Telegram Group Search
የትምህርት ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክተር የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ወራት የዝግጅት ምዕራፍ ውይይት አካሄደ፡፡
(መስከረም 10 ቀን 2017 ዓ.ም) የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የትምህርትና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ወራት የዝግጅት ምዕራፍ ውይይት የ9ኙም ቅ/ጽ/ቤት የኢንፔክሽን ዳይሬክተሮች፣የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጥ እና የትምህርት ስልጠና ጥራት ማረጋገጥ ቡድን መሪዎች በጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ውይይት ተካሂዷል፡፡
በእለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቅሩ ገቢሳ እንደገለጹት የዘርፍ ግንኙነት እርስ በርስ ለመማማርና የተሻለ አሰራርን ቀስሞ ወደራስ ተግባራዊ ለማድረግና ተሞክር ወስዶ ለመስራት እንዲሁም ጤናማ ግንኙነትን ለመፍጠር አስተዋጽኦ አለው ብለዋል::
የቀረቡት የመወያያ ነጥቦችም በዋናነት የድንገተኛ ኢንስፔክሽን ቼክሊስት ማዘጋጀትና ማወያየት፣ የBSC ካስኬዲንግ ያለበትን ደረጃ መገምገም፣የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት በ2016 የስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ውጤት ከ40% በታች አምጥተው በማስጠንቀቂያ የቆዩ ተቋማት የውሳኔ ሃሳብ ውይይት ማድረግ እንዲሁም በጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት በዝግጅት ምዕራፍና የመረጃ አደረጃጀት 9ቅ/ጽ/ቤት ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች የልምድ ልውውጥ አከናውኗል፡፡
በመጨረሻም ለተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች የባለስልጣኑ የትምህርት ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አንዋር ሙላት ማብራሪያ ሰተውበታል፡፡
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.group-telegram.com/AAEQOCAA.com
ግብዣ
(መስከረም 10 ቀን 2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ አዲስ ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን ፕሮግራም ዛሬ ከምሽቱ 2፡30 ላይ እንድትመለከቱ ጋብዘናችኋል፡፡
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.group-telegram.com/AAEQOCAA.com
ባለስልጣኑ ዘወትር ሰኞ ጠዋት የሚያካሄደውን የሠራተኞች የማነቃቂያ እና ትምህርታዊ የውይይት መርሃ-ግብር አከናወነ፡፡
(መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም) በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ሰኞ ማለዳ የሚቀርበው የማነቃቂያና ትምህርታዊ የውይይት መርሃ-ግብር ጤናማ የሆነ የኑሮ ዘይቤ በሚል ርዕስ በዛሬው ዕለትም የባለስልጣኑ ሰራተኞች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
የመወያያ ሃሳቡን ያቀረቡት የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥ ባለሙያ የሆኑት አቶ ረታ ሚደቅሳ ሲሆኑ ጤናማ የመሆን ጥቅም ምንድነው? ጤናማ ለመሆን ምልክቶቹ ምንድ ናቸው?ጤንነትንስ የሚያጓድሉት ምንድ ናቸው?ለጤና ችግር መፍትሄውስ ምድነው? የሚሉ ዝርዝር ሃሳቦችን አንስተዋል፡፡በዚህም ሰውነታችን በአግባቡ ስራውን የሚያከናውን ከሆነ ጤናማ ይባላል፡፡የአእምሮ፣ የአካልና የማህበራዊ ግንኙነታችን የተሟላ ከሆነ ጤናማና ውጤታማ የሆነ ተግባርን እናከናውናለን፡፡ከዚህም ሌላ አንድ ሰው ጤናማ ከሆነ በሁሉም አገልግሎቱ ውጤታማ አስተዋጽኦ ለማህበረሰቡ ያደርጋል ብለዋል፡፡
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.group-telegram.com/AAEQOCAA.com
ቅ/ጽ/ቤቱ በትስስርና በቅንጅታዊ ስራዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ፡፡
የትስስር ስራዎች በዋናነት ለአንድ ተቋም የተሰጡ ስራዎች ወይም ተግባራት እንዲሳኩ የሌሎች የውጭ ባለድርሻ አካላት እገዛ በጋራ በማቀድ ፣የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ እና ተጠያቂነት ጭምር በማስቀመጥ በጋራ የሚከናወኑ ተግባራት ስለመሆናቸዉ ተገለፀ፡፡
(መስከረም 15 ቀን 2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባላስልጣን የጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቅሩ ገቢሳ የ2017 በጀት ዓመት በትስስር እና በቅንጅታዊ ስራ ከተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች ጋር በቅንጅታዊ አሰራር በጋራ ሊሠሩ በታቀዱት ስራዎች ዙሪያ በተደረገዉ የዉይይት መድረክ ላይ በመገኘት እንደተናገሩት የትስስር ስራዎች በዋናነት ለአንድ ተቋም የተሰጡ ስራዎች ወይም ተግባራት እንዲሳኩ የሌሎች የውጭ ባለድርሻ አካላት እገዛ በጋራ በማቀድ፣የጊዜ ገደብ እና ተጠያቂነት ጭምር በማስቀመጥ በጋራ የሚከናወኑ ተግባራት መሆናቸዉን በመግለጽ የእለቱን የቅንጅታዊ አሰራር የስምምነት ሰነድ ፊርማ መድረክ በመክፈቻ ንግግር ከፍተዋል፡፡
በተጨማሪም ስራ አስኪያጁ የመድረኩን ዓላማ ስገልፁ በ2017 ዓ.ም በቀጣይ ወራት በትስስር መሰረት ሊከናወኑ የታቀዱት ተግባራት ዙሪያ በጋራ ተወያይተን የጋራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ወደ ትግበራ ምዕራፍ ለመግባት ነዉ ብለዋል።
በመቀጠልም የቅ/ጽ/ቤቱ የመምህራንና የት/ቤት አመራር የሙያ ፍቃድ ባለሙያና የእቅ/ዝግ/ክትትልና ግምገማ ባለሙያ ተወካይ የሆኑት አቶ አሸናፊ መለሠ በበጀት ዓመቱ በትስስርና በቅንጅት የሚሰሩ ስራዎችን እቅድ በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን የትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ሊያሳካቸው ያቀዳቸውን ተግባራት ለማሳካት ይረዳ ዘንድ በበጀት ዓመቱ የዝግጅት ምዕራፍ ከሰባት ሴከተሮች፣ሶስት ኮሌጆች እና ሁለት ሲቪክ ማህበር ጋር የጋራ መግባቢያ ሰነድ የጋራ በማድረግ የመፈራረም ስነስርዓቱን አከናዉኗል።
በመጨረሻም ከተሳታፊዎቹ ለተነሱት ጥያቄዎች ማብራርያና ምላሽ የመስጠት እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል ።
ምንጭ፡-የጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.group-telegram.com/AAEQOCAA.com
በቅንጅታዊ አተገባበር ላይ ድጋፍና ክትትል ተደረገ፡፡

(መስከረም 15 ቀን 2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ከከንቲባ ጽ/ቤት በመጡ የድጋፍና ክትትል ቡድን በ2017 የቅንጅታዊ አተገባበር ስራዎች ላይ ድጋፍና ክትትል ተደረገለት፡፡

የድጋፍና ክትትል ቡድኑ ባለስልጠኑ ከቅንጅታዊ ስራዎች አንጻር ያከናወነውን ተግባር ጥንካሬዎቹን እና ክፍተቶቹን በመለየት አስተያየት የሰጠ ሲሆን ሰፋ ያለ ውይይትም ተደርጎበታል፡፡

የክትትልና ድጋፍ ቡድኑ አባላት ባለስልጣኑ በዝግጅት ምዕራፍ በቅንጅታዊ ተግባራት ያከናወነው ተግባር መልካም መሆኑን ጠቅሰው የተሰጠውን አስተያየት መሰረት በማድረግ ለቀጣይ የበለጠ በርካታ ተግባራትን በማከናወን የበለጠ ሃላፊነቶችን መወጣት ይገባል ብለዋል፡፡

አቶ ዳኛው ገብሩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ በክትትልና ድጋፉ ወቅት በሰጡት አስተያየት ድጋፍና ክትትል ራስን መልሶ ለማየትና ለማስተካከል የሚጠቅም ሲሆን ከትስስርም ጎን ለጎን ከተቋማት ጋር በመናበብ ተግባራትን ማከናወን ውጤታማ ያደርጋል ብለዋል፡፡በተጨማሪም የድጋፍና ክትትል ቡድኑ ድጋፍ የተሻለ ውጤታማ ለመሆን ያስችላል ብለዋል፡፡
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.group-telegram.com/AAEQOCAA.com
ግብዣ
(መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ አዲስ ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን የቶክሾው ፕሮግራም እሁድ መስከረም 19/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 ላይ እንድትመለከቱ ጋብዘናችኋል፡፡
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.group-telegram.com/AAEQOCAA.com
2024/09/30 02:34:48
Back to Top
HTML Embed Code: