Telegram Group & Telegram Channel
TIKVAH-ETHIOPIA
" ' ብር (ጉቦ) ክፈሉና እንቀጥልላቹ ' ያለን የቴክኒክ ክፍል ሰራተኛ አለ " - ቅሬታ አቅራቢዎች በአዲስ አበባ ከተማ በለሚኩራ ክፍለ ከተማ በቦሌ አራብሳ ኮንዶሚኒየም ሳይት 3 የብሎክ 734 እና 735 ነዋሪዎች ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በገቡት የቆጣሪ እዳ ውዝግብ ምክንያት ሃይል ከተቋረጠባቸው 1 ወር ከ 5 ቀን መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ…
" ከክፍያ ለመሸሽ የተቋሙን ገጽታ ማበላሸት አይቻልም በህግ እንጠይቃለን ፣ ከፖሊስ እና ጸረ ሙስና ጋር በመሆን አጣርተን እርምጃ እንወስዳለን " -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በቦሌ አራብሳ ሳይት 3 ብሎክ 734 እና 735 የጋራ መኖሪያ መንደር የሚኖሩ ነዋሪዎች ከቆጣሪ እዳ ጋር በተገናኘ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ከጉዳዩ ጋር በተገናኘ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ኦልጅራ ዝርዝር ምላሽ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

አቶ ብርሃኑ ኦልጅራ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" ነዋሪዎቹ ሃይል የተቋረጠባቸው በየብሎኩ የገባላቸውን ቆጣሪዎች ትተው በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ለኮንስትራክሽን ሥራ የገባውን ቆጣሪ እንዳይቆጥር አድርገው ሲጠቀሙ በእኛ ኢንስፔክሽን ቲም (የምልከታ ቡድን) በ15/04/17 ዓ/ም በተረገ ምልከታ ተደርሶባቸው ነው።

በእኛ አሰራር መሰረት ደግሞ ቆጣሪን እንዳይቆጥር አድርጎ ሲጠቀም የተገኘ ካለ አገልግሎቱን በማቋረጥ ሂሳቡ ይሰላል በድጋሚ ሃይል ለማግኘት ያንን ሂሳብ መክፈል አለበት።

በዚህ ምክንያት ሃይል ተቋርጧል ከተቋረጠ በኋላ ሲጠቀሙ የነበሩትን ሂሳብ አስልተን በደብዳቤ ክፈሉ ብለን አሳውቀናቸዋል።

በእነሱ ስም ቆጣሪው ስለሌለ በቤቶች ልማት ጽ/ቤት ስም አሳውቀናቸዋል በተደጋጋሚ ለመክፈል ፈቃደኛ አልነበሩም ኤሌክትሪኩ ተቋርጦ ነው ያለው።

ቆጣሪው ቢሉ የወጣው በኮንትራክተሩ ሳይሆን በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ነው እኛ የምናውቀው በኮንትራክተር የገባ ቆጣሪ የለም ውላችንም ከቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር ነው ኮንትራክተሩን አናውቀውም።

አንድን ኮንትራክተር ሊቀጥረው የሚችለው የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ነው እኛም ውል የሚኖረን ከኮንትራክተሩ ጋር ሳይሆን ኮንትራክተሩን ቀጥሮ ከሚያሰራው ተቋም ጋር ነው ሃላፊነቱን ወስዶ ደብዳቤ ጽፎ ቆጣሪ ይግባ የሚለው የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ነው።

በስርቆት ቆጣሪ በማሰናከል ኤሌክትሪክ ሲጠቀሙ ሲገኝ የመጀመሪያው እርምጃ አገልግሎት ተቋርጦ መንግስት ያጣውን ገንዘብ ታስቦ ክፈሉ ብሎ ማሳወቅ ነው ነዋሪዎች እኛን አይመለከትንም እያሉ ነው ነገር ግን እየተጠቀሙ ነው አይ ቤቶች ልማት እኔን አይመለከተኝም ኮንትራክተሩን ነው ካለም ሃላፊነት መውሰድ አለበት " ብለዋል።

አቶ ብርሃኑ ነዋሪዎቹ ቆጣሪው እንዳይቆጥር በማሰናከል ካርድ መሙላት ካቆሙ ጀምሮ በሦስት ቆጣሪዎች የተጠራቀመው እዳ ቅጣትን ጨምሮ 480,538 ብር መሆኑን ተናግረዋል።

ይህንን ያህል መጠን ኤሌክትሪክ ሃይል የተጠቀሙት ተብለው ለቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተላከ ደብዳቤ የተገለጹት የጋራ መኖሪያ መንደሩ ነዋሪዎች ብሎክ 734 ፣ 735 ፣ 750 እና 751 ነዋሪዎች ሲሆኑ ነገር ግን ቆጣሪዎቹ የተመዘገቡት በኮርፖሬሽኑ በኩል በመሆኑ የተጠቀሰውን ክፍያ እንዲፈጽም አገልግሎቱ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽንን በተደጋጋሚ መጠየቁን ነገር ግን እስካሁን ክፍያው አለመፈጸሙን አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል።

ነዋሪዎች ሃይል ከቆጣሪው ጠልፈው አለመጠቀማቸውን እና ቆጣሪዎቹ መንገድ ላይ የሚገኙ በመሆናቸው ምክንያት ነዋሪ ያልሆኑ አካላት መስመሩን እንደሚጠቀሙ ይገልጻሉ ታውቁታላቹ ወይ ? ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄ ዳይሬክተሩ ምላሽ ሰጥተዋል።

" በእኛ በኩል እንደዚህ አይነት ጥቆማ አልደረሰንም ይህንን ቆጣሪ ካስገባን በኋላ በየወሩ ለንባብ ስንመጣ እንዲሁም በእቅድ ምልከታ እናደርጋለን የተጠቀስነውን ችግር ያገኘነው ለምልከታ ስንመጣ ነው። ይሄንን ጥቆማ እንመለከተዋለን በቦታው ስንሄድ ግን የተባለውን ጉዳይ አልተመለከትንም " ብለዋል።

ቆጣሪዎቹ በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በኩል ለግንባታ አላማ ነበር የተቀመጡት ግንባታው ከተጠናቀቀ ቆይቷል ለምን አልተነሱም ስንል ላነሳነው ጥያቄም።

" ቤቶች ልማት አገልግሎቱን ጨርሰናል ቆጣሪው ይነሳልን አገልግሎቱን አንጠቀመውም ብለው ደብዳቤ መጻፍ አለባቸው ውል አለን ዝም ብለን ቆጣሪ ማንሳት አይቻልም ይግባልን ተብሎ በደብዳቤ እንደተጠየቀው ሁሉ ይነሳልን ብለው ሲጠይቁ ብቻ ነው የሚነሳው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ዳይሬክተሩ ነዋሪዎች የተቋረጠው ሃይል ተመልሶ እንዲቀጠል ጉቦ ክፈሉ ያለን ባለሞያ አለ ሲሉ ላነሱት ቅሬታም " ከክፍያ ለመሸሽ የተቋሙን ገጽታ ማበላሸት አይቻልም በህግ እንጠይቃለን ፣ ከፖሊስ እና ጸረ ሙስና ጋር በመሆን አጣርተን እርምጃ እንወስዳለን " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽንን ምላሽ የሚያካትት ይሆናል።

በተጨማሪም ነዋሪዎች ከተጠቀሱት ቆጣሪዎች ላይ ሃይል መቀጠላቸውን እና አለመቀጠላቸውን እንዲሁም ሌሎችም ነዋሪዎች ያቀረቧቸውን ቅሬታዎች በሚመለከት በቦታው ተገኝቶ ምልከታ ማድረግ እንደሚቻል የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ኦልጅራ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቦታው በመገኘት ቅሬታውን በማጣራት የሚያሳውቅ መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia

group-telegram.com/tikvahethiopia/94109
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
group-telegram.com/tikvahethiopia/94109

View MORE
Open in Telegram

Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Perpetrators of such fraud use various marketing techniques to attract subscribers on their social media channels. Sebi said data, emails and other documents are being retrieved from the seized devices and detailed investigation is in progress. Russians and Ukrainians are both prolific users of Telegram. They rely on the app for channels that act as newsfeeds, group chats (both public and private), and one-to-one communication. Since the Russian invasion of Ukraine, Telegram has remained an important lifeline for both Russians and Ukrainians, as a way of staying aware of the latest news and keeping in touch with loved ones. Pavel Durov, a billionaire who embraces an all-black wardrobe and is often compared to the character Neo from "the Matrix," funds Telegram through his personal wealth and debt financing. And despite being one of the world's most popular tech companies, Telegram reportedly has only about 30 employees who defer to Durov for most major decisions about the platform. These administrators had built substantial positions in these scrips prior to the circulation of recommendations and offloaded their positions subsequent to rise in price of these scrips, making significant profits at the expense of unsuspecting investors, Sebi noted.
from tw

Telegram TIKVAH-ETHIOPIA
FROM American