TIKVAH-ETHIOPIA
#ExitExam የ2017 ዓ/ም የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ውጤት ለዩኒቨርሲቲዎች እየተላከ ይገኛል። ትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና ውጤት ለተቋማት እየላከ እንደሚገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተቋማቱ ያገኘው መረጃ ያሳያል። ውጤቱ የደረሳቸው የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸው ውጤታቸውን በሬጅስትራር በኩል እንዲያዩ መልዕክት እያስተላለፉ ናቸው። ካስፈተኗቸው ተማሪዎች መካከልም ምን ያህል ተማሪዎች ፈተናውን…
#ExitExamResult
“ ዳታውን አናላይዝ እያደረግን ነው ገና። ውጤት ግን ተለቋል ” - ኤባ መጂና (ዶ/ር)
በዘንድሮው መውጫ ፈተና ምን ያህል ተማሪዎች እንዳለፉና እንዳላለፉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።
የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኤባ መጂና (ዶ/ር) በሰጡት ምላሽም “ ዳታውን አናላይዝ እያደረግን ነው ገና። ውጤት ግን ተለቋል ” ሲሉ ተናግረዋል።
ስንት ተማሪዎች አለፉ ? ስንት ተማሪዎች ወደቁ ? የሚለውን ጥያቄ በተመለከተ አናላይሲሱ እየተሰራ እንደሆነ፣ ነገ ማብራሪያ እንደሚሰጡን መሪ ሥራ አስፈጻሚው የገለጹ ሲሆን፣ ነገር ግን ውጤቱ ስለተለቀቀ ተማሪዎች ማየት እንደሚችሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
ከዚህ ቀደም ውጤት በሚለቀቅበት በተለመደው ድረ ገጽ ውጤት ማየት እንደሚቻል መሆኑን ጠቁመዋል። “ ውጤት የሚታየው ያው ከዚህ በፊት በነበረው ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት በበኩሉ፣ ተማሪዎች እያዩ መሆኑን፣ ማለፊያው 50% መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል። ምን ያህል ተማሪዎች እንዳለፉና እንዳላለፉ መረጃው እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።
https://result.ethernet.edu.et
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በነፃ ይመዝገቡ !
Big 5 Construct Ethiopia እና East Africa Infrastructure & Water Expo
ከመስመር እስከ ከባድ መሳሪያ፣ ከአዳዲስ ቴክኖሎጂ እስከ የስልጣን መፍትሄዎች፣ ለየትኛውም የኮንስትራክሽን እና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችዎ የሚፈልጉትን ሁሉ በአንድ ቦታ ያግኙ። Big 5 Construct Ethiopia እና East Africa Infrastructure & Water Expo የሚያስተናግዱት እዚህ ነው።ከየትኛውም ዓለም አቀፍ አገር የመጡ 180+ ባለስልጣን ብራንዶችን በአንድ ጣቢያ ይያዙ፤ ፕሮጀክቶችዎን ለማንቃት የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችንና መፍትሄዎችን ያግኙ።አሁኑኑ በነፃ ይመዝገቡ:👉 https://www.big5constructethiopia.com/Tikvah_Ethiopia📅 ሰኔ 19–21፣ 2017 ዓ.ም (26–28 June 2025)📍 ሚሊኒየም አዳራሽ፣ አዲስ አበባ

#Tigray " 1.2 ሚሊዮን ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ አልተመለሱም፤ የጦርነቱ ጦስ ዛሬያችን ብቻ ሳይሆን ነገያችንም እያጨለመው ነው " - የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ኪሮስ ጉዑሽ (ዶ/ር) የፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት ሙሉ ሆኖ ባለመተግበሩ 1.2 ሚሊዮን ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ እንዳልተመለሱ ገልጹ። " የጦርነቱ ጦስ ዛሬያችን ብቻ ሳይሆን ነገያችንም እያጨለመው…
#Tigray
" የተደፈረው ግዛትና ተፈናቃዮች በሰላማዊ መንገድ ለመመለስ የሚደረገው ሁሉን አይነት ጥረት ካልተሳካ ዝም ብሎ የሚተው እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል " - አቶ አማኒኤል አሰፋ
በሺህዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የተገኙበት ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የሚጠይቅ " ይበቃል ! " በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሰላማዊ ሰልፍ በመቐለ ተካሂደዋል።
ዛሬ ሰኔ 13/2017 ዓ.ም ለሦስተኛ ቀን የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ውሳኔ መሰረት የመንግስት ሠራተኞች ስራቸውን በማቆም የታደሙበት ነው።
በሰልፉ ማጠቃለያ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የሚጠይቁ በርካታ መልእክቶች ተደምጠውበታል።
በሰልፉ መልእክት ያስተላለፉት የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ አማኒኤል አሰፋ " የተደፈረው ግዛትና ተፈናቃዮች በሰላማዊ መንገድ ለመመለስ የሚደረገው ሁሉን አይነት ጥረት ካልተሳካ ዝም ብሎ የሚተው እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል " ብለዋል።
" ከተፈረመ ሦስት ዓመት ሊሞላ ወራት የቀሩት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተኩስ ከማቆም በዘለለ የተፈናቃዮች ደህንነት ማረጋገጥ አቅቶታል " ሲሉ ተደምጠዋል።
" የትግራይ ህዝብ ሉአላዊ ግዛቱ ተቀምቶ ፣ ከቄዩ ተፈናቅሎ ተሰዶ በማያቋርጥ መከራ ተዘፍቆ ይገኛል " ያሉት ምክትል ፕሬዜዳንቱ " የፌደራል መንግስት በጦርነት ያላሳካው ድል በፕሪቶሪያ ውል ስምምነት ስም የተከፋፈለች ትግራይ እንድትኖር የዲሞግራፊ ለውጥ ለመቀየር እየተጠቀመበት ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።
" የፌደራል መንግስት ለሰላም ዋጋ ሰጥቶ እንዲሰራ ደጋሜ ጥሪ እናቀርባለን " ያሉት አቶ አማኒኤል " የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮች የኩርድ ህዝቦች ዕጣ ፈንታ እንዲደርሳቸው የሚፈቅድ ትክክለኛ ያልሆነ ተግባር መቆም አለበት " ሲሉ ተናግረዋል።
ዛሬ በመቐለ ሮማናት አደባባይ የሦስት ቀናት ማጠቃለያ ሰላማዊ ሰልፍ ፦
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት
- የሁሉም የሃይማኖት ተቋማት አመራርና ምእመናንና ምእመናት
- የሚድያ ባለሙያዎች በሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሰራተኞች
- ተማሪዎች
- መምህራንና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች መገኘታቸው ተነግሯል።
የፌዴራል መንግሥት ሁሉም ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ፅና ፍላጎ እንዳለው በተደጋጋሚ መግለጹ አይዘነጋም።
የቀድሞ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳም አሁን ላይ በትግራይ ትርምስ እንዲፈጠር እየሰራ ያለው የህወሓት አንጃ ተፈናቃዮችን ለፖለቲካ ፍጆታ በመጠቀም ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዳይመለሱ እየሰራ መሆኑን አስገንዝበው ነበር።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከትላንት በስቲያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት የትግራይ ተፈናቃዮችን ጉዳይ አንስተው ነበር።
" የተፈናቀሉ ሰዎች መመለስ በሚመለከት 100% ዝግጁ ነን እኛ 100% ፤ ነበርን ነን ፤ ራያ እኮ መልሰናል ፤ ራያ ተመልሰዋል የተፈናቀሉ ሰዎች ወልቃይትም እንደዛ አይነት ፍላጎት ነው ያለን። ከጊዜያዊ መንግሥቱ ጋር እየተነጋገርን ነው በእኛ በኩል እነኚያ ዜጎች ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀሚያ ሳይሆኑ ቦታቸው ቢመለሱ ከማንም በላይ ኢትዮጵያ ታተርፋለች " ብለዋል።
" በእኛ በኩል አንዴ አይደለም 10 ጊዜ እቅድ ያወጣነው ፤ የትግራይ ጉዳይ ብዙ የማይገደን ፣ የማያሳስበን አይመሳላችሁ " ሲሉ ገልጸዋል።
" ያስጨነቀንን ጉዳይ በግልጽ እንድታውቁት ግን ትንሽ ዘመን ተቀይሯል የዛሬ 4 አመት 5 አመት የነበረን የውጊያ አቅም የነበረን ቴክኖሎጂ እና ዛሬ ትንሽ ይለያያል። በተቻለ መጠን maximum ውጊያ ብናስቀር ይሻላል ለምን ? እንደምታውቁት በባለፈው ውጊያ ያኔም ተናግሪያለሁ ከትግራይ ወጣቶች ከትግራይ እናቶች በላይ የተጎዳ ሰው የለም ፤ የሚያስገድሉ ሰዎች ይፎክራሉ አስገዳዮች ይፎክራሉ ሟቾች ግን ጉዳዩን ሳያውቁ ይጠፋሉ ያ እንዳይፈጠር ነው maximum ትዕግስት የምናደርገው " ብለዋል።
" ትግራይ ውስጥ ሊመጣ የሚገባው ልማት ፤ ሊሰራ የሚገባው ስራ በበቂ ተሰርቷል ብለን አናምንም እንጂ የሚደረጉ ሙከራዎች unconstitutional ልምምዶች እንዳሉ ስለማናውቅ አይደለም በደምብ ነው የምናየው " ሲሉ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

" የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል ! "
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ የ8 ዓመቷ ልጅ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት በመፈጸምና በመግደል የተጠረጠሩ ግለሰቦች የግብረስጋ ድፍረት ወእና ግድያ ወንጀል መዝገብ ተከፍቶባቸዉ በሰውና በህክምና ማስረጃ በመረጋገጡ የቅጣት ዉሳኔ እንደተላለፈባቸው የሶዶ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ም/ኮማንደር ሀብታሙ አስፋዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰረድተዋል።
ዳዊት ሻንቆ እና ታምራት ኦሳ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በሶዶ ከተማ ' ፋና ዎንባ ' ተብሎ ከሚጠራዉ አከባቢ ሰኔ 16/ 2016 ዓ/ም የ8 ዓመት ልጅን ከቤት አታለው ወደ ጫካ በመውሰድ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል ከፈጸሙ በኋላ ወዲያዉኑ ሕይወቷ ያልፋል።
በዚህም ጊዜ እራሷን ያጠፋች ለማስመሰል በአከባቢዉ በሚገኝ አንድ ኦና ቤት በማስገባት አስክሬኗን በማንጠልጠል ከአከባቢው መሠወራቸው በፖሊስ ምርመራ መረጋገጡን አዛዡ ገልፀዋል።
የወንጀል ድርጊቱ ጥቆማ የደረሰዉ የሶዶ ከተማ ፖሊስ ግለሰቦቹን በጠንካራ ክትትል ይይዛቸዋል።
የምርመራ መዝገብ በማደራጀት ለዐቃቤ ሕግ ያቀርባል።
ጉዳያን የተከታተለው የወላይታ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ግለሰቦቹን በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ም/ኮማንደር ሀብታሙ አስፋዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahEthiopia

#ETHIOPIA #USA
ዛሬ ጥዋት ላይ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካ ማሪን ኮርፕስ ጄኔራል እና አፍሪኮም አዛዥ ከሆኑት ጄነራል ማይክል ላንግሌይ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን አሳውቀዋል።
ውይይቱ የጋራ ፍላጎት በሆኑ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ እንዳተኮረ አመልክተዋል።
አሜሪካም ጄነራሏ ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ውይይት ማድረጉን አሳውቃለች።
ውይይቱ በአፍሪካ ቀንድ የአልሸባብ እና የአይኤስ የሽብር ስጋትን መከላከል ላይ ያተኮረ እንደነበረም ጠቁማለች።
በሌላ በኩል ፥ የአሜሪካ በአፍሪካ ዕዝ አዛዥ (AFRICOM) ጀነራል ማይክል ላንግሌይ ኢትዮጵያን እንደጎበኙ አሜሪካ አሳውቃለች።
በዚህም ወቅት ከኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ጋር መምከራቸውን ገልጻለች።
ምክክራቸው ፦
- ቀጠናዊ ሰላምና ደህንነት፣
- በቀጠናው ላይ ያሉ ችግሮችን በጋራ የመፍታት ጥረት፣
- በሱማሊያ ያለውን ሽብርተኝነት መዋጋት ላይ፣
- በአፍሪካ ቀንድ የረዥም ጊዜ መረጋጋትን ስለ መደገፍ ትኩረት ያደረገ እንደሆነ አሜሪካ አሳውቃለች።
የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ምን አለ ?
ሀገር መከላከያ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የአሜሪካ በአፍሪካ ዕዝ አዛዥ (አፍሪኮም) ጀነራል ሚካሄል ላንግሌይ የተመራ ልዑክን ተቀብለው እንዳነጋገሩ ገልጿል።
ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ " አሜሪካና ኢትዮጵያ ከመቶ ዓመት በላይ ግንኙነት አላቸው " ያሉ ሲሆን " ሁለቱ ወዳጅ ሀገራት በመከላከያ ዘርፉ በቀጣይም በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ ደርሰዋል " ሲሉ ገልፀዋል።
በውይይቱ በቀጠናው ባለው ሁኔታ የጋራ መግባባት የተያዘበትና በተለይም በቀይ ባህር ፣ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በሚታዩ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ለጋራ ተጠቃሚነት በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መስማማታቸውን አመልክተዋል።
የአፍሪኮም አዛዥ ጀነራል ሚካኤል ላንግለይ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድና በቀጠናው ከፍተኛ ሚና ያላት ሀገር መሆኗን እንደተናገሩ መከላከያ አሳውቋል።
በቀጣይ በወታደራዊና በፀጥታ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን እንደተናገሩም አክሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
Photo ፦ PM Office & US Embassy