" ኦነግ የሚቆም ትግል አልጀመረም ፤ የተቋቋመበትን አላማ ከግብ ሳያደርስ አያቆመም " - አቶ ዳውድ ኢብሳ
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ ) ከ5 ዓመታት ቆይታ በኃላ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ጽ/ቤት ዳግም መክፈቱን ተከትሎ ይፋዊ ፕሮግራም በጽ/ቤቱ አካሂዷል።
በወቅቱ መስሪያ ቤቱ ሊዘጋ የቻለው በኦነግ አመራሮች መካከል አለመግባባት በመፈጠሩ ነበር።
ዛሬ በተካሄደው በዚህ የመክፈቻ መርኃግብር ላይ የፖርቲው ሊቀ-መንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳ ባደረጉት ንግግር " ኦነግ የሚቆም ትግል አልጀመረም፥ የተቋቋመበትን አላማ ከግብ ሳያደርስ አያቆመም " ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ዳውድ በንግግራቸው ኦሮሞ ያካሄደውን ትግል ወደኋላ በመመለስ ያስታወሱ ሲሆን፥ ከሜጫ እና ቱለማ ማኅበር ምስረታ ጀምሮ እስከ ዛሬ ያለው እንቅስቃሴ በሰላም ለሚደረገው ትግል እድል ካለመስጠት የመነጨ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም ከጓደኞቻቸው ጋር ያለፉበትን ውጣ ውረዶች በመስታወስ " የሚቆም ትግል አልጀመርንም " ያሉ ሲሆን በሰላም መንገድ የመታገል ዕድሉ መስፋት አለበት ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል።
ሊቀመንበሩ ፥ ላለፈው ምርጫ በሚደረግ እንቅስቃሴ አሁን የተመለሰላቸውን ጨምሮ በሌሎች አከባቢዎች ያሉ ቢሮዎቻቸውም እንደተዘጋባቸው አባላቶቻቸው ለእስርና ለእንግልት እንደተጋለጡ በማስታወስ በኋላ ላይም በፓርቲው መሪዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ከምርጫው እንዳሶጣቸው ነው የገለጹት።
በነበሩት ጊዜያት ፓርቲያቸው ከኃላፊዎች እስከ አባላት ድረስ ብዙ ስቃይ እንደደረሰባቸው ገልጸዋል ፤ በዚሁ መንገድ ህወታቸውን ያጡ የመኖራቸውንም አመልክተዋል።
እዚህ ላይ አቶ በቴ ኡርጌሳን በማንሳት ተናግረዋል።
አቶ ዳውድ " እስካሁን ድረስ ባልታወቀ አካል ተገድሏል (አቶ በቴ ኡርጌሳ) ፤ በህይወት ባለ ጊዜ ባደረገው ትግል ብዙ ነገር አድርጎልናል " በማለት አመስግነዋል።
አቶ ዳውድ፥ መንግስት በሰላም መንገድ ለሚደረገው ትግል እድል እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።
በተጨማሪም ፥ ዋና መስሪያ ቤታቸውን ለማስመለስ ትልቅ ትግል እንደነበር በማንሳት፣ በዚህ ትግል ውስጥ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትልቁን ድርሻ እንደተወጡ ተናግረዋል።
ሌሎች ሳይመለስላቸው የቀሩትን የተቋሙ መስሪያ ቤቶች እንዲመለስላቸው በመጠየቅ ሂደት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አቶ ዳውድ ኢብሳ ፥ የብሔራዊ ምክክሩን በተመለከት ሁሉን አቀፍ ሀገራዊ ምክክር አስፈላጊ መሆኑን በመጠቆም አሳታፊ ውይይትና ፍትህ የተሞላበት እንዲሆን እየጠየቁ እንደነበርና ያ ሳይሆን ሲቀር መሳተፍ እንደተዉ ተናግረዋል።
#OLF #BBCAfaanOromoo
@tikvahethiopia

" አሁንም የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር እኔ ነኝ " - ራሔል ባፌ (ዶ/ር)
በትናንትናው ዕለት፣ ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም፣ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲዘዋወር የነበረው፣ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲን የሚመለከተው መግለጫ ሐሰተኛ መሆኑን፣ ፓርቲውን በምክትል ሊቀመንበርነት የሚመሩት ራሔል ባፌ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡
" የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ ምክትል ሊቀመንበሯን ከኃላፊነት አገደ " በሚል የተሰራጨው መግለጫ፣ ከስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት በታገዱ ሰዎች በሐሰተኛ ማህተምና ቲተር ተዘጋጅቶ መለቀቁን ራሔል ባፌ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃለመጠይቅ ገልፀዋል፡፡
ራሔል ባፌ (ዶ/ር) በዝርዝር ምን አሉ ?
" አሁን የሶዴፓ ምክትል ሊቀመንበር ነኝ፣ ሙሉ የሊቀመንበርነትን ስልጣን ይዤ ነው የምሰራው፡፡ በጠቅላላ ጉባኤያችን ሊቀመንበር እስክንመርጥ ድረስ ማለት ነው፡፡ የመተዳደሪያ ደንባችንም የሚለው ይህንን ነው፣ የማዕከላዊ ኮሚቴውም የሰጠኝ ስልጣን ይህ ነው፡፡
የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ባለፈው መስከረም ወር ላይ ከዚህ አለም መለየታቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ/ሶዴፓ የስራ አስፈፃሚ አባላት መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል፡፡
ይኸው አለመግባባት የሊቀመንበራችንን ህልፈት ተከትሎ፣ ባለፈው ጥር 4 ቀን 2017 ዓ.ም የተካሔደው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እንዳይካሔድ፣ አራት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት አሉታዊ እንቅስቃሴ አድርገዋል፡፡ ምርጫ ቦርድንም ስብሰባውን እንዲያግድ በደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡
ለምርጫ ቦርድ ባስገቡት ደብዳቤ ላይ፣ ሌሎች ሁለት አባላትም አብረዋቸው እንደሆኑ በማስመሰል በአጠቃላይ ስድስት አባላት ሆነው የጥር 4ቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ የስብሰባ ቀን እንዲራዘም መጠየቃቸውን በሐሰት ገልፀዋል ሰዎቹ፡፡
ሆኖም፣ ምርጫ ቦርድ ጉዳዩን በማየትና ለእኛም በማሳወቅ፣ 31 አባላት የሚሳተፉበትን የማዕከላዊ ኮሚቴውን ስብሰባ መከልከል እንደማይችል ገልፆላቸዋል፡፡ ለምርጫ ቦርድ ባስገቡት ደብዳቤ ላይ የሁለት ሰዎችን ስም በሐሰት በማስገባትና ፊርማቸውንም አስመስለው በመፈረም ለፈጠሩት ችግርም ለፖሊስ አመልክተን ክትትል ሲደረግባቸው ነበር፡፡
በዚህ አመት ባለፈው ጥር 4 ቀን 2017 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በተካሔደ የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ፣ አራቱ ሰዎች በፈጠሩት ችግር ምክንያት ከስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት ታግደዋል፡፡
31 አባላት ያሉት ማዕከላዊ ኮሚቴው፣ ከ 10 ስራ አስፈፃሚ አባላት 4ቱን በማገድ፣ የፓርቲው ስራ በ6ቱ አባላት ብቻ እንዲከናወን፣ እንዲሁም ጉዳያቸው በሚቀጥለው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጠው ወስኗል፡፡
የሚቀጥለውን የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ለመጥራት በዝግጅት ላይ እያለን ነው አሁን ሐሰተኛ ማህተምና ቲተር በማስቀረፅ፣ የትናንትናውን ሐሰተኛ መግለጫ የለቀቁት፡፡
በመግለጫው ላይ እንደተጠቀሰው፣ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ምክትል ሊቀመንበሯን አግዷል ይላል፡፡ ስራ አስፈፃሚ እንዲህ ዓይነት ስልጣን አልተሰጠውም በመተዳደሪያ ደንባችን፡፡
ሐላፊዎችን መሾምና መሻር የሚችለው በትንሹ 500 አባላት የሚሳተፉበት ጠቅላላ ጉባኤው ነው፡፡ በመሐል ግን 31 አባላት ያሉት ማዕከላዊ ኮሚቴው ሐላፊዎችን የማገድ ስልጣን በውክልና ተሰጥቶታል፡፡ ግን የመጨረሻውን ውሳኔ በጠቅላላ ጉባኤ ነው አቅርቦ የሚያፀድቀው፡፡
ይህን ባደረጉት አባላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ በነገው ዕለት ለፖሊስ እናመለክታለን፡፡ በቅርቡ አስቸኳይ የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ጠርተን በጎደሉት የስራ አስፈፃሚ አባላት ምትክ እናሟላለን፣ በታገዱት ሰዎች ጉዳይ ላይም የመጨረሻ ውሳኔ እንሰጣለን፡፡ "
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ጦርነቱ ወደ ሌላ አቅጣጫ እያመራ ይሁን ?
🇮🇷 " ብዙ አማራጮች በእጃችን አለ፤ ሊሆን ይችላል (የሆርሙዝ መዘጋት) " - ኢራን
🇺🇸 " አራን ሰርጡን ብትዘጋ መጥፊያዋ ይሆናል " - አሜሪካ
ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን ለመዝጋት የደኅንነት ምክር ቤቱን ውሳኔ እየጠበቀች ነው።
የአለም 20 በመቶ የነዳጅ ምርት የሚቀርብበትን የሆርሙዝ ሰርጥ እንዲዘጋ የኢራን ፓርላማ ሲወስን የደኅንነት ምክር ቤቱ የመጨረሻ ውሳኔ እየተጠበቀ እንደሚገኝ የኢራን የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
አሜሪካ ኢራን ላይ ጥቃት ከፈፀመች በኋላ የጦርነቱ ሂደት ወደ ሌላ አቅጣጫ እያመራ ሲሆን ስለ ሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት የተጠየቁት የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርም " ብዙ አማራጮች በእጃችን አለ፤ ሊሆን ይችላል " ብለው መልሰዋል።
የአያቶላህ አሊካሚኒ ከፍተኛ አማካሪም ሃገራቸው በአሜሪካ በተጠቃች በኋላ ኢራን ሰርጡን መዝጋት እንዳለባት እና የአሜሪካን መርከብ ማጥቃት እንዳለባት ሲገልፁ ነበር።
የምክር ቤቱ ውሳኔ የአለምን ኢኮኖሚ በተለየ ሁኔታ የነዳጅን ዋጋ ሊያሻቅብ የሚችል ሲሆን የሚሰጠው ውሳኔ ይጠበቃል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአሜሪካ ምክትል ፕረዚዳንት ጄዲ ቫይንስ ፤ የኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን መዝጋት መጥፊያዋ እንደሚሆን ገልየዋል።
ቫይንስ ሃገራቸው አሜሪካ ወደ ጦርነት ውስጥ የገባችው ከኢራን ጋር ሳይሆን ከኒውኪሊየር ፕሮግራሟ ጋር እንደሆነ ተናግረዋል።
በ100% መተማመን የአሜሪካ ጥቃት የኢራንን የኒውኪሊየር ጣቢያዎች አጥፍቷል ወይ ? በሚል ተጠይቀው "ወደ እንደዚህ አይነት የደህንነት መረጃዎች መግባት አልፈልግም፤ የአሜሪካ የምሽቱ ጥቃት ግን የኢራንን ኒውኪሊየር የመታጠቅ አቅም በእጅጉ አዘግይቶታል " ብለዋል።
ጥቃቱን ተከትሎ ኢራን በሆርሙዝ ሰርጥ አካባቢ ያለውን የመርከብ እንቅስቃሴ ልትረብሽ ትችላለች በሚል የተጠየቁት ጄዲ ቫንስ "እሱ ለኢራን መጥፊያዋ ይሆናል" ሲሉ መልሰዋል።
ሆርሙዝ ቢረበሽ ምን ይፈጠራል ?
- ሳውዲ አረቢያ፣ ኢራን፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ፣ ኩዌት ኢራቅ ፣ ኳታር አብዛኛውን የነዳጅና የተፈጥሮ ጋር ምርታቸውን ወደ ውጭ የሚልኩት በሆርሙዝ ሰርጥ ነው።
- ነዳጅ ላኪዎች የሚጠቀሙበት ሰርጥ ስለሆነ የነዳጅ እጥረት ይከሰታል በመሆኑም ዋጋው ይወደዳል።
- ብዙ ሀገራት በዚህ ሰርጥ በሚመጣው ነዳጅ ነው ኢኮኖሚያቸው የሚንቀሳቀሰው በመሆኑም ሰርጡ ቢረበሽ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ይፈጠራል።
- የተለያዩ ሸቀጦችም፣ የኢንዱስትሪ እቃዎች፣ ምርቶች በመርከብ በዚህ ሰርጥ ያልፋሉ ይህ ሰርጥ ቢረበሽ የሎጂስቲክስ ስራዎች ችግር ይገጥማቸዋል የዓለም የንግድ ስርዓት ላይም ትልቅ ችግር ይፈጠራል። ዋጋም ይወደዳል።
መረጃው ከተለያዩ የውጭ ሀገራት መገናኛ ብዙሃን የተሰባሰበ ነው።

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Ethiopia
" ኢትዮጵያ በሚቀጥለው መስከረም ወር ላይ የመጀመሪያ ዙር የጋዝ ምርት ለገቢያ ታቀርባለች " ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስት ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህንን ጉዳይ የተናገሩት ከሚዲያ እና ከኮሚኒኬሽን ባለሞያዎች ጋር ባደረጉት የውይይት መድረክ ነው።
" ላለፉት ዓመታት በዚህ ጉዳይ ምን ሲሰራ እንደነበር አታውቁም " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ከነገርናችሁ ከውስጥም ከውጭም ጣጣው ስለሚበዛ ነው ዝም ብለን የሰራነው " ሲሉ ገልጸዋል።
ይህ ምርት የት አከባቢ እንደሆነ በቀጥታ ባይናገሩም በንግግራቸው ወቅት " ላለፉት ሁለት ሦስት ዓመታት እኔ የምጎበኘው ጋዙን ነው እናንተ የምታዩት ስንዴውን " ሲሉ ተናግረዋል።
" እስካሁን ያልነገርናችሁ በህዳሴ ላይ የከፈልነውን ዋጋ ከፍተኛ ስለሆነ ነው " ሲሉ ፕሮጀክቱ ላለፉት ዓመታት በተለያዩ መንገዶች በሚዲያው ከሚደርስበት ጫና ለመላቀቅ በዝምታ መስራታቸውን አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት በቅርቡ ከናይጄሪያው ባለኃብት ዳንጎቴ ጋር እንደምትፈራረም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈረንጆቹ ሐምሌ ወር አጋማሽ የስምምነት ፊርማው እንደሚደረግ የገለጹ ሲሆን " በቀጣይ 3 ዓመታት ኢትዮጵያ ማዳበሪያ ይኖራታል " ሲሉ በንግግራቸው ጠቅሰዋል።
ይህ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ በጎዴ አከባቢ እንደሚገባ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) የ3 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት መሆኑን መግለጻቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

" የ3 ዓመት ህጻንን ጨምሮ 9 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል " - ፖሊስ
በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ አባሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ረፋድ በግምት 3 ሰዓት ገደማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ከሟቾቹ መካከል የ3 ዓመት ዕድሜ ያለው ሕጻን የሚገኝበት ሲሆን፤ በ8 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ ገልጿል።
አደጋው ሊከሰት የቻለው ከሃይሌ ጋርመንት ወደ ዩኒሳ አደባባይ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-78979 ኢት የሆነ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አውቶቡስ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-04273 ኢት ከሆነ ሌላ ከባድ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ እና መንገድ ስቶ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ በመግባቱ ነው፡፡
አውቶቡሱ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ከገባ በኋላ ከዩኒሳ አደባባይ ወደ ሃይሌ ጋርመንት ሲጓዝ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-77970 ኦሮ ከሆነ ዶልፊን ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ በዶልፊኑ ውስጥ ከነበሩት ተሳፋሪዎች መካከል አሽከርካሪውን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስረድቷል።
ከሟቹቹ መካከል የ3 ዓመት ሕጻን ይገኝበታል።
በሌሎች 8 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።
ከዚህ በተጨማሪ በአካባቢው ላይ የቆመ እና በጉዞ ላይ የነበረ ሌሎች ሁለት ተሽከርካሪዎች በአውቶቡሱ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ ፖሊስ ገልጿል።
#AddisAbabaPolice