Telegram Group & Telegram Channel
አቶ ብርሃኑ አዴሎ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነርነት  ዕጩ ሆነው ቀረቡ።

በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ዘመነ መንግስት የሚኒስትሮች ካቢኔ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ብርሃኑ አዴሎ ገብረማርያም ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኮሚሽነርነት ለመሰየም ዛሬ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ/ም  ፓርላማ ቀርበዋል።

ሌሎች አራት ዕጩዎችም መቅረባቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

አቶ ብርሃኑ ከዚህ ቀደም በተለያዩ መንግሥታዊ ኃላፊነቶች ላይ የሠሩት ሲሆን የመጨረሻ መንግሥታዊ ኃላፊነታቸው የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተርነት ነበር።

ከኃላፊነታቸው የተነሱት " በቀረበባቸው ቅሬታ " መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ ከ10 ዓመታት በፊት ዘግቧል።

" ከሠራተኞች እና ከተቋሙ ደንበኞች ቅሬታዎች ይቀርቡባቸው እንደነበር " ጋዜጣው በወቅቱ ዘግቧል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አቶ ብርሃኑን ከዚህ ኃላፊነት ማንሳታቸውም የሪፖርተር ዘገባ ያሳያል።

አቶ ብርሃኑ የአዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬከተር ሆነው ከመሾማቸው በፊት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው ከ1996 እስከ 2002 ዓ.ም. ለ6 ዓመታት አገልግለዋል።

በሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ መሠረት አቶ ብርሃኑ ከዚህ ኃላፊነታቸው የተነሱትም በቀረበባቸው ቅሬታ ምክንያት ነው።

ከተወለዱበት ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች አዲስ አበባ ድረስ በመምጣት በአቶ ብርሃኑ ላይ የተፈራረሙትን ቅሬታ በጊዜው ጠቅላይ ሚኒስትር ለነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ ማቅረባቸውን የሪፖርተር ዘገባ ያስታውሳል።

ይህን ተከትሎ " በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የተቋቋመ አጣሪ ኮሚቴ ባቀረበባቸው ሪፖርት ከካቢኔ ጉዳይ ሚኒስትርነታቸው እና ከኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲነሱ " መደረጉን ሪፖርተር ከ10 ዓመታት በፊት በሠራው ዘገባ ጠቅሷል።

አቶ ብርሃኑ በመንግሥታዊ ተቋማት ከነበራቸው ኃላፊነት በተጨማሪ አወዛጋውን የ1997 ምርጫ ተከትሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ነበሩ።

የትምህርት ሁኔታቸው ምን ይመስላል ?

ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ አላቸው። በዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ከሕንድ አገር የማስተርስ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል።

የስራ ህይወታቸው ምን ይመስላል ?

- ከመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ ዩኒቨርሲቲ አስተምረዋል።

- በዞን ፋይናንስ መምሪያ የህግ አማካሪ ሆነው አገልግለዋል።

- የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ባገኙበት የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የህግ ፋካልቲ ለ3 ዓመታት አስተምረዋል።

- በቀድሞው ደቡብ ክልል የፍትህ ቢሮ ኃላፊነት ላይ ሰርተዋል። ከዛ በመቀጠልም በቀረበባቸው ቅሬታዎች ከስልጣን ወደተነሱባቸው የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት አቅንተዋል።

- ከመንግስታዊ የሥራ ኃላፊ ከተነሱ በኋላ ላለፉት 10 ዓመታት በጥብቅና እና በህግ ማማከር ስራ ላይ መሰማራታቸውን ለፓርላማ አባላት የቀረበው የስራ ልምድ ያሳያል።

@tikvahethiopia

group-telegram.com/tikvahethiopia/94128
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
group-telegram.com/tikvahethiopia/94128

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

"The result is on this photo: fiery 'greetings' to the invaders," the Security Service of Ukraine wrote alongside a photo showing several military vehicles among plumes of black smoke. READ MORE Also in the latest update is the ability for users to create a unique @username from the Settings page, providing others with an easy way to contact them via Search or their t.me/username link without sharing their phone number. After fleeing Russia, the brothers founded Telegram as a way to communicate outside the Kremlin's orbit. They now run it from Dubai, and Pavel Durov says it has more than 500 million monthly active users. Lastly, the web previews of t.me links have been given a new look, adding chat backgrounds and design elements from the fully-features Telegram Web client.
from us

Telegram TIKVAH-ETHIOPIA
FROM American