውይይቱ ወቅት የተገኙትን ስቴት ሴክሬተሪ ማርኮ ሩቢዮ ጋርም ተገናኝተዋል።
Photo credit: The White House

#EthiopianAirlines🇪🇹
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስካይትራክስ ለስምንተኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ ክብርን ተቀዳጅቷል።
ከዚህም በተጨማሪ ፦
🏆 የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክፍል
🏆 የአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክፍል እና
🏆 በአፍሪካ ቢዝነስ ክፍል ምርጥ ምግብ አገልግሎት ሰጪ አየር መንገድ በመባል ሽልማትን ተጎናጽፏል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM